የዓለም መሪዎች ስለዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ምን እያሉ ነው?

ጀስቲን ትሩዶ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ጋር በተደጋጋሚ ተገናኝተዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ጀስቲን ትሩዶ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ጋር በተደጋጋሚ ተገናኝተዋል

የዓለም መሪዎች እና ታላላቅ ሰዎች በ96 ዓመታቸው ባረፉት ንግሥት ኤልዛቤጥ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን እየገለጹ ነው።

በዚህም ንግሥቲቱ በነበራቸው ኃላፊነትን የመወጣት ብቃትና ጽናት እንዲሁም መልካምነታቸውን በመጥቀስ ሐዘናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በንግሥት ኤልዛቤጥ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያም መንግሥት እና ሕዝብ ስም “በግርማዊት ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ሞት የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን፤ ለብሪታኒያ ንጉሣዊ ቤተሰብ፣ መንግሥት እና ሕዝብ” አገልጻለሁ ብለዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

የ X ይዘት መጨረሻ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን “የፈረንሳይ ወዳጅ” በማለት የገለጿቸው ንግሥቲቷ “ቀና ልብ ያላቸው” ብለዋቸዋል።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ንግሥቲቱ በነበራቸው ብቃትና “ባልደከመ የሥራ ሥነ ምግባር” ዓለምን ማርከው ነበር።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ከንግሥት ኤልዛቤጥ ጋር ባለፈው ዓመት በተገናኙበት ወቅት

የፎቶው ባለመብት, 10 DOWNING STREET

የምስሉ መግለጫ, ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ከንግሥት ኤልዛቤጥ ጋር ባለፈው ዓመት በተገናኙበት ወቅት

ንግሥቲቱን በመጀመሪያ ከ40 ዓመታት በፊት አግኝተዋቸው የነበሩትና ባለፈው ዓመት በተገናኙበት ጊዜ አስደሳች አቀባበል ያደረጉላቸው የአሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደግሞ፣ “ከንግሥትም በላይ ነበሩ፣ የኖሩበት ዘመን መገለጫ ነበሩ” በማለት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ በንግሥና ዘመናቸው 13 የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶችን አግኝተዋል።

ንግሥት ኤልዛቤጥ ዋይት ሐውስ ውስጥ ከጆርጅ ቡሽ፣ ከባላቤታቸው ላውራ ቡሽና ከልዑል ፊሊፕ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ንግሥት ኤልዛቤጥ ዋይት ሐውስ ውስጥ ከጆርጅ ቡሽ፣ ከባላቤታቸው ላውራ ቡሽና ከልዑል ፊሊፕ ጋር

ዶናልድ ትራምፕም “የግርማዊነታቸውን መልካም ወዳጅነትን፣ ታላቅ ጥበብን አስደናቂ ቀልድ አዋቂነታቸውን ፈጽሞ አልረሳውም” ብለዋል።

“ታላቅ እና ውብ ሴት ነበሩ፣ እሳቸውን የሚመስል ማንም ሰው አልነበረም” በማለት ትራምፕ በራሳቸው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ሐዘናቸውን አስፍረዋል።

ሌላኛው የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ወደብሊው ቡሽም ከንግሥቲቱ ጋር ሻይ የጠጡበትን ጊዜ በማስታወስ ለዳግማዊት ኤልዛቤት ያላቸውን አድናቆት ገልጿል።

ባራክ ኦባማ እና ንግሥት ኤልዛቤት በባኪንግሃም ቤተመንግሥት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ባራክ ኦባማ እና ንግሥት ኤልዛቤት በባኪንግሃም ቤተመንግሥት

ርዕሰ ብሔሯ የነበሩት ካናዳ በንግሥቲቱ የሥልጣን ዘመን ውስጥ 12 ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተፈራርቀውባታል።

በእጅጉ ያዘኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ንግሥቲቱ ለካናዳውያን “በግልጽ የሚታይ ጥልቅ እና ታማኝ ፍቅር ነበራቸው።”

በተጨማሪም ከአፍሪካ የኬንያው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፤ ከእስያ ደግሞ የታላላቆቹ አገራት የቻይና እና የሕንድ መሪዎች በንግሥቲቱ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

በሌሎች በዓለም ዙሪያ ያሉ የአገራት መሪዎች እና ታላላቅ ሰዎች በዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት ሞት ሐዘናቸውን ለንጉሣውያኑ ቤተሰብ፣ ለታላቋ ብሪታኒያ መንግሥት እና ሕዝብ የሐዘን መግለጫ እያስተላለፉ ነው።