ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን 'አምባገነን' ማለታቸው ቅሬታን ፈጠረ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን "አምባገነን" ብለው መጥራታቸው የሁለቱን መሪዎች መቃቃር ይበልጥ አባብሶታል።
ትራምፕ ይህንን ያሉት ዜሌንስኪ ኪየቭ የተገለለችበት እና በሳዑዲ አረቢያ ለተደረገው በአሜሪካ እና ሩሲያ ንግግር በሰጡት ምላሽ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በሚተዳደረው በሞስኮ "የሐሰት መረጃ ላይ ነው" በማለት ከወቀሱ በኋላ ነው።
ፍሎሪዳ ውስጥ በሳዑዲ በሚደገፈው የኢንቨስትመንት ስብሰባ ላይ ትራምፕ እንደተናገሩት ዜሌንስኪ "በጣም ጥሩ የነበሩበት ብቸኛው ነገር ጆ ባይደንን በከንቱ ማታለል ላይ ነው" ብለዋል።
"አምባገነኑ" የሚለውን ዘለፋ ተከትሎ የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝን ጨምሮ የአውሮፓ መሪዎች "ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪን ዲሞክራሲያዊ ቅቡልነታቸውን መካድ ስህተት እና አደገኛ ነው" ሲሉ ተችተዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታመር ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ጋር በስልክ ባደረጉት ንግግር ዜሌስኪን እንደሚደግፉ ግልፅ አድርገዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ቃል አቀባይ ሰር ኪር "ለፕሬዚዳንት ዘለንስኪ የዩክሬን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መሪ መሆናቸውን ድጋፋቸውን ገልጸዋል" ብለዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም "በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት እንግሊዝ እንዳደረገችው በጦርነት ጊዜ ምርጫን ማራዘም ምክንያታዊ ነበር" ብለዋል ።
የዘለንስኪ የአምስት ዓመት የስልጣን ዘመን እ.አ.አ በግንቦት 2024 ማብቃት ነበረበት። ሆኖም ሩሲያ በየካቲት 2022 ሙሉ ወረራዋን ከጀመረች በኋላ ዩክሬን በወታደራዊ አስተዳደር እየተዳደረች ትገኛለች።
የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ኡልፍ ክሪስተርሰን በተመሳሳይ የትራምፕን "አምባገነን" የሚለውን ዘለፋ ሲተቹ የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ሌናሌና ቤርቦክ አስተያየቶቹን "ትርጉም አልባ" ሲሉ ጠርተዋቸዋል።
"ትዊት ከማድረግ ይልቅ እውነተኛውን ዓለም ስንመለከት ከሆነ በአውሮፓ ውስጥ ማን በአምባገነንነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ይታወቃል። ሩሲያ ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ ቤላሩስ ውስጥ ያሉ ሰዎች" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ለዜድዲኤፍ ብሮድካስት ተናግረዋል።
ትራምፕ 'በትሩዝ ሶሻል' ልጥፍ ላይ ተመሳሳይ ቃል ከተጠቀሙ ጥቂት ሰዓታት በኋላ በፍሎሪዳ ሲናገሩ ዜለንስኪን "አምባገነን" ሲሉ ጠርተዋቸዋል።
"ምርጫ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም። በዩክሬን ብዙም አይፈለገም። እያንዳንዱ ከተማ እየፈረሰ እንዴት ከፍ ሊል ይችላል?" ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።
የዘለንስኪን መንግሥት "ስምምነቱን አፍርሷል" ሲሉ በመክሰስ ከዩክሬን የከበሩ ማዕድናት ለማግኘቱ ያደረጉትንም ሙከራ ጠቅሰዋል።
ትራምፕ ዘለንስኪ "መጥፎ ሥራ ሠርቷል፣ አገሩ ፈርሳለች፣ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ያለምክንያት ሞተዋል" ሲሉ "የትሩዝ ሶሻል" ልጥፋቸውን አስተጋብተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ "ጦርነቱን በተሳካ ሁኔታ ለማቆም ከሩሲያ ጋር ድርድር እያደረገች ነው" ብለዋል።
የዋይት ሀውስ ባለስልጣን የትራምፕ ልጥፍ ለዘለንስኪ ለሰጡት የ"ሃሰት መረጃ" አስተያየቶች ቀጥተኛ ምላሽ ነው ብለዋል።
ማክሰኞ የአሜሪካ እና የሩሲያ ባለስልጣናት ከሩሲያ የዩክሬን ወረራ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ፊት ለፊት ተገናኝተው ንግግሮችን አድርገዋል።
የዩክሬን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አርሴኒ ያሴንዩክ የትራምፕን አስተያየት ተከትሎ ሩስያ "አሁን ፈንጠዝያ ላይ ነች" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"ቮልዲሚር ዘለንስኪ ሕጋዊ ፕሬዚዳንት ናቸው" ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር "በወታደራዊ ሕግ ስር ምርጫ ማካሄድ አንችልም" ብለዋል።
የቃላት እንካ ሰላንትያው የተጀመረው ትራምፕ ማክሰ በፍሎሪዳ ማር-አ-ላጎ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዩክሬንን ለጦርነቱ ተጠያቂ የሚያደርግ አስተያየት በሰጡበት ወቅት ነው።
ትራምፕ ክህደት ሊሰማቸው ለሚችል ዩክሬናውያን የሚያስተላልፉት መልእክት ምን እንደሆነ በቢቢሲ ኒውስ ተጠይቀው ሲመልሱ "እፎይታ ባለመኖሩ እንደተናደዱ ሰምቻለሁ፣ እንግዲህ ከዚያ በፊት ለሦስት ዓመታት እና ለረጅም ጊዜ እፎይታ ነበራቸው። ይህ በቀላሉ ሊፈታ ይችል ነበር" ብለዋል
ትራምፕ "በፍፁም [ጦርነቱ] መጀመር አልነበረበትም። ስምምነት ማድረግ ይቻል ነበር። ሲሉ አክለዋል
ትራምፕ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በየካቲት 2022 ዩክሬንን ለመውረር መወሰናቸውን አልገለፁም።
ረቡዕ እለት ዘለንስኪ በኪዬቭ ለጋዜጠኞች "ብዙ የተዛቡ መረጃዎች እያየን ነው እናም ከሩሲያ እየመጣ ነው ። ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደ መሪ ያለኝ አክብሮት እንተጠበቀ ሆኖ ... በዚህ የተሳሳተ መረጃ ውስጥ እየኖረ ነው" ሲሉ ተናግረዋል
አክለውም "ዩናይትድ ስቴትስ ፑቲንን ከዓመታት መገለል እንዲወጡ ረድታዋለች" ብለው እንደሚያምኑ ተናግረል።
ዓለም "ከፑቲን ጋር ወይም ከሰላም ጋር" የመሆን ምርጫ ገጥሞታል ያሉት የዩክሬኑ መሪ ሐሙስ በዩክሬን የዋሽንግተን መልዕክተኛ ኪት ኬሎግ ጋር እንደሚገናኙ አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል ዘለንስኪ የትራምፕ የዩክሬንን የከበሩ ማዕድናት ለማግኘት ያደረጉትን ሙከራ ምንም አይነት የደህንነት ዋስትና አልሰጡም በማለት ውድቅ አድርገውታል።
ትራምፕ የዩክሬን ፕሬዚደንት 4% ተቀባይነት ብቻ ነው ያላቸው በማለት ከዘለንስኪ ተወዳጅነት ውጭ የሆነ ጉዳይ ለመፍጠር ሞክረዋል። ነገር ግን በዚህ ወር በተሰበሰበው የህዝብ አስተያየት 57% ዩክሬናውያን በፕሬዚዳንቱ እንደሚተማመኑ መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በረቡዕ የትሩዝ ሶሻል ልጥፋቸው ትራምፕ በዩክሬን ያለው ጦርነት "ከእኛ ይልቅ ለአውሮፓ በጣም አስፈላጊ ነው" ተናግረዋል።
"የሚለየን ትልቅና የሚያምር ውቅያኖስ አለን" ብለዋል
አውሮፓ በቀጠናው "ሰላም ማምጣት ተስኗት ነበር" ሲሉም አክለዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ከትራምፕ ጋር ለመገናኘት "ደስተኛ" መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጥል ተናግሯል።
አዲሱ ማዕቀብ የሩስያ አልሙኒየምን እና በህገ ወጥ መንገድ ዘይት በማጓጓዝ የተጠረጠሩ በደርዘን የሚቆጠሩ መርከቦች ላይ ያነጣጠረ ነው።
በተጨማሪም ብዙ የሩሲያ ባንኮችን ከዓለም አቀፉ የስዊፍት የክፍያ ሥርዓት ያቋርጣሉ እና ተጨማሪ የሩሲያ ሚዲያዎችን በአውሮፓ እንዳይሰራጭ ይከለክላሉ።












