ለናይሮቢው የሽብር ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን ወሰደ

በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ከሚገኙት ቅንጡ ሆቴሎች አንዱ በሆነው ዱሲት2ናይሮቢ የሽብር ጥቃት እየተፈጸመ ነው።
ለሽብር ጥቃቱም አልሸባብ ኃላፊነቱን ወስዷል። የአልሸባብ ቃል አቀባይ በናይሮቢ ለደረሰው ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ለቢቢሲ ሶማልኛ በስልክ ተናግሯል። የአልሸባብ ቃል አቃባይ ጨምሮም ''በናይሮቢ ኦፕሬሽን እያካሄድን ነው'' ብሏል።
ከሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ በኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የተኩስ ድምጽ ሳይቋረጥ ተሰምቶ ነበር። የአይን እማኞች እንደሚሉት አራት የታጠቁ ወንዶች ወደ ሆቴሉ ቅጥር ጊቢ ሲገቡ አይተዋል።

ከፍንዳታው በኋላ የተኩስ ድምፅም የተሰማ ሲሆን አንድ ግለሰብም በጥይት ቆስሎ ሰዎች ተሸክመውት ሲወጡ ታይቷል።
በጥይት ተመተው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በህንጻው አቅራቢያ ህክማና እየተደረገላቸው ነው።
በስፍራው የነበረው ሮበርት ሉታ የተባለ የፌስቡክ ተጠቃሚ የነበረውን ሁነት እንደሚከተለው በፌስቡክ አማካኝነት በቀጥታ አሰራጭቶት ነበር። በዚህ በቀጥታ በተሰራጨው ምስል ላይ ሰዎች ህይወታቸውን ለመታደግ ሲሯሯጡ፣ ከፎቅ ላይ ሲዘሉ እና በጥይት የተመቱ ሰዎችን ምስል ያሳያል።
የሚፈልጉት ይዘት የለም
በ Facebook ተጨማሪ ይመልከቱቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም.የ Facebook ይዘት መጨረሻ

''ጥቃት እየተፈጸመብን ነው'' በማለት በዱሲት2ናይሮቢ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው ለሬውተርስ የዜና አገልግሎት ተናግሯል።
ሌላው የትዊተር ተጠቃሚ ሮን ንጌኖ የተሰኘው ፍንዳታው በተሰማበት አካባቢ በነበረው ሆቴል ውስጥ በመታጠቢያ ቤት መደበቁንና ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ገልጿል።
ከባድ ፍንዳታ ከመስማቱም በተጨማሪ ተኩስ መሰማቱንም አክሎ ከተናገረ በኋላ "ዛሬ ከሞትኩኝ ፈጣሪዬን እንደምወድና ለቤተሰቤ እንደምወዳቸው ንገሩልኝ" ብሎ ስማቸውን ዘርዝሯል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
ዱሲት2ናይሮቢ የሆቴል አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ቢሮዎች አሉት።
የኬንያ የፖሊስ አገልግሎት ቢሮ ሆቴሉ በሚገኘበት ስፍራ ጥቃት መኖሩን ገልጾ ስፍራው መከለሉን እና አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንግዶችን እንዲጠቀሙ በመግለጽ ዝርዝር መረጃዎችን ይዞ እንደሚቀርብ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።













