ፑቲን የዩክሬንን 'አላስፈላጊ ጦርነት' ካላቆሙ አዲስ ማዕቀብ እንደሚጠብቃቸው ትራምፕ ገለጹ

ትራምፕ እና ፑቲን እአአ በ2017

የፎቶው ባለመብት, EPA

ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬንን ጦርነት ማስቆም ካልቻሉ በሩስያ ላይ ከፍተኛ ታሪፍ እና ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጥሉ ዶናልድ ትራምፕ አስጠንቀቁ።

ጦርነቱን አንዲቋጭ በማድረግ ለሩሲያና ለፕሬዚዳንቱን "በጣም ትልቅ ጥቅም" እያስገኙ መሆናቸውን ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው አስፍረዋል።

ትራምፕ እአአ በየካቲት 2022 የተከፈተው የሩስያ ወረራ በአንድ ቀን ውስጥ እልባት እንደሚያገኙለት ቀደም ሲል ተናግረው ነበር።

ሩሲያ በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም። ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሰሞኑ ሞስኮ ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ለመነጋገር ያላት ዕድል አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ፑቲን ለመጀመሪያ ጊዜ በ2014 የተጀመረውን ጦርነት ለማስቆም ለመደራደር መዘጋጀታቸውን ደጋግሞ ተናግረዋል። ይህ የሚሆነው ግን 20 በመቶ የሚሆነውን መሬቷን በሩሲያ የተነጠቀችው ዩክሬን ግዛቷን የመነጠቁን እውነታ መቀበል ስትችል ነው ሲሉ ተናግረዋል። ዩክሬን ኔቶን እንድትቀላቀልም ፍቃደኛ አይደሉም።

ኪየቭ ግዛቷን አሳልፋ መስጠት አትፈልግም። ምንም እንኳን ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በቅርብ የተያዙትን አንዳንድ ቦታዎች በጊዜያዊነት አሳልፈው መስጠትን እንዳለባቸው ግን አምነዋል።

ትራምፕ ማክሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከፑቲን ጋር በቅርቡ እንደሚነጋገሩ ተናግረዋል። የሩሲያው መሪ ወደ ክብ ጠረጴዛ ካልመጡ ተጨማሪ ማዕቀቦችን "ሊመለሱ" እንደሚችሉ አክለዋል።

ረቡዕ ዕለት በትሩዝ ሶሻል ላይ "ኢኮኖሚዋ እየከሰመ ላለውን ሩስያን እና ለፕሬዝዳንት ፑቲንን በጣም ትልቅ ጥቅም አውልላቸዋልሁ" ሲሉ ጽፈዋል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

"አሁን ተረጋጉ እና ይህንን አስቂኝ ጦርነት አቁሙት! [ካልሆነ] እየተበለሻሸ ይሄዳል። 'ውል' የማይታሰር ከሆነ በሩስያ እና በሌሎች ተሳታፊ አገራት ላይ በቅርቡ በማንኛውም ምርቶች ላይ ከፍተኛ ግብሮችን፣ ታሪፎችን እና ማዕቀቦችን ከመጣል ሌላ ምርጫ የለኝም።"

"እኔ ፕሬዚዳንት ብሆን ፈጽሞ የማይጀመረውን ጦርነት እናስወግደው! በቀላል ወይም በከባድ መንገድ ይህን ማድረግ እንችላለን። ቀላሉ መንገድ ሁልጊዜ የተሻለ ነው። ከስምመነት ለመድረስ ጊዜው አሁን ነው" ሲሉ አክለዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩስያ ምክትል አምባሳደር ዲሚትሪ ፖሊያንስኪ ቀደም ሲል ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አገራቸው ወደ ፊት ከመራመዷ በፊት ክሬምሊን ጦርነቱን ለማቆም በሚደረገው ስምምነት ትራምፕ ምን እንደሚፈልጉ ማወቅ ትፈልጋለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ማክሰኞ ዕለት ለዓለም የኢኮኖሚክ ፎረም እንደተናገሩት በየትኛውም ስምምነትወ ውስጥ ቢያንስ 200 ሺህ የሠላም አስከባሪ ኃይል መካተት አለበት።

ማንኛውም በአገራቸው የሚሠማራ የሠላም አስከባሪ ኃይል ለሩሲያ ተጨባጭ የሆነ እንቅፋትን መፍጠር እንዲችል የአሜሪካ ወታደሮችን ማካተት እንዳለበት ለብሉምበርግ ተናግረዋል።

"ከዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ሊሆን አይችልም ... አንዳንድ የአውሮፓ ወዳጆቻችን ሊሆን ይችላል ብለው ቢያስቡም ግን አይሆንም" ብለዋል። ከዩናይትድ ስቴትስ ሌላ ማንም አገር እንዲህ ያለውን እርምጃ መወሰድ አይችልም ብለዋል።

ፑቲን ጠንከር ያለ ነገር ብቻ እገባቸዋል ሲሉ የቆዩት የዩክሬን መሪዎች ይህን ጠንከር ያለ የትራምፕን ንግግር ሊያደንቁ ቢችሉም ኪየቭ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት መጀመሪያ የምትፈልገው ድርጊት እንጂ ቃል አይደለም።

ትራምፕ ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦች ምን ላይ ሊነጣጠሩ እንደሚችሉ እና መቼ እንደሚደረጉ አልገለፁም። ከ2022 ወዲህ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የሩሲያ ምርቶች ከማሽቆልቆላቸውም በላይ ሞስኮ ላይ ከባድ ማዕቀቦች ተጥለዋል።

በአሁኑ ጊዜ ሩሲያ ወደ አሜሪካ በዋነኝነት ምትልከው ፎስፌት ላይ የተመሰረቱ ማዳበሪያዎች እና ፕላቲኒየም ናቸው።

ዛፖሪዥያ አካባቢ የሚገኙ የዩክሬን ወታደሮች

የፎቶው ባለመብት, EPA

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የአብዛኛው የዩክሬናውያን ምላሽ ትችት አዘል ነበር። ብዙዎች ተጨማሪ ማዕቀቦች ለሩሲያ ጥቃት ደካማ ምላሽ እንደሆነ ጠቁመዋል። የብዙዎቹ ዋነኛ ጥያቄ ግን ፑቲን ከዩክሬን ጋር ለመወያየት ምን ዝግጁ ናቸው ነው የሚለው ነው።

በሞስኮ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ሩሲያውያን አንድ ጊዜ እስከ ደቡባዊ የዩክሬን የወደብ ከተማዋ ኦዴሳ ከታሰበው "ድል" ያነሰ እንዲቀበሉ ሞስኮ እያዘጋጀች መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶችን እያዩ ነው።

የቴሌቭዥን አዘጋጇ እና የፑቲን ደጋፊ የሆነችው ማርጋሪታ ሲሞንያን ጦርነቱን ለማስቆም "ተጨባጭ" ሁኔታዎች መኖራቸውን መናገር የጀመረች ሲሆን ይህም አሁን ባለበት የግዛት ይዞታ ጦርነቱን ማቆምን ሊያካትት እንደሚችል ጠቁማለች።

ይህም ማለት ፑቲን ከሁለት ዓመት በፊት በህገ ወጥ መንገድ የሩሲያ ግዛት ናቸው ብለው ከሰየሟቸው እንደ ዛፖሪዥያ ካሉ አራት የዩክሬን ክልሎች አሁን በከፊል በኪዬቭ ቁጥጥር ስር ይሆናሉ ማለት ነው።

‹የዜድ› ጦማሪያን የሚባሉት የሩሲያ የልብ ደጋፊዎች ግን በዚህ "ሽንፈት" ተቆጥተዋል።