በኬንያ ብሔራዊ ፓርክ በተቀሰቀሰ እሳት 600 ሄክታር ደን ወደመ

እሳቱ የተነሳበት ፓርክ

የፎቶው ባለመብት, Samuel Ihure

በኬንያ ብሔራዊ ፓርክ በተቀሰቀሰ እሳት 600 ሄክታር ደን ወደመ።

ስመ ገናናው የኬንያ የአበርዳሬስ ብሄራዊ ፓርክ እና ደን ላይ ከደረሰው የእሳት አደጋ 90 በመቶው በቁጥጥር ስር መዋሉን ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።

የእሳት አደጋ ተከላካዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ከቅዳሜ ጀምሮ እሳቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው።

መጀመሪያ ላይ እሳቱ ሆን ተብሎ ነው የተቀሰቀሰው የሚሉ መረጃዎች ወጥተው ነበር።

መንግሥት በበኩሉ እሳቱ እንዴት እንደጀመረ ምርመራ መጀመሩን ተናግሯል።

በአደጋው ከ600 ሄክታር የሚበልጥ ደን ወድሟል።

ይህም ጥብቅ ዝሆኖችን እና ጥቁር አውራሪሶች ስጋት ላይ ጥሏል።