የቴክሳስ ጥቃት ሰለባዎች፡ " እስከ ዛሬ ከማውቃቸው በጣም አስደሳች ልጆች አንዱን አጣን"

ኢርማ ጋርሺያ

የፎቶው ባለመብት, UCISD

የምስሉ መግለጫ, ኢርማ ጋርሺያ ታጣቂው መተኮስ ሲጀመር ተማሪዎችን ለመከላከል ስትሞክር ታይታለች

ኡቫልዴ ቴክሳስ በሚገኘው በሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈጸመ የተኩስ እሩምታ 19 ህጻናት እና ሁለት መምህራን ተገድለዋል።

ህይወታቸው ያለፈው ህጻናት ከሰባት እስከ 10 ዓመት መሆናቸው ተገልጿል። አንዳንዶቹም በቅርቡ ባስመዘገቡት ውጤት ከፍተኛ ሽልማት የተቀበሉ ናቸው።

አንዱ ተማሪ መደነስ የሚወድ የ10 ዓመት ልጅ ነው። ሌላዋ ደግሞ ፖሊስ ለመጥራት ስትሞክር ነበር ህይወቷ ያለፈው።

ከአስር ዓመታት በፊት በሳንዲ ሁክ ትምህርት ቤት 20 ህጻናት እና ስድስት ጎልማሶች ከተገደሉ ወዲህ በአሜሪካ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እጅግ አስከፊው ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል

በጥቃቱ ከተገደሉት ልጆች መካከል ዝምድና ያላቸውም ይገኙበታል።

'እስከ ዛሬ ከማውቃቸው በጣም አስደሳች ልጆች አንዱ ነው'

አንዳንድ ወላጆች ከተኩሱ በፊት በትምህርት ቤት ተገኝተው ልጆቻቸው በሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ ምስክር ወረቀት ሲበረከትላቸው በኩራት ተመልክተዋል። ከሰዓታት በኋላ በተኩሱ ምክንያት ተመልሰው ወደ ትምህርት ቤቱ አቀኑ።

አሜሪ ጆ ጋርዛ መሞታቸው ከተረጋገጠ የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት። ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር 10ኛ የልደት በዓሏን ያከበረችው። አያቷ በርሊንዳ አይሪን አሪዮላ ወደ ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ለመደወል ስትሞክር በጥይት ተመትታለች ሲሉ ለዴይሊ ቢስት ተናግረዋል።

አሜሪ "እጅግ ተግባቢ" እና "በአስተማሪ የምትወደድ" እንደነበረች አክለው ተናግረዋል።

አንድ የቤተሰብ አባል በፌስቡክ ላይ "እባካችሁ የትኛውንም ሰከንድ እንደ ቀላል ነገር አትውሰዱ። ቤተሰብዎን ይቀፉ፤ እንደሚወዷቸውም ይንገሯቸው" ሲሉ አስፍረዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት, 1
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ, 1

ዣቪየር ሃቪየር ሎፔዝ 10 ዓመቱ ነው። "አስደሳች እና ተጫዋች" ልጅ መሆኑን የቅርብ ዘመዱ ሊዛ ጋርዛ ይናገራሉ።

የሞቱን ዜና ሲሰሙ እሳቸውም ሆኑ ቤተሰቡ ክፉኛ መደንገጡን ግራዛ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ለፋሲካ አግኝተውት እንደነበርና በዓሉን ከቤተሰቡ ጋር በማሳለፉ መደሰቱንም ይናገራሉ።

ዣቪየር ዳንስ የሚወድ ሲሆን የቲክ ቶክ ተከታታይም ነበር ብለዋል።

በተምህርት ቤቱ የሚማሩ ሌሎች ዘመዶች እንዳሏቸው ጋርዛ አስታውቀው አንዳንዶቹ ቢጎዱም መትረፋቸውን ገልጸዋል። አንዱ በሳን አንቶኒዮ ሆስፒታል ህክምናውን በመከታተል ላይ ይገኛል ብለዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት, 2
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ, 2

Short presentational transparent line

ኡዚያህ ጋርሺያ ስምንት ዓመቱ ነው። "እስከ ዛሬ ከማውቃቸው በጣም አስደሳች ልጆች አንዱ ነው" ሲሉ አያቱ ማኒ ሬንፍሮ ያስታውሱታል።

ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ትምህርት ቤት በተዘጋበት ወቅት መሆኑን አስታውሰው እግር ኳስ ስንለማመድ ነበር ብለዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት, 3
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ, 3

Short presentational transparent line

"በጣም ፈጣን ልጅ ሲሆን ኳስ ሲቆጣጠርም ጎበዝ ነበር። አንዳንድ የተለማመድናቸውን ነገሮች እያስታወሰ ደግሞ ይሠራ ነበር" ሲሉ ያስታውሳሉ።

'ከመቼውም ጊዜ የከፋው ቅዠት'

የ44 ዓመቷ ኢቫ ሚሬልስ መገደሏ የተረጋገጠ የመጀመሪያዋ መምህርት ነች። በሁለት ቋንቋ እና በልዩ ትምህርት የሰለጠነች ናት። በኡቫልዴ አካባቢ የአራተኛ ክፍል ተማሪዎችን ለ17 ዓመታት አስተምራለች።

በትምህርት ቤቱ ድረ-ገጽ ላይ በተለጠፈው አጭር የህይወት ታሪኳ ላይ የሩጫ እና የእግር ጉዞ እንደምትወድ ተገልጿል።

"ደጋፊ፣ አዝናኝ እና አፍቃሪ ቤተሰብ" እንዳላት ትናገራለች።

የሚሬሌስ ባለቤት ሩበን ሩይዝ የተባለ የአካባቢው የፖሊስ መኮንን ከሁለት ወራት በፊት በኡቫልዴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተኩስ ልምምድ ወቅት ጥንቃቄዎችን በተመለከተ ስልጠና መስጠቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ልጇ አዳሊን ሩዪዝ በትዊተር ገጿ ላይ ባስተላለፈችው መልዕክት "ሙሉ የምታደርገኝ" ስትል ገልጻ "ከተማሪዎቿ ፊት ሆና ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መንገድ ህይወታቸውን ለማዳን መሞከሯን" ጨምራ አወድሳለች።

"ሁሉም ነገር እንዲመለስ እፈልጋለሁ።ልቤ ለዘላለም እንደተሰበረ ይኖራል" ብላለች።

የሚሬልስ አክስት ሊዲያ ማርቲኔዝ ዴልጋዶ በፌስቡክ ገፃቸው ሃዘናቸውን ገልጸው " የተኩስ ጥቃቶች በመቀጠላቸው በጣም ተናድጃለሁ" ብለዋል። የቅርብ ዘመዷ ክሪስቲና አሪዝማንዲ ሚሬሌዝ ደግሞ "ይህ የማይታሰብ ነው ... ከመቼውም ጊዜ የከፋው ቅዠት" ነው ስትል ገልጻለች።

አንድ በሐዘን የተደቆሰ ወላጅ በትዊተር ላይ ለሚሬሌስ ያላቸውን ክብር አስፍረዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት, 4
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ, 4

Short presentational transparent line

በተከፈተው ተኩስ ከሞቱት መካከል ሁለተኛዋ መምህርት የ46 ዓመቷ ኢርማ ጋርሺያ ናት።

በሮብ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ23 ዓመት አገልግላለች። እአአ በ2019 ትምህርት ቤቱ ለዓመቱ ምርጥ መምህርነት ዕጩ አድርጓት ነበር። ከሚሬሌስ ጋር ለአምስት ዓመታት በጋራ ሠርተዋል።

ለ24 ዓመታት በጋብቻ የቆችው ጋርሺያ የአራት ልጆች አናት ነበረች። ከባለቤቷ ጋር ምግብ ማብሰል እና ሙዚቃ ማዳመጥ ትወድ ነበር።

ልጇ በህግ ማስከበር የተሰማራ ጓደኛው እናቱ ተማሪዎችን ከጥቃት አድራሹ ለመከላከል ስትሞከር መመልከቱን መናገሩን ኤንቢሲ ገልጸዋል።

የወንድሟ ልጅ የሆነው ጆን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "አክስቴ አልተሰካላትም። በክፍሏ የነበሩ ልጀችን ለመከላከል ስትሞክር ተሰውታለች" ብሏል።

"ኢርማ ጋርሺያ ስሟ ነው።ጀግና ሆና አልፋለች። በብዙዎች የምትወደድ ነበር። ሁሌም ትናፈቃለች" ሲል ገልጿታል።