በአሜሪካ ለልጆች ሞት የመጀመርያው ምክንያት የጦር መሣሪያ መሆኑን ጥናት አመለከተ

የጦር መሳሪያ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አንድ ጥናት በፈረንጆቹ 2020 ዓ/ም የጦር መሣሪያ ለበርካታ የአሜሪካዊያ ልጆች ሁነኛ የሞት መንስኤ መሆኑን አመለከተ፡፡

ከዚህ ቀደም ለከፍተኛ ሞት ምክንያት የነበረው የመኪና አደጋ ሲሆን ይህ በ2020 በጦር መሣሪያ ተተክቷል፡፡

የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የተገኘ አሐዝ እንዳመላከተው በአሜሪካ በ2020 ብቻ 4ሺህ 300 ወጣት አሜሪካዊያን የሞታቸው መንስኤ ከጦር መሣሪያ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ይህም ሲባል በጦር መሣሪያ ራስን ማጥፋት፣ ሌላውን ተኩሶ መግደል፣ ሆን ብሎም ባይሆን በአጠቃቀምና በሌሎች አጋጣሚዎች ነፍስ ማጥፋትን ሁሉ ያካተተ ነው፡፡

ራስን በጦር መሣሪያ ማጥፋት ለዚህ አሐዝ አስተዋጽኦ ቢያደርግም አብዛኛዎቹ ሞቶች ግን በጦር መሣሪያ ሌላውን ከመግደል ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

በአሜሪካ 390 ሚሊዮን የጦር መሣሪያዎች በግለሰቦች እጅ ይገኛሉ፡፡

ይህ በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ሜዲሲን የታተመ አሐዝ እንዳሳየው ዕድሜያቸው ከ1 ዓመት እስከ 19 ዓመት ያሉ አዳጊ ወጣቶች በብሔራዊ ደረጃ ከጦር መሣሪያ ጋር ተያይዞ በሚከሰት ሞት ምክንያት ከሚሞቱት 33.4 እጅ ይይዛሉ፡፡

ሰዉን በጦር መሣሪያ መግደል በአሜሪካ በስፋት ለሞት ለብዙ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡

ራስን በጦር መሣሪያ አማካኝነት ራስን ማጥፋት ደግሞ ካለፉት ዓመታት በ1.1 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል።