ከኮሮናቫይረስ በኋላ ኢኮኖሚያቸው በቶሎ ሊያገግም የሚችል አምስት አገራት

ኒው ዮርክ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኒው ዮርክ

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አገራት ከበሽታ ጋር በሚያደርጉት ትግል በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። ከዚህ አንጻር ከወረርሽኙ በኋላ የትኞቹ አገራት በተሻለ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንደሚመለሱ ባለሙያዎች ለመገምገም ሞክረዋል።

ይህንን በተሻለ ለመረዳት የኢንሹራንስ ኩባንያ የሆነው ኤፍ ኤም ግሎባል የ2019 ዓለም አገራት የምጣኔ ሃብት ፈተናን የመቋቋም አቅም አመላካች ደረጃን ተመለከትን።

በዚህም አገራት ለቫይረሱ የሰጡትን የመጀመሪያ ምላሽ ከግምት በማስገባት ቀውሱን በተረጋጋ መንገድ የሚወጡበትን ሁኔታና የመቋቋም ዕድላቸው ተቃኝቷል።

ዴንማርክ

በደረጃ ጠቋሚው በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠችው ዴንማርክ ከቫይረሱ ስርጭት አንፃር ማኅበራዊ ርቀት እንዲተገበር በፍጥነት እርምጃ ወስዳለች።

ጥቂት በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንደተገኙ ነው ትምህርት ቤቶችን፣ አስፈላጊ ያልሆኑ ሥራዎችንና ድንበሯን በፍጥነት በመዝጋት ውሳኔዋ ውጤታማ መሆኑን ያረጋገጠችው።

የዴንማርካዊያን ባህል የሆነው በመንግሥት ላይ እምነት ማሳደርና ለጋራ ዓላማ አብሮ የመቆም ፍላጎት በእርምጃዎቹ ውጤታማነት ላይ አውንታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል።

እናም ብዙ ሰዎች ለሕዝብ ጤና ሲሉ መስዋዕት የማድረግ የሞራል ግዴታ እንደሆነ ይሰማቸዋል።

በዚህ ወቅት ዴንማርክ የሠራተኞችን ደመወዝ እስከ 90 በመቶ ድረስ ለመክፈል መወሰኗ እንደ ምሳሌ እንድትታይ አድርጓታል። ይህን ግን ቀላል አይደለም። እርምጃው ከጠቅላላው የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት 13 በመቶውን ያህሉን ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ዴንማርክ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዴንማርክ

ሲንጋፖር

ሲንጋፖር በጠንካራ ኢኮኖሚዋ፣ በአነስተኛ የፖለቲካ አደጋ፣ ጠንካራ መሠረተ ልማት እና ዝቅተኛ ሙስና በደረጃ ጠቋሚው 21ኛ እንድትሆን አድርጓታል። አገሪቱ ቫይረሱን ለመቆጣጠር በፍጥነት ከመንቀሳቀስ ባለፈ ስርጭቱም የተረጋጋ ነው።

ቫይረሱን በመዋጋት ረገድ በግልጽነት በሚሰራው መንግሥት ላይ ሕዝቡ ከፍተኛ እምነት አለን። መንግሥት አንድ ውሳኔ ካስተላለፈ ሁሉም ተገዢ ሆኖ ተግባራዊ ያደርጋል።

እንደ ትንሽ አገርነቷ የሲንጋፖር በጣም ስኬታማ መልሶ የማንሰራራት ውጤት ለማስመዝገብ በተቀረው ዓለም የማገገም ሂደት ላይ የተመሠረተ ነው።

ሴንጋፖር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሴንጋፖር

ዩናይትድ ስቴትስ

የዩናይትድ ስቴትስ ሰፊ ጂኦግራፊያዊ ቦታ መያዟ በደረጃ ጠቋሚው ላይ በሦስት የተከፈለች ሲሆን በአጠቃላይ ጥሩ ደረጃ ይዛለች።

ቫይረሱ እንደ ኒው ዮርክ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ ፈታኝ ሲሆን፤ የሥራ አጥነት መጠኑም ታሪካዊ በሚባል ደረጃ ከፍ ብሏል። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የተወሰደው አስገዳጅ የእንቅስቃሴ ገደብና ሌሎችም ለዚህ በምክንያትነት ተቀምጠዋል።

ነገር ግን የአሜሪካ መንግሥት ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የማነቃቂያ እርምጃዎችን በፍጥነት መውሰዱና ማኅበራዊ ርቀት መጠበቅ መተግበሩ ውጤት በማምጣት የቫይረሱ አጠቃላይ ተፅእኖን ሊቀንስና ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ማገገም ሊያስገኝ ያስችላል።

21 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማበረታቻ ይፋ ያደረገችው አሜሪካ፤ ሩብ ያህሉን የዓለም አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርትን በመያዟ ወሳኝ የሚያደርጋት ሲሆን የዓለም ምጣኔ ሃብት ማገገም በአሜሪካ ውጤታማነት ላይ ጥገኛ እንደሆነ ይነገራል።

ሲያትል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሲያትል

ሩዋንዳ

በቅርብ በተደረጉት በኮርፖሬት አስተዳደር ማሻሻያዎች ምክንያት ሩዋንዳ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በደረጃ ጠቋሚዎች ውስጥ ትልቁን መሻሻል በማድረግ በዓለም ላይ የ77ኛ ደረጃን፣ ከአፍሪካ ደግሞ የአራተኛ ደረጃን ይዛለች።

ከሁሉም በላይ ደግሞ በአውሮፓዊያኑ 2019 በጎረቤትዋ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ድንበር ላይ በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር ከቻለች በኋላ እንደዚህ ዓይነቱን ቀውስ ለመከላከል በጥሩ ሁኔታ የተቀመጠች ይመስላል።

ሁለን አቀፍ የጤና አጠባበቅ፣ የህክምና ቁሳቁስን በሚያደርሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) እገዛ እና በድንበር ላይ የሙቀት ልየታ በማድረግ ሩዋንዳ በዚህ ቀውስ ወቅት ከሌሎች የአካባቢው አገራት አንጻር ጥንካሬዋን ጠብቃ ትቆያለች።

ሩዋንዳ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ቤት ለቤት ነፃ ምግብ እያሰራጨች የምትገኝ ሲሆን ይህም ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት የመጀመሪያዋ ያደርጋታል።

የቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚገጥመው ይጠበቃል። ሩዋንዳም ለብዙ የዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖች ተወዳጅ መድረሻ ናት።

አገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሚሆኑ እና በፍጥነት ለማገገም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳላት ይታመናል።

ሩዋንዳ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሩዋንዳ

ኒውዚላንድ

ኒውዚላንድ በደረጃ ጠቋሚው የ12ኛ ቦታን ይዛለች። አገሪቱ ድንበሮችን ለዓለም አቀፍ ተጓዦች በመዝጋትና አስፈላጊ ያልሆኑ ሥራዎችን በፍጥነት በመዝጋት የቫይረሱ ስርጭትን ለመቆጣጠር መንቀሳቀስ ችላለች።

ቱሪዝምና የወጪ ንግድ የምጣኔ ሃብቷ ዋና አካል ሲሆኑ ኒውዚላንድ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አንዳንድ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያጋጥማታል ተብሎ ተሰግቷል። ነገር ግን ይህ የግድ መጥፎ ውጤት ላይኖረው ይችላል።

ወረርሽኙ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳርፈው ጉዳት ቀላል የሚሆን ባይሆንም ኒወ ዚላንድ ግን ይህንን ተቋቁማ ለማገገም ብዙም እንደማትቸገር የምጣኔ ሃብት ሙያተኞች ያምናሉ።

ኒውዚላንድ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኒውዚላንድ
ኮሮና
Banner