ኬንያዊው እግር ኳስ ተጫዋች በመብረቅ ተመትቶ ሞተ

ኬንያዊው እግር ኳስ ተጫዋች አለን ምቦቴ

የፎቶው ባለመብት, Daily Nation Twitter page

ኬንያዊው እግርኳስ ተጫዋች አለን ምቦቴ በመብረቅ ተመትቶ መሞቱ ለብዙዎች አስደንጋጭ ዜና ሆኗል።

የኬንያ ሚዲያ እንደዘገበው እግር ኳስ ተጫዋቹ በመብረቅ ተመትቶ የሞተው አብረውት የሚጫወቱት የቡድኑ አባላት ጎል አስቆጥረው እየጨፈሩ በነበረበት ወቅት ነው።

የ20 ዓመቱ አለን ምቦቴ እሁድ ዕለት በምዕራባዊ ኬንያ በምትገኘው ቡሲያ ግዛት ሜዳ ውስጥ ነው የሞተው።

ሬድ ሻርክ ተብለው የሚታወቁት ስድስት የቡድኑ አባላት ወደ አካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ሶስቱ ተሽሏቸው እንደወጡ የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ ሜሪ ኪያሪ ለደይሊ ኔሽን ጋዜጣ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሶስቱ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ ገልፀዋል።

ቀጣይ ጨዋታዎችም በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚካሄዱም ዴይሊ ኔሽን በዘገባው አስነብቧል።