ኬንያዊቷ አትሌት የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል የለንደን ማራቶንን አሸነፈች

ኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር

ኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር 2 ሰዓት 16 ደቂቃ 16 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት የሴቶች የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን በማሻሻል የለንደን ማራቶንን አሸነፈች።

በለንደኑ የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታ ኬንያዊያን የበላይነቱን ይዘዋል።

ፔሬስን ተከተላ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በለንደን የተካሄደውን የሴቶች ማራቶን 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

የነሐስ ሜዳሊያውን ሌላኛው ኬንያዊት ጆይስሊን ጄፕኮስጌ አሸንፋለች።

በወንዶች በተካሄደው የለንደን ማራቶን ውድድር ኬንያዊው አሌክሳንደር ሙንዮ 2 ሰዓት ከ 4 ደቂቃ 01 ሰከንድ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችሏል።

ቀነኒሳ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በውድድሩ ትልቅ አደናቆትን ያተረፈው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዚህ የለንደን የማራቶን ውድድር ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ከ2019 ወዲህ ፈጣኑን ሠዓት ማስመዝገብ ችሏል።

ቀነኒሳ በቫሌንሲያ ማራቶን ውድድር 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን የዛሬው ውጤቱ ደግሞ በአራት ሰከንድ ዝቅ በማድረግ አሻሽሎታል።

በወንዶቹ ለታላቋ ብሪታኒያ የሚሮጠው ኢምሊ ሦሰተኛ ደረጃን ይዞ መጨረስ ችሏል።