በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ውስጥ ቁልፍ ጉዳይ የሆነው ስፍራ

ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲሞቱ ሚሊዮኖች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

ባለፈው መጋቢት ወር የተደረሰው የተኩስ ማቆም ስምምነት የተስፋ ጭላንጭል ቢፈጥርም፣ ነሐሴ ላይ ጦርነቱ ዳግም አገርሽቷል።

ጦርነቱ ብዙ ምስቅልቅሎችን አምጥቷል። የምዕራብ ትግራይ/ወልቃይት ጉዳይ ደግሞ አንዱ ነው። ለመሆኑ የወልቃይት ጉዳይ ዋነኛ ነጥብ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው?