የእንግሊዝ ፓርላማ አባላትን በቺምፓንዚ የሚመስለው ስእል 353 ሚሊየን ብር ተሸጠ

የእንግሊዝ ፓርላማ አበላትን በቺምፓንዚ የሚመስለው ስእል

የፎቶው ባለመብት, Sotheby's

የእንግሊዝ ፓርላማ አባላትን በቺምፓንዚዎች መስሎ የሚያሳየው አራት ሜትር የሚረዝመው ስእል ለጨረታ ቀርቦ 12.2 ሚሊየን ዶላር (353 ሚሊየን ብር) ተሸጠ።

ማንነቱ ባልተገለጸ ባለሙያ የተሰራው ስእል እ.አ.አ. በ 2009 ነበር እንግሊዝ ብሪስቶል ውስጥ የተሳለው።

ስእሉ ምናልባት ቢበዛ ከ2.5 ሚሊየን ዶላር በላይ አያወጣም ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም በአስገራሚ ሁኔታ ለንደን ውስጥ ከተገመተለት አምስት እጥፍ ከፍ ባለ ዋጋ መሸጡ የስእሉ ባለቤት የሆነው 'ባንክሲ' አስታውቋል።

ለ 13 ደቂቃዎች በቆየው የጨረታ ስነ ስርአት ይህን ያክል ገንዘብ መገኘቱ ግረምታን ፈጥሯል።

የአጫራች ድርጅቱ ''በብሬግዚት ጉዳይ ደጋፊም ሆነ ተቃዋሚ ይህንን ስእል ሲመለከት ያለምንም ጥርጥር ከምን ጊዜውም በበለጠ ጎልቶ የሚወጣ ጥበብ መሆኑን መረዳት ይችላል'' ብሏል።

እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት የምትሰናበትበትን ብሬግዚትን የተመለከተው ሕዝበ ውሳኔ ከተካሄደ በኋላ የእንግሊዝ ፓርላማ በአንድ ጉዳይ ላይ መስማማት ሳይችሉ ብዙ ወራት ተቆጥረዋል።

የቀድሞዋ ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ የብሬግዚት እቅድ በእንግሊዝ የሕዝብ እንደራሴዎች 432 ለ 202 በሆነ ድምጽ ውድቅ መደረጉም የሚታውስ ነው።

አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ድል መቀዳጀታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ፤ በሥልጣን ዘመናቸው ቅድሚያ የሚሰጡት ብሬግዚትን እውን ለማድረግ፣ አገሪቱን ለማዋሀድና የሌበር ፓርቲው ጀርሚ ኮርቢን ለማሸነፍ እንደሆነ ተናገረው ነበር።