የሕንድ ፖሊስ 27 ሰዎችን ጭኖ በፍጥነት ሲሄድ የነበረን ‘ባጃጅ’ ያዘ

ሰዎች ከባጃጅ ሲወርዱ

የፎቶው ባለመብት, PIYUSH RAI/TWITTER

እናንተ ባላችሁበት አካባቢ አንድ ባጃጅ 'ጥቅጥቅ' አድርጎ ሲጭን ስንት ሰዎችን ያሳፍራል? ስድስት፣ ስምንት ወይስ አስር? ከአስር በላይ ሊይዝ ይችላል ብላችሁ አስባችሁ ታውቃለችሁ?

የባጃጅ አምራች በሆነችው ሕንድ ውስጥ ግን የተከሰተው በተሽከርካሪው ታሪክ ክብረ ወሰን የሚሆኑ ተሳፋሪዎች ታጭቀው በፖሊስ ተይዘዋል ተብሏል።

የሕንድ ፖሊስ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረን ባለ ሦስት ጎማ ተሸከርካሪ [ባጃጅ] አስቁሞ ባደረገው ፍተሻ በውስጡ 27 ሰዎች ተጭነው አገኘ።

በተለምዶ ባጃጅ ተብሎ ከሚጠራው ባለሦስት ጎማ ተሸከርካሪ ውስጥ 27 ሰዎች ሲወርዱ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ብዙዎችን አጀብ አስብሏል።

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጨው ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል፤ የፖሊስ አባላት ከባጃጁ የሚወርዱ ሰዎችን ሲቆጥሩ ያሳያል።

በባጃጁ ውስጥ ተሳፍረው ከተገኙት 27 ሰዎች መካከል ጥቂት የማይባሉ ሕጻናት እና አዛውንቶች ይገኙበታል።

አብዛኛውን ጊዜ ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች ሶስት ሰዎችን ብቻ እንዲጭኑ የሚሰሩ ቢሆንም አንዳንድ ማሻሻያዎች እየተደረገላቸው እስከ 6 ሰዎች የሚጭኑበት አጋጣሚዎች አሉ።

በሕንዷ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ግን 27 ሰዎች የጫነ ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ በፍጥነት ሲጓዝ ነበር መባሉ ብዙ አግራሞትን ፈጥሯል።

የ X ይዘትን ይለፉት, 1
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

የ X ይዘት መጨረሻ, 1

የሕንድ የመገናኛ ብዙኃን ሪፖርቶች እንደጠቆሙት ፖሊስ በፍጥነት ሲጓዝ ስለነበረው ባጃጅ ጥቆማ ከደረሰው በኋላ፤ ተሸከርካሪውን ለማስቆም ሲሞክር አሸከርካሪው በፍጥነት አሸከርክሮ ለማምለጥ ሞክሮ ነበር ተብሏል።

ፖሊስ ባለ ሦስት ጎማ ተሸከርካሪውን ተከታትሎ በኃይል እንዲቆም ካደረገ በኋላ፤ “ከሁለት ደርዘን በላይ ሰዎች ሲወርዱ ማየቱ ከፍተኛ ድንጋጤን እንደፈጠረ” የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ ራጄሽ ኩማራ ለታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ተናግረዋል።

ባለ ሦስት ጎማው ተሸከርካሪ ከፍጥነት በላይ በመጓዝ እና ትርፍ በመጫን ተይዟል።

ከባጃጁ 27 ሰዎች ሲርዱ የሚያሳየው ምስል በርካቶች የተመለከቱት ሲሆን፤ ብዙዎች ክስተቱን ተከትሎ ፈገግታ የሚያጭሩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት, 2
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

የ X ይዘት መጨረሻ, 2

አንዳንዶች ይህ “የዓለም ክብረ ወሰን” ተብሎ መመዝገብ አለበት ሲሉ ሌሎች ደግሞ ክስተቱ በሕንድ የሕዝብ ትራንስፖርት እጥረት መኖሩን ያሳያል ብለዋል።

ባለ ሦስት ጎማው ተሽከርካሪ 27 ሰዎች ጭኖ በፍጥነት ሲጓዠ ነበር መባሉን ተከትሎ የተሸከርካሪው አምራች መደነቅ ይገባዋል ያሉም አልጠፉም።

በሕንድ በርካቶች ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪዎችን እንደ ዋነኛ የትራንስፖርት አማራጭ ይጠቀማሉ።