የሩሲያ ወታደሮች አስክሬን ኪዬቭ አቅራቢያ ተጥሎ ተገኘ

የሩሲያ ወታደሮች አስከሬን

በዩክሬን ዛቫላሊቪካ በተሰኘችው መንደር ውሾች አስክሬኖቹ ያሉበትን ስፍራ ደጋግመው በመቆፈራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ጉዳዮን ለአስተዳዳሪዎች አመልክተዋል።

ይህንንም ተከትሎ የዩክሬን ወታደሮችን ያቀፈ ቡድን በስፍራው ተገኝቶ ፍተሻ ሲያደርግ የሩሲያ ወታደር መሆኑ በደንብ ልብሱ የተረጋገጠ አስክሬንን አግኝተዋል።

በተደረገው ተከታታይ ፍተሻም ከዩክሬን ዋና ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው መንደር ተጨማሪ የሩሲያ ወታደሮች አስክሬን እየተገኘ ሲሆን ወታደሮቹ ኪዮቭን ለመቆጣጠር ተሰማርተው ያልተሳካላቸው ናቸው ተብሏል።

ታዲያ እንደ ዩክሬን ገለጻ ሩሲያ የወታደሯቾን አስክሬን ለማንሳት ብዙም ፍላጎት አላሳየችም።

አስክሬኖቹ ከነበሩበት አከባቢ እየተነሱ ሲሆን ወደ ዩክሬን የሩሲያ ወታደር አስክሬኖችን ወደምታሳርፍበት ተንቀሳቃሽ የአስክሬን ማቆያ ውስጥ አርፈዋል።

እነዚህ አስክሬኖች በተጠቀለሉበት ፕላስቲክ ላይ ቁጥሮች የተጻፈባቸው ሲሆን በስፍራው የነበሩ የቢቢሲ ዘገቢዎች በሁለት የአስክሬን ማቆያዎች ውስጥ ቢያንስ 137 አስክሬኖችን ተመልክተዋል።

ዩክሬን የአስክሬኖቹን ማንነት ለመለየት እያጣረች ሲሆን ከአንድ አንድ ሟቾች የተገኙ የባንክ ካርዶች እና የሩሲያ ወታደር የሚንጠለጠሉ መለያዎች ላይ ምርመራ እያደረገች ነው።

"ቢያንስ እነዚህን ለቤተሰኖቻቸው የመላክ እድል አላቸው" ብሏል ጉዳዩ እንዲያስረዳ የተመደበው ሰው። ሰውዬው ተገኘ ያለውን የሩሲያ ጦር አርማ ያለበትን ቲሸርትም አስመልክቷል።

ሩሲያ "የራሳችንን አንጥልም" የሚል በኩራት የሚገልጹት መፈክር አላቸው። ይህ መፈክር ሩሲያ በዩክሬን ለፈጸመችው ወረራ ፕሬዝዳንት ፑቲን እንድደ ምክንያት የሚያቀርቡት ነው።

"ወታደሮቻቸውን አይፈልጓቸውም። እዚህ ጠለዋቸው ሸሽተዋል" ሲሉ ኮረኔል ቮሊዲሚር ሊያማዚን የተባሉ የዩክሬን የጦር መኮንን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የሩሲያ ወታደሮች አስከሬን

የቢቢሲ ዘጋቢዎች የሟቾችን ዕድሜ በትክክል ማወቅ ባይችልም ወደ እሳት ሲሮጡ የነበሩ ወጣት እና ልምድ የሌላቸው መሆኑን ተረድተዋል።

ለቢቢሲ አስተያየቱን የሰጠው የጦር መኮንን ሩሲያ እንዲመለሱ የምታፈልጋቸውን አስክሬኖች ስም ዝርዝር ማቅረቧን ገልጸዋል።

"እኛ ሁሉንም ለመመለስ ዝግጁ ነን። በምላሹ ደግሞ የኛን ወታደሮች አስክሬን እንፈልጋለን። አስክረኖቻችንን ለማግኘት ያላደረግ ነው ጥረት የለም። ምላሽ ማግኘት ግን አልቻልንም" ሲል ኮረኔል ቮሊዲሚር ሊያማዚን አስረድቷል።

በሁለቱም ወገን በጦርነቱ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለማወቅ አዳጋች ሆኗል። ሆኖም ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዩክሬናውያን በጦርነት ሜዳ የሞቱ የቤተሰብ አባላቶቻቸውን ለማግኘት የራሳቸው መግስት እየረዳቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል።

አንዲት በጦርነቱ ምክንያት ባለቤቷ የሞተባት ሴት አስክሬኑንን ለማግኘት ሶስት ወር መጠበቅ እንደነበረባት ተናግራለች።

ከዚህ በተቃራኒ በዩክሬን የሩሲያ ወታደሮችን አስክሬን ማገኘት ቀላል ነው።