በደቡብ አፍሪካ የተቀበሩት የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዝዳንት አስክሬን ዛምቢያ እንዲወሰድ ፍርድ ቤት ወሰነ

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የዛምቢያ መንግሥት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉን አስክሬን ወደ ዛምቢያ ወስዶ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈጸም እንደሚችል የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ወሰነ።
የኤድጋር ሉንጉ ቤተሰቦች ይህንን በመቃወም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የቀብር ሥነ ሥርዓት ፈጽመዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት የሞቱት ያለፈው ሰኔ ነበር። የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት የሉንጉ አስክሬን ወደ ዛምቢያ እንዲወሰድ ከወሰነ በኋላ ቤተሰቦቻቸው ማዘናቸውን ገልጸው ይግባኝ እንደሚሉም አስታውቀዋል።
የዛምቢያ መንግሥት በውሳኔው ደስተኛ መሆኑን ገልጿል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት "አገራችን ነው መሆን ያለባቸው" ብሏል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንትና ተከታያቸው ሀካኒዴ ሂቺልማ መካከል ያለው አለመግባባት ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞት በኋላም ቀጥሏል።
በቀብራቸው ላይ ተከታያቸው ሀካኒዴ ሂቺልማ እንዲገኙ እንደማይፈልጉ የዛምቢያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ መናገራቸውን ቤተሰባቸው ገልጿል።
ውሳኔውን ያሳለፉት ዳኛ አውብሪ ሌውባ "የዛምቢያ መንግሥት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት አስክሬን የመውሰድ መብት አለው" ብለዋል።
ቤተሰቡ አስክሬኑን ለዛምቢያ መንግሥት እንዲያስረክብም ወስነዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት በ68 ዓመታቸው ምንነቱ ባልተገለጸ ሕመም ምክንያት ከሞቱ በኋላ ቤተሰቦቻቸው የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በግላቸው ለማስፈጸም ወስነዋል። የዛምቢያ መንግሥት ግን አስክሬኑ እንዲሰጠው ሲጠይቅ ቆይቷል።
የዛምቢያ መንግሥት ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማከናወን ከቤተሰቡ ጋር ቢስማማም ቀብሩ ምን መምሰል አለበት በሚለው ላይ መስማማት ስላልቻሉ ሥነ ሥርዓቱ በደቡብ አፍሪካ እንዲከወን ቤተሰቡ ወስኗል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት እህት ብሬታ ሉንጉ በፍርድ ቤት ሲያለቅሱ ታይተዋል።
የዛምቢያ አቃቤ ሕግ ሙሊሎ ዲ ካምባሻ ውሳኔው ለዛምቢያ መንግሥት ድል ነው ባይባልም "ትክክለኛ ፍርድ ነው" ብለዋል።
"የአገሪቱ አባት ነው። ስለዚህ በቤተሰቦቹ ብቻ የተገደበ አይደለም" ሲሉም አክለዋል።
ቤተሰባቸው ይግባኝ ማለት ቢችልም ውሳኔው ግን "ትክክለኛ" መሆኑን ጠቅሰዋል።
ቤተሰቡ ይግባኝ እስከሚሉ ድረስ አስክሬናቸው በደቡብ አፍሪካ እንደተቀበረ ይቆያል።
ያለ ፈቃድ አስክሬናቸውን ለመውሰድ የተደረጉ ሙከራዎችን ለመከላከል አስክሬኑ ጥበቃ እየተደረገለት ነው።
እአአ ከ2015 እስከ 2021 ዛምቢያን የመሩት ሉንጉ በምክትላቸው የተተኩት በሰፊ የድምጽ ልዩነት ነበር።
ከሽንፈታቸው በኋላ ከፖለቲካ ተገልለው ቢቆዩም ኋላ ላይ ወደ ፖለቲካ ተመልሰዋል።















