በኤምሬትሱ ፍልሚያ አርሰናሎች እንደሚያሸንፉ ሰፊ ግምት ተሰጥቷል፤ ይስማማሉ?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
አራተኛው የፕሪሚየር ሊግ ሳምንት መሰናዶ መድፈኞቹን ከቀያይ ሴጣኖቹ ያገናኛል።
አርሰናልም ሆነ ዩናይትድ የውድድር ዘመኑን ገና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ አልጀመሩም።
የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን መድፈኞቹ ቀያይ ሴጣኞቹን አሸንፈው የውድድር ዘመናቸውን በሞቅታ የሚጀምሩበት ጨዋታ ሊሆን ይችላል ይላል።
በጉጉት የሚጠብቀው ጨዋታ ፍጻሜው ምን ይሆናል?

ዓርብ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሉቶን ከ ዌስት ሃም
ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሉቶን ከ ዌስት ሃም ይገናኛሉ።
ሉቶን በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየቱ ነገር ቀላል እንደማይሆን ቀድሜ አውቄው ነበር። ውድድሩን በጥሩ ሁኔታ አልጀመሩም። ዌስት ሃም ቀላል ተጋጣሚ ባይሆንም ሉቶን በሜዳቸው የሚያደርጉት የመጀመሪያው ጨዋታቸው እንደመሆኑ የተቻላቸውን ያደርጋሉ።
በአንጻሩ ዌስት ሃም በአስደናቂ ሁኔታ 22 በመቶ ብቻ ኳስ ተቆጣጥረው ሳይገመት ብራይትንን አሸንፈዋል። ዌስት ሃም ፈተና ቢጠብቀውም ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ ሉቶን 0 - 2 ዌስት ሃም

ቅዳሜ
ሼፊልድ ዩናይትድ እና ኤቨርተን
ቅዳሜ በምሳ ሰዓት ጨዋታ ሼፊልድ እና ኤቨርተን ይገናኛሉ።
ኤቨርተን የግድ ተሻሽሎ መቅረብ አለበት። እስካሁን ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ግብ ያላስቆጠረው የሊቨርፑል ከተማ የግድ አጥቂ ያስፈልገዋል።
ኤቨርተን እስካሁን ባያሸንፍም ዘንድሮ ወደ ሊጉ የመጣው ሼፊልድ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ ሼፊልድ 0 – 1 ኤቨርተን

ብሬንትፎርድ ከ ቦርንመዝ
ቅዳሜ 11 ሰዓት ሲል ከሚደረጉ አራት ጨዋታዎች መካከል አንዱ ብሬንትፎርድ ከ ቦርንመዝ የሚያደርጉት አንዱ ነው።
ቦርንመዝ እያሳየ ያለው አቋም አሳማኝ አይደለም። ከሦስት ጨዋታ 1 ነጥብ ብቻ ነው የሰበሰበው።
በአንጻሩ ደግሞ ብሬንትፎርድ በሜዳው የማይቀመስ ሆኗል። ዊሳ እና ምቦሞ በቅጣት የማይሰለፈውን አይቫን ቶኒ ጥሩ አድርገው ተክተው እየተጫወቱ ነው።
ግምት፡ ብሬንትፎርድ 2 - 0 ቦርንመዝ

በርንሌይ ከ ቶተነሃም
በርንሌይ በኢኤፍኤል ዋንጫ ፎረስትን ማሸነፍ ችሏል። በርንሌይ ድንቅ የኳስ ጥበብ እያሳየ ቢሆንም በመጀመሪያው ሁለት ጨዋታ በሲቲ እና ቪላ ተሸንፏል።
ምንም እንኳ የኮምፓኒ ቡድን ጥሩ ቢሆንም ከቶተነሃም ነጥብ ያገኛል ብዬ አልጠብቅም።
ግምት፡ በርንሌይ 1 - 2 ቶተነሃም

ቼልሲ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት
በባለፈው የውድድር ዓመት ፎረስት ከሜዳ ውጪ እጅግ ደካማ የሚባል ሪኮርድ ነበረው። ይህ በቼልሲ ሜዳ የሚቀጥል ይመስለኛል።
ራሂም ስተርሊንግ ጎል ወደ ማስቆጠር ተመልሷል። በራስ መተማማን ይታይበታል። ይህ ለቼልሲ መልካም ነገር ነው።
ግምት፡ ቼልሲ 2 - 0 ፎረስት

ማንቸስተር ሲቲ ከ ፉልሃም
ሲቲ ይህን ጨዋታ ያሸንፋሉ ብቻ ሳይሆን በሰፊ የግብ ልዩነት ይረታሉ የሚል ግምት አለኝ።
ፉልሃም በኤምሬትስ ነጥብ ቢጋራም በኢትሃድ ግን ጎል እንኳ ያስቆጥራል ብዬ አልጠብቅም።
ግምት፡ ሲቲ 4 - 0 ፉልሃም

ብራይተን ከ ኒውካስል
ይህ ጨዋታ ቅዳሜ ከምሽቱ 1፡30 ሲል ይጀምራል። ይህ ግጥሚያ አስደናቂ ጨዋታ ያሳየናል።
ኒውካስል ከሊቨርፑል በነበረው ጨዋታ ሙሉ ነጥብ እንደሚወስድ እርግጥ ይመስል ነበር። የኋላ የኋላ በቀይ ካርድ አምበሉን ያጣው፤ ከሜዳው ውጪ 1 ለ 0 ሲመራ የነበረው ሊቨርፑል ድል አድርጓል።
ይህ ለኒውካስል ትልቅ ቁጭት ነው።
ብራይተን በተመሳሳይ ያሸንፋሉ ተብሎ በተገመተ ጨዋታ በደጋፊው ፊት በዌስት ሃም ተሸንፏል።
ይህን ጨዋታ ውጤት መገመት ከባድ ስለሆነ አቻ ይጠናቀቃል ብዬ እገምታለሁ።
ግምት፡ ብራይተን 1 - 1 ኒውካስል

እሁድ
ፓላስ ከ ዎልቭስ
ክርስታል ፓላስ እሁድ 4 ሰዓት ላይ ከዎልቭስ ይገናኛል።
ፓላስ በሮይ ሆድሰን እየተመራ ጥሩ እየተፎካከረ ይገኛል።
ዎልቭስም ቢሆን አማካዩን ማቲያስ ኑኔስ ለሲቲ አሳልፎ ቢሰጥም ጥሩ የተደራጀ ቡድን እንደሆነ ይሰማኛል።
ግምት፡ ፓላስ1 - 1 ዎልቭስ

ሊቨርፑል ከ አስተን ቪላ
ይህ ማራኪ ጨዋታ እንደሚሆን እገምታለሁ። ኡናይ ኤምሪ ቡድኑን ደህና አድርገው አደራጅተዋል። በመጀመሪያው ጨዋታቸው በኒውካስል ከባድ ሽንፈትን ቢከናነቡም ቀጥሎ ያደረጓቸውን ሁለት ጨዋታዎች አሸንፈዋል።
ይሁን እንጂ ባለፈው ሳምንት በኒውካስል ሜዳ ተዓምር ያሳዩን ባለሜዳዎቹ ያሸንፋሉ የሚል ግምት አለኝ።
ግምት፡ ሊቨርፑል 2 - 1 አስተን ቪላ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
አርሰናል ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
ሁለቱም ክለቦች የውድድር ዘመኑን በጥሩ ሁኔታ አልጀመሩም። አርሰናል ከሦስት ጨዋታ 7 ነጥብ ሰብስቧል። ዩናይትድ ደግሞ ከ9 ነጥብ 6 ነው ማግኘት የቻለው።
መድፈኞቹ ተቀናቃኛቸውን በሜዳቸው የሚያስተናግዱበት ጨዋታ እንደመሆኑ ምናልባት ይህ ጨዋታ የውድድር ዘመኑን በመነቃቃት የሚጀምሩበት ሊሆን ይችላል።
አርሰናል ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ ብገምትም ጨዋታው ቀላል እንደማይሆን ግን አምናለሁ።
ግምት፡ አርሰናል 2 - 1 ዩናይትድ















