ኮሮና ቫይረስ: በዓለም ላይ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ትንሳኤን እንዴት እያከበሩት ነው?

በጆርጂያ የትንሳኤ በአል አከባበር

የፎቶው ባለመብት, EPA

በዓለም ላይ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በአልን እያከበሩ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንቅስቃሴዎችም ሆኑ ሌሎች እግዶች ቢኖሩም፤ አበይት የሚባለውን የትንሳኤ በአልን ከማክበር አላገዳቸውም።

በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት፣ መካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም በአብዛኛዎቹ አፍሪካ አገራት ቫይረሱ ይዛመታል በሚል ፍራቻ ህዝቡ የቤተ ክርስትያን አገልግሎቶችን እንዳይታደም ተከልክሏል።

ነገር ግን የጆርጂያ እውነታ ሌላ ነው፣ አብያተ ክርስትያናቷን አልዘጋችም፤ ምዕመናኑም በቤተክርስቲያን ተገኝተዋል።

በጆርጂያ ብቻ አይደለም በእየሩሳሌምም ወና በሆኑ አብያተ ክርስቲያናት በትናንትናው ዕለት ባህላዊና እምነታዊ መሰረት ያለው 'ሆሊ ፋየር' የተሰኘው በአል ተከብሯል።

ቤተ ክርስቲያኑ የተዘጋው ባለፈው ወር ቢሆንም የተወሰኑ የኦርቶዶክስ ካህናት ጥቁር ጭምብል አጥልቀው በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ነበሩ።

የሆሊ ፋየር በአል አከባበር በእየሩሳሌም

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በእየሩሳሌም ከተለያየ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተውጣጡ ጳጳሳት በተገኙበት ጧፍ በማብራት የተከበረ ሲሆን፤ ጧፉም የእየሱስ ክርስቶስን መነሳት የሚያበስር ነው። የግሪኩ ፓርያርክ አባ ቴዎፍሎስ ሶስተኛ ጧፉን የለኮሱ ሲሆን እንደ ቀድሞው ጧፉን ለምእመናኑ አላቀበሉም።

በክብረ በአሉ ላይ ተገኝተው የነበሩት የአርመኑ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ፣ የሶሪያው ኤጲስ ቆጶስ እንዲሁም አራት ረዳቶች እንደነበሩ የእስራኤል ሚዲያ ዘግቧል።

የቤተ ክርስቲያኗ ደወል ሲደወል አቡነ ቴዎፍሎስ ሶስተኛ ጧፉን እያበሩ ቤሎሎቹ ታጅበው ቴል አቪቭ አካባቢ ወደሚገኘው ቤን ጉሪዮን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አምርተዋል። በመቀጠልም ወደ አስር አገራት እንደበረሩ ተዘግቧል።

በሌሎች አገራት ያሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንዴት አከበሩት?

ሩስያ፦ የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቀደመ ትውፊቷን ወደ ጎን በማለት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናኖቿ ሌሊት የሚደረገውን ቅዳሴም ሆነ ቡራኬ እንዳይካፈሉ ከልክላለች።

የቅዳሴው አገልግሎት የተፈፀመውም ካህናትና ዲያቆናት ብቻ በተገኙበት ነው።

በሩስያዋ መዲና ሞስኮ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን

የፎቶው ባለመብት, AFP

በዩክሬን አንድ የኦርቶዶክስ ካህን ምዕመናኑን ፀበል ሲረጩ

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በዩክሬን አንድ የኦርቶዶክስ ካህን ምዕመናኑን ፀበል ሲረጩ
የቅድስት ካቴድራል ቤተክርስቲያን

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በኢትዮጵያ ያሉ ምእመናን በቤተክርስቲያን ውስጥ አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ ተደርጓል።

በዩክሬን ዋና ከተማዋን ኪቭን ጨምሮ በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች በአብያተ ክርስቲያናት እንዳይሰባሰቡ ፖሊሶች ተሰማርተዋል።

በግሪክ ባለስልጣናት ሁኔታውን ለመቆጣጠር ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) እየተጠቀሙ ነው። ከከተሞች መውጣትም ሆነ መግባት ተከልክሏል። ብዙዎች ቤተሰብና ዘመድ ጥየቃ ሊወጡ ይችላሉ በሚልም ግሪክ በሺዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶችን አሰማርታለች።

ከእየሩሳሌም የተለኮሰው ጧፍ በአቴንስ አመሻሹ ላይ ሲደርስ ለሌሎች ቤተ ክርስቲያናት አልተሰጠም። ቀጥታ በአቴንስ ወደ ሚገኙት የእየሩሳሌም ፓትርያርክ ዘንድ ነው የተወሰደው።

ጧፉም ከአቴንስ በተጨማሪ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ባለው በፍልስጥኤሟ ቤተልሄም ከተማም ተወስዷል።

ግብፅ ኮፕቲክ ፓትያርክ ታዋድሮስ ሁለተኛ ስቅለትን በምስራቅ ካይሮ በምትገኝ ገዳም ውስጥ አሳልፈዋል፤ ምዕመናንም አልተገኙም ተብሏል። አገልግሎቱ በቴሌቪዥን የተላለፈ ሲሆን በዲያቆናቱና በቀሳውስቱ መካከል አካላዊ ርቀትም ታይቷል።

ሮማንያ ህዝቡ ከቤት እንዳይወጣ በመከልከሉ የጧፍ ማብራትም ሆነ ፀበል የመረጨት ስነ ስርአት አልተከናወነም።

ነገር ግን ለሚፈልጉ ሰዎች በየቤታቸው እንደሚመጣ ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንት ክላውስ ዮሃንስ "የቫይረሱን መዛመት የምንከላከለው ለምንወዳቸው ሰዎች ህይወት ስንል ነው" ብለዋል።

በቡልጋሪያዋ መዲና ሶፊያ የሰአት እላፊ የታወጀ ሲሆን ይህም ለበአል ብለው ከከተማዋ የሚወጡትን ሰዎች ለመከላከል ነው።

ሰርቢያና ሞንቴኔግሮ ህዝቡ የትንሳኤ በአልን በየቤታቸው እንዲያከብሩ ተገደዋል።

በሰሜን ሜቄዶንያ ያለችው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግን አማኞችን በኃይል ከቤተክርስቲያን እንዲቀሩ አንከለክላቸውም ብላለች።

ኮሮና
Banner