ተጫዋቾቹ በመሰደዳቸው የከሰመው ባለ 100 ዓመት ዕድሜው የእግር ኳስ ቡድን

ቱኒዚያ ውስጥ በምዕራብ ቱኒዚ የሚገኘው የእግር ኳስ ቡድን በመቶ ዓመት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስፖርቱ ውጪ ሆኗል።

ባለፉት ሦሰት ዓመታት ይህ እግር ኳስ ቡድኑ የሚገኝባት ጋርዲማኦ ከተማ፣ ለሕገ ወጥ ስደት መነሻ ሆና ቆይታለች።

ይህ ስደት ግን ለእግር ኳስ ተጫዋቾችም ምርጫቸው ሆኗል። በዚህም ምክንያት 32 ዋና ተሰላፊ ተጫዋቾቹ በመሰደዳቸው ቡድኑ ለመፍረስ ተገዷል።