ኮሮናቫይረስ ያጠላባቸው በየጎዳናው የሚለምኑ የናይጄሪያ ታዳጊዎች

ኮሮናቫይረስ ያጠላባቸው በየጎዳናው የሚለምኑ ታዳጊዎች

የፎቶው ባለመብት, JIGAWA STATE GOVERNMENT

በሰሜናዊ ናይጄሪያ ቁርዓን ይማሩ የነበሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች ወደየቤታቸው እንዲመለሱ በጭነት መኪና የተከተቱት በቅርቡ ነበር። እርምጃው የተወሰደው የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ነው።

የጭነት መኪና ቢታገድም፤ ታዳጊዎቹን የጫኑ መኪኖች ግን ልዩ ፍቃድ ተሰጥቷቸው ነበር። በመንግሥት አስተባባሪነት ታዳጊዎች በብዛት የተንቀሳቀሱበት እርምጃ ሳይሆን አይቀርም።

ናይጄሪያ 200 ሚሊዮን ዜጎች አሏት። ገሚሱ ሙስሊም ገሚሱ ደግሞ ክርስቲያን።

በሀውሳ ቋንቋ ታዳጊዎቹ ‘አልማጅሪ’ ይባላሉ። ከአረብኛ ቃል የተወረሰ ነው። ከታዳጊዎቹ መካከል ምን ያህሉ ወደቤታቸው እንደተመለሱ አይታወቅም።

ነገር ግን ካዱና ግዛት 30 ሺህ ልጆች አስመልሻለሁ ብላለች።

ከታዳጊዎቹ መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት በኮቪድ-19 ተይዘዋል። ወደየቤታቸው አንዲመለሱ ትዕዛዝ የተላለፈው የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት ቢሆንም፤ ውሳኔ ወረርሽኙ አንዲዛመት መንገድ ከፍቷል።

ችላ የተባለው ማስጠንቀቂያ

ከታዳጊዎቹ መካከል በትውልድ ቀዬያቸው ሲደርሱ ለይቶ ማቆያ ገብተው የተመረመሩ አሉ። በካንዱ ግዛት ከተመረመሩት 196 ታዳጊዎች 65 ያህሉ ላይ በሽታው ተገኝቷል። በጎምቤ ግዛት ደግሞ ከ168 ታዳጊዎች 91ዱ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

የሌሎች ታዳጊዎች የምርመራ ውጤት አሁንም እየተጠበቀ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች እስካሁን አልተመረመሩም። ናይጄሪያ በበቂ ሁኔታ ምርመራ እያካሄደች አይደለም በሚል ትተቻለች።

የናይጄሪያ የኮቪድ-19 መከላከያ ግብረ ሀይል ኃላፊ፤ ታዳጊዎቹን ወደቤታቸው መመለስ አደገኛ ነው ቢሉም ሰሚ አላገኙም።

በሰሜናዊ ናይጄሪያ የሚገኙ አገረ ገዢዎች ወረርሽኙን የቁርዓን ትምህርትን ለማቆም ተጠቅመውበታል። ትምህርቱ በአብላጫው ሙስሊሞች በሚኖሩበት ሰሜናዊ ናይጄሪያ የትምህርት ሥርዓት አካል ነው።

የካዱና አገረ ገዢ ናሲር ኤልሩፊያ የትምህርት ሥርዓቱ ታዳጊዎቹንም ናይጄሪያንም እየጠቀመ ስላልሆነ ማስወግድ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ታዳጊዎቹ ዘመናዊ ትምህርት ቢማሩ ይሻላልም ብለዋል። “ታዳጊዎቹ በየጎዳናው የሚበሉትን ከሚለምኑ አልማጅሪን ማዘመን ይቻላል” ብለዋል አገረ ገዢው።

አብዛኞቹ ታዳጊዎቹ ከአቅመ ደካማ ቤተሰብ የተገኙ ናቸው። ከአምስት እስከ አስር ዓመት በቁርዓን መምህር ሥር ይሆናሉ።

የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው ከአምስት እስከ 14 ዓመት የሞላቸው 10.5 ሚሊዮን ናይጄሪያውያን ትምሀርት ቤት አልገቡም። ድርጅቱ የአልማጅሪን ሥርዓት እንደ ትምህርት ቤት አይቆጥረውም።

በየጎዳናው የሚለምኑ ታዳጊዎች

በአልማጅሪን ትምህርት ቤቶች አምስት ዓመት የሞላቸው አዳጊዎች ለመምህራቸው በየሳምንቱ እሮብ 100 ናይራ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።

ማላማ በመባል የሚባሉት መምህራን ክፍያው ለትምህርት ቤቱ እድሳት እንጂ ለግል ጥቅማችን አይውልም ይላሉ።

አብዛኞቹ አዳጊዎች ገንዘቡን ለማግኘት በየጎዳናው ይለምናሉ።

የሚኖሩበት ሁኔታ ምቹ አይደለም። በተጨናነቀና ንፅህናው ባልተጠበቀ ቦታ የሚኖሩት አዳጊዎቹ፤ ላሳምንታት ሰውነታቸውን ላይታጠቡ ይችላሉ። ይህም ከእስልምና አስተምሮት ውጪ ነው።

መምህራኑም ድሃ ናቸው። በቂ የማስተማር ስልጠናም አልወሰዱም።

ትምህርት ቤቶቹ ከሁለት ወር በፊት እንዲዘጉ ሲወሰን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳጊዎች መጠለያ ስሌላቸው በየጎዳናው መለመናቸውን ቀጥለዋል።

መንግሥት ታዳጊዎቹ በሽታውን ሊያሰራጩ ይችላለሉ ብሎ በየቤታቸው እንዲመለሱ ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም፤ ውሳኔው ዘግይቷል።

የቀድሞ አልማጅሪን የነበሩት ኢምራን ሞሐመድ እንደሚሉት፤ ታዳጊዎቹ በበሽታው የተያዙት ሲለምኑ ሊሆን ይችላል።

ላለፉት ዓመታት ይህንን የትምህርት ሥርዓት ለማቆም ውይይቶች ሲካሄዱ ነበር። ሆኖም ግን ከትምህርት ቤቶቹ ደጋፊዎች የእስልምና ትምህርትን ልታጠፉ ነው የሚል ተቃውሞ ቀርቧል።

ተስፈኛው አባት

የቀድሞው ፕሬዘዳንት ጉድላክ ጆናታን በቢሊዮን የሚቆጠር የናይጄሪያ ገንዘብ አውጥተው ነበር እነዚህን ትምህርት ቤቶች ያስገነቡት። ፕሬዘዳንቱ ክርስቲያንና ከደቡብ ናይጄሪያ የተገኙ መሪ ነበሩ።

እሳቸውን ተከትለው ሥልጣን የያዙት የሰሜን ናይጄሪያው ሙስሊም መሪ ሙሐመዱ ቡሐሪ ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጉ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ከተማሪዎቹ መካከል ጎዳና የወጡም አሉ።

ሻይፉ ያዩ የተባሉ አባት፤ “ትምርት ቤቶቹ የገነት በር ናቸው” ይላሉ፤ እንዲዘጉም አይፈልጉም።

የ15 ዓመት ልጃቸው አሁንም ድረስ በካኖ ግዛት አልማጅሪን ነው።

“አሁን ሁለተኛ ዓመቱ ነው። ከአምስት ዓመት በኋላ ስለ ቁርዓንና ስለ ኃይማኖቱ እውቀት አካብቶ እንደሚመጣ ተስፋ አፈርጋለሁ” ይላሉ ሻይፉ።

ሐሳባቸውን የማይቀበሉም አሉ።

ሼክ አብዱላሂ ጋራንግማዋ፤ የትምህርት ሥርዓቱ ተበዝብዟል ይላሉ። በሰሜን ናይጄሪያ የሚገኝ መስጅድ ኢማም ሲሆኑ፤ “አሁን ላይ ትምህርት ቤቶቹ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ግዞት ነው። መንግሥት ማመንታቱን ትቶ ቶሎ ሊዘጋቸው ይገባል” ሲሉም ያስረዳሉ።

“ታዳጊዎቹ የእስልምና ትምህርት እየተሰጣቸው አይደለም። ብዙዎቹ ወንጀለኛና የፖለቲከኞች የወንጀል ድርጊት አስፈጻሚ ቅጥረኛ ነው የሚሆኑት” ይላሉ ሼክ አብዱላሂ።

ኮሮና