የሳምንቱ አጋማሽ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማክሰኞ፣ ረቡዕ እና ሐሙስ ቀጥለው እንዲከናወኑ መርሐ ግብር ወጥቶላቸዋል።
ኒውካስል ዩናይትድ ከቶተንሃም እና ሊቨርፑል ከሰንደርላንድ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው።
የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን በሳምንቱ አጋማሽ የሚከናወኑ ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ገምቷል።
ማክሰኞ

በርንመዝ ከ ኤቨርተን
ሁለቱም ቡድኖች በሳምንቱ መጨረሻ ከባድ ሽንፈትን አስተናግደዋል።
በርንመዝ 2 ለምንም ከመምራት 3 ለ 2 በሰንደርላንድ ተሸንፏል።
ኤቨርተን ደግሞ በኒውካስል 4 ለ 1 በመሸነፍ ጨዋታውን አጠናቋል።
ጨዋታውን በጠባብ የጎል ልዩነት በርንመዝ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 - 1 [ውጤት 0 - 1]
ፉልሃም ከ ማንቸስተር ሲቲ
ፉልሃም በሜዳው ጥሩ ቢሆንም ከሲቲ ጋር ያለው ውጤት ግን አሳሳቢ ነው።
ሁለቱ ቡድኖች 18 ጊዜ በተገናኙባቸው ያለፉት ጨዋታዎች ሲቲ 54 ጎሎችን አስቆጥሮ ሰባት ብቻ በማስተናገድ ሁሉንም አሸንፏል።
ሲቲ ከሊድስ ጋር በነበረው ጨዋታ ዕድለኛ ሆኖ ሦስት ነጥቦችን አግኝቷል።
ግምት፡ 0 - 2 [ውጤት 4 - 5]
ኒውካስል ከ ቶተንሃም
የቶተንሃሙ አሠልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ውጤት የማስመዝገብ ጫና አለባቸው።
ደጋፊዎች ተጫዋቾች ላይ ተቃውሞ ከማሰማታቸው አንጻር ቡድኑ ከሜዳ ውጭ መጫወቱ ለተጫዋቾቹ ጥሩ ሊሆን ይችላል።
ዘንድሮ በካራባኦ ዋንጫ ቶተንሃም በኒውካስል ተሸንፏል።
ግምት፡ 2 - 0 [ውጤት 2 - 2]
ረቡዕ
አርሴናል ከ ብሬንትፎርድ
አርሴናል ወደ አንድ ሰዓት ገደማ በ10 ተጫዋች ከተጫወተው ቼልሲ ጋር አቻ መለያየቱ አስገርሞኛል።
ተጫዋች ባይወጣ ውጤቱ ጥሩ የሚባል ይሆን ነበር።
በዚህ ጨዋታ ጎሎችን አስቆጥረው ብሬንትፎርድን እንደሚያሸንፉ እገምታለሁ።
ብሬንትፎርዶች በመልሶ ማጥቃት መጫወትን ቢመርጡም የሚሳካላቸው አይመስለኝም።
ግምት፡ 3 - 0
ብራይተን ከ አስቶን ቪላ
ቪላ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ ቢሆንም ይህ ጨዋታ ግን ፈታኝ ይሆንበታል።
ብራይተንም በሜዳው በጥሩ አቋም ላይ ነው የሚገኘው።
ቡድኑ ጥሩ ጥሩ አጥቂዎች እና ምርጥ ቡድን ስላለው እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 - 1
በርንሌይ ከ ክሪስታል ፓላስ
የፓላሱ አለቃ ኦሊቨር ግላስነር ተጫዋች እንዲመጣላቸው እየጠየቁ ነው።
አንድ አሠልጣኝ ተመሳሳይ ጥያቄ ካቀረበ የመጥፎ ምልክት ማሳያ ነው።
በርንሌይ ጥሩ አቋም ላይ ባለመሆኑ ይህንን ጨዋታ ፓላስ ያሸንፋል።
የስኮት ፓርከር ቡድን ጎሎችን የማስቆጠር ችግር አለበት።
ግምት፡ 0 - 1
ዎልቭስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት
ዎልቭስ ካለፉት 13 ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻ ሰብስቧል።
ቡድኑ ፔፕ ጋርዲዮላ፣ አሌክስ ፈርጉሰን ወይንም ጆሴ ሞሪንሆን ቢያመጡም ከመውረድ አይተርፉም።
ፎረስት በሳምንቱ መጨረሻ ቢሸነፍም ይህንን ጨዋታ ያሸንፋል።
ግምት፡ 0 - 1
ሊድስ ዩናይትድ ከ ቼልሲ
ሊድስ በሳምንቱ መጨረሻ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ጥሩ መፎካከር ቢችልም ተሸንፏል።
ቡድኑ ጥሩ መነቀሳቀስ እየቻለም ውጤት እያጣ ይገኛል።
ቼልሲ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ ከመሆኑ አንጻር ይህንን ጨዋታ ያሸንፋል።
ግምት፡ 0 - 2
ሊቨርፑል ከ ሰንደርላንድ
ሊቨርፑል ያለ ሞ ሳላህ ማሸነፍ ችሏል።
ሰንደርላንድ ወደ አንፊል በማቅናት ጥሩ ተጫውቶ ማሸነፍ የሚችል ቡድን እንደሆነ አስባለሁ።
ሊቨርፑል ባለፉት በፎረስት እና በፒኤስቪ ሲሸነፍ መጥፎ አልነበረም። ስለዚህ ቀያዮቹ እንደሚያሸንፉ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 - 1

ሐሙስ
ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ዌስት ሃም
ማንቸስተር በሳምንቱ መጨረሻ ፓላስን ቢያሸንፍ ተገቢ ውጤት አልነበረም።
ሁለቱንም ቡድኖች ለመገመት አስቸጋሪዎች ናቸው።
በዚህ ጨዋታ ብዙ ጎል አይቆጠርም።
ግምት፡ 2 - 0















