ማንቸስተር ሲቲ ከቶተንሃም እና ሊቨርፑል ከኒውካስል፡ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ኢሳቅ እና ሞ ሳላህ

ሁለተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አርብ፣ ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ።

በሳምንቱ ተጠባቂ የሆኑት ጨዋታዎች ቅዳሜ እና ሰኞ እንዲከናወኑ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል።

ቅዳሜ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ቶተንሃምን የሚያስተናግድ ሲሆን ሰኞ ደግሞ ሊቨርፑል ወደ ኒውካስል ያቀናል።

የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ጨዋታዎቹን እንደሚከተለው ገምቷል።

አርብ

ቼልሲ ከ ዌስት ሃም

ዌስት ሃም በመጀመሪያው ሳምንት ጨዋታ በአዲስ መጪው ሰንደርላንድ ተሸንፏል።

ቼልሲ በመጀመሪያው ሳምንት ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየት ተስኖት ታይቷል።

አጥቂዎቹ ጆአኦ ፔድሮ እና ኮል ፓልመር ጥሩ ምሽት አላሳለፉም።

በዚህ ጨዋታ ቼልሲ አሸንፎ ሦስቱን ነጥብ ያሳካል።

ግምት፡ 0 - 2

ማንቸስትር ሲቲ ከ ቶተንሃም
ቅዳሜ

ማንቸስትር ሲቲ ከ ቶተንሃም

ማንቸስተር ሲቲ በተለይም አማካዩ ቲጃኒ ሬይንደርስ ባለፈው ሳምንት ድንቅ ነበር።

ቶተንሃም ካለፈው ዓመት አንጻር ተሻለ እንደሚሆን እገምታለሁ።

ቡድኑ ክሪስቲያን ሮሜሮን ውል ቢያራዝምም አስገራሚ በሆነ ሂደት ኤበሪቺ አዜን በአርሰናል ተነጥቋል።

ቶተንሃም እንደ ሲቲ ካሉ ቡድኖች ጋር ለመፎካከር ተጨማሪ ተጫዋቾችን ማስፈረም ይጠበቅበታል።

ግምት፡ 2 - 1

በርንመዝ ከ ዎልቭስ

በርንመዝ በመጀመሪያው ሳምንት ሽንፈትን ቢያስተናግድም ከሊቨርፑል ጋር አጥቅቶ ለመጫወት መሞከሩ የሚደነቅ ነው።

ቡድኑ በክረምቱ የለቀቁትን ሦስት ተከላካዮች በመተካቱ ላይ ጥያቄ ይነሳል።

ዎልቭስም ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ዕድሎችን አግኝቶ ነበር።

ውጤቱን ለመገመት የሚከብድ ጨዋታ ቢሆንም ባለሜዳው በጠባብ ውጤት ያሸንፋል።

ግምት፡ 1 - 0

ብሬንትፎርድ ከ አስቶን ቪላ

ብሬንትፎርድ በመጀመሪያው ሳምንት ጥሩ አልተንቀሳቀሰም።

ቡድኑ የብሪያን ምቡሞን አገልግሎት ከማጣቱም በላይ ዮአን ዊሳም የመልቀቅ ፍላጎት ስላለው የቡድኑ ነገር አሳሳቢ ነው።

ቡድኑ አሸንፎ በራስ መተማመኑን ማሳደግ ያስፈልገዋል።

ቪላ በበኩሉ ጥሩ ሳይንቀሳቀስ ከኒውካስል ጋር አቻ የተለያ ቢሆንም በዚህ ጨዋታ ግምቴ ለቪላ ይሆናል።

ግምት፡ 1 - 2

በርንሌይ ከ ሰንደርላንድ

ሰንደርላንድን ከግምቴ ውጭ በሆነ መልኩ በመጀመሪያው ሳምንት ድንቅ ውጤት አስመዝግቦ አስደንቆኛል።

ኤሊይዘር ማዬንዳ እና ዳን ባላርድ ድንቅ ሆነው አምሽተዋል።

ብርንሌይ በበኩሉ ከቶተንሃም ጋር ዕድሎችን ቢያገኝም አልተጠቀመበትም።

ጨዋታው በአቻ ውጤት እንደሚጠናቀቅ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 1

አርሰናል ከ ሊድስ

አርሰናል ከ ሊድስ

አርሰናል ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ጥሩ ባይሆንም ሦስቱን ነጥቦች ማሳካት ችሏል።

አሁንም ትልቅ መነጋገሪያ ርዕስ የሚሆነው ቪክቶር ግዮኮሬስ ኳስና መረብን ያገናኛል ወይ የሚለው ጉዳይ ነው።

ሊድስ ከኤቨርተን ጋር ጥሩ ቢጫወትም ያገኘው ፍጹም ቅጣት ምት ግን ትንሽ አግባብ አይመስልም።

ቡድኑ ተመሳሳይ አጨዋወትን ኤምሬትስ ላይ ይደግም ይሆን?

ግምት፡ 4 - 0

እሑድ

ክሪስታል ፓላስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ፓላስ ባለፈው ሳምንት ቼልሲን ማሸነፍ ነበረበት። አጨዋወቱም ማራኪ ነበር።

የቡድኑ ደካማ ጎን የቡድኑ ትልቀት መሳሳት ነው። እንዴት አድርገው ኤዜን ይተኩታል?

ኤዜን እና ማርክ ጉሄን የመተካት ትልቅ ፈተና ከፊታቸው ተደቅኗል።

ይህም ተመጣጣኝ ፉክክር የሚታይበት ጨዋታ ይሆናል።

ግምት፡ 1- 1

ኤቨርተን ከ ብራይተን

ኤቨርተን ባለፈው ዓመት ከሚገባው በላይ ውጤት አግኝቷል። አሁን ያሉበት ቦታ ትክክለኛው ነው ብዬ አላሰብም።

ከሊድስ ጋርም ጥሩ አልተፎካከሩም።

በዚህ ጨዋታ ብራይተን የበላይ የሚሆን ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 - 2

ፉልሃም ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት ቢሸነፍም የባለፈው ዓመት አይነት መጥፎ ጊዜን ያሳልፋሉ ብዬ አልገምትም።

ብሪያን ምቡሞ እና ማቲያስ ኩኛ በማጥቃቱ ላይ ጥሩ ተንቀሳቅሰዋል።

ፉልሃም ባለፈው ሳምንት አንድ ነጥብ ማግኘቱ ዕድለኛ ቢያስብለውም በሜዳው ጥሩ እንደሚንቀሳቀስ እገምታለሁ።

ፉልሃም በማጥቃት ለመጫወት ስለሚሞክር ለዩናይትድ የሚመቸው ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 - 1

ኒውካስል ከ ሊቨርፑል
ሰኞ

ኒውካስል ከ ሊቨርፑል

ይህ ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክ የሚደረግበት ቢሆንም ትኩረቱ ግን በአሌክሳንደር ኢሳቅ የዝውውር ጉዳይ ላይ ይሆናል።

ኒውካስል አጥቂ አላገኘም። ቡድኑ ከቪላ ጋር ጥሩ ቢንቀሳቀስም የኢሳቅ ቦታ አልተሸፈነም።

ሊቨርፑል ደግሞ በተከላካይ መስር ላይ ባለው ክፍተት ምክንያት ሁለት ጎሎችን አስተናግዷል።

ኒውካስል ሁጎ ኤኪቲኬን ቢያስፈርም ኖሮ ኢሳቅ በቀያዮቹ ማሊያ ኒውካስልን የሚገጥምበት ጨዋታ ይሆን ነበር።

ጎሎች የሚቆጠሩበት ጨዋታ እንደሚሆን እና ኒውካስል አጥቂ ስለሌለው በሊቨርፑል የበላይነት እንደሚጠናቀቅ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 2