በድህረ-ኮቪድ ወቅት የቻይና ኢኮኖሚ 18.3 በመቶ አደገ

የቻይና ፋብሪካ ሰራተኞች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የቻይና ኢኮኖሚ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ 2021 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 18.3 በመቶ አደገ፡፡

ቻይና ከአውሮፓውያኑ 1992 ጀምሮ የሩብ ዓመቱን ዕድገት መመዝገብ የጀመረች ሲሆን ይህም ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ትልቁ ዕድገት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

የሮይተርስ የምጣኔ ሃብት ጥናት የ 19 በመቶ ዕድገት እንደሚኖር በመተንበዩ የአሁኑ ቁጥር ከሚጠበቀው በታች ሆኗል፡፡

ካለፈው ዓመት ግዙፍ የኢኮኖሚ መቀነስ ጋር ሲወዳደርም የተዛባ እና ጠንካራ ዕድገትን የሚያመለክት አይደለም ተብሏል፡፡

እንደ መነሻም በቻይና የኮሮናቫይረስ ከፍተኛ በሆነበት እና ሃገር ዓቀፍ የእንቅስቃሴ እገዳ በተጣለበት የ2020 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተመዘገበውን 6.8 በመቶ ዕድገት ወስዷል።

የቻይና የስታቲስቲክስ ቢሮ የተለቀቁ ሌሎች ቁልፍ አኃዞችም ቀጣይ ዕድገትን ቢያመለክቱም ከነበረው ካለፈው ዓመት ጋር ስለሚነጻጸሩ ጥንካሬው እምብዛም ነው ተብሏል፡፡

በመጋቢት የኢንዱስትሪ ምርት ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው አንጻር በ 14.1 በመቶ ከፍ ሲል የችርቻሮ ሽያጭ ደግሞ 34.2 በመቶ አድጓል፡፡

"ተስፋ ሰጪ በሆነ መልኩ ወርሃዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወሮች ድክመት ቢኖርም በመጋቢት ወር የኢንዱስትሪ ምርት፣ የፍጆታ እና ኢንቨስትመንት ዕወድገት አሳይተዋል" ሲሉ በኦክስፎርድ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሉሲ ኩይስ ገልጸዋል፡፡

ሁሉም ነገር ለቻይና ኢኮኖሚ አልጋ በአልጋ አልሆነም። የመንግሥት የበጀት እና የገንዘብ ማበረታቻ እርምጃዎች እየቀነሱ በመሆናቸው የአንዳንድ ዘርፎች ዕድገት እንደሚቀንስ ተንታኞች ተናግረዋል።

የኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት ባልደረባው ዩ ሱ እንዳሉት የቅርብ ጊዜ አኃዞች የቻይና ኢኮኖሚያዊ ማገገሚያ ሰፊ መሠረት ያለው እንደሆነ ቢያሳዩም አንዳንድ የምርት እና የወጪ ንግድ እንቅስቃሴዎች ከመጀመሪያው ሩብ ዓመት በፊት "ሊሰጡ" ይችሉ ነበር የዕድገት መቀዛቀዝ መኖሩን ይጠቁማሉ፡፡

አሃዞቹ እንደሚያመለክቱት ቻይና በ 2020 የመጨረሻ ሩብ ዓመት የ 6.5 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቷን እንዳስቀጠለች ነው፡፡

በጥብቅ የቫይረሱ መከላከያ እርምጃዎች እና ለንግድ ድርጅቶች አስቸኳይ እፎይታ በመስጠት ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ኢኮኖሚው በተከታታይ እያገገመ ነው፡፡

የዓመቱ አጀማመር ከባድ የነበረ ቢሆንም በ 2020 ዕድገትን በማስመዝገብ ቻይና ብቸኛዋ የትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት ነች፡፡

ከዓለም ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤቶች ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው ቻይና 2.3 በመቶ ዕድገት ብታስመዘግብም በአስርት ዓመታት ውስጥ ደካማው ነው፡፡

ቻይና ባለፈው ዓመት ዕቅዷን በመተው ለ 2021 የ 6 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ አቅዳለች፡፡

ኮሮናቫይረስ ግን አሁንም በቻይና ኢኮኖሚ ላይ ጥላው እንዳጠላ ነው፡፡