“በአምላክ እና በመንግሥት እጅ ላይ ወድቀናል...” የትግራይ አርሶ አደሮች

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,

በትግራይ ሲካሄድ የነበረው ጦርነት ካበቃ ከአንድ ዓመት በኋላ በክልሉ በርካታ ቦታዎች ላይ ባጋጠመ ድርቅ እና የእርዳታ አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት የነዋሪዎች ሕይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን አርሶ አደሮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በክልሉ እንዲሁም በአገሪቱ ለተረጂዎች የሚቀርብ የምግብ እርዳታ ላይ መጠነ ሰፊ ዝርፊያ ተፈጽሟል በመባሉ የረድኤት ድርጅቶች የእርዳታ ሥራቸውን ለወራት አቋርጠው ቆይተዋል።

በዚህም ውሳኔ ምክንያት በትግራይ የሚገኙት የእርዳታ አቅርቦት መጋዝኖች በእርዳታ እህል ተሞልተው እያለ ነዋሪዎች ግን በረሃብ እየሞቱ መሆኑን የክልሉ ባለሥልጣናት ይናገራሉ።

ቢቢሲ በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን የሚገኘው የአጽበደራ ወረዳ ተገኝቶ የአርሶ አደሮቹ ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቷል።