ሮናልዶ ከከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኞች ቀዳሚው ሆነ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፎርብስ ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመት ከከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኞች ቀዳሚ ሲሆን የኤንቢኤው ኮከብ ስቴፈን ከሪ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።
በቢዝነስ መፅሔቱ እንደተገለጸው ከሆነ ሮናልዶ ዝርዝሩን ለአምስተኛ ጊዜ መምራት የቻለ ሲሆን አጠቃላይ ገቢው በ15 ሚሊዮን ዶላር አድጎ 275 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።
ይህን አሃዝ መብለጥ የተቻለው ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር።
የቀድሞው የዓለም የቦክስ ሻምፒዮኑ ፍሎይድ ሜይዌዘር እአአ በ2015፣ 300 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ደግሞ በ2018 275ሚ ዶላር ማግኘት ችሎ ነበር።
የ40 ዓመቱ ፖርቹጋላዊው አጥቂ ሮናልዶ በ 2022 በከፍተኛ ክፍያ አል ናስርን በመቀላቀል በሳዑዲ ፕሮ ሊግ እየተጫወተ ይገኛል።
ከሜዳ ውጪ ባለው የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶች እና 939 ሚሊዮን በሚጠጉት የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮቹም ከፍተኛ ገቢ ያገኛል።
የኤንቢኤ ተጫዋች የሆነው የጎልደን ስቴቱ ስቴፈን ከሪ 156 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ብሪታኒያዊው ቦክሰኛ ታይሰን ፉሪ በታህሳስ ወር የዓለም የከባድ ሚዛን ሻምፒዮንነቱን በአሌክሳንደር ኡሲክ ቢነጠቅም በ146 ሚሊዮን ዶላር ወደ ሦስተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።
ፉሪ የኔትፍሊክስ የቴሌቭዥን ተከታታይ ትርኢት እና ከማልታ ቱሪዝም ጋር ያለው ውል ለገቢው ማደግ አገዛ አድርገዋል።
የሮናልዶ የረዥም ጊዜ ተቀናቃኝ የሆነው ሊዮኔል ሜሲ ከሶስተኛ ወደ 5ኛ በመውረድ ከፖርቹጋሉ አጥቂ ወደ ኋላ ቀርቷል።
በ2025 የዓለማችን ከፍተኛ ከፍተኛ ተከፋይ 10 ስፖርተኞች
- ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ እግር ኳስ፡ 275 ሚሊዮን ዶላር
- ስቴፈን ከሪ፣ ቅርጫት ኳስ፡ 156 ሚሊዮን ዶላር
- ታይሰን ፉሪ፣ ቦክስ፡ 146 ሚሊዮን ዶላር
- ዳክ ፕሬስኮት፣ የአሜሪካ እግር ኳስ፡ 137 ሚሊዮን ዶላር
- ሊዮኔል ሜሲ፣ እግር ኳስ፡ 135 ሚሊዮን ዶላር
- ሌብሮን ጀምስ፣ ቅርጫት ኳስ፡ 133.8 ሚሊዮን ዶላር
- ሁዋን ሶቶ፣ ቤዝቦል፡ 114ሚ ሚሊዮን ዶላር
- ካሪም ቤንዜማ፣ እግር ኳስ፡ 104 ሚሊዮን ዶላር
- ሾሄይ ኦታኒ፣ ቤዝቦል፡ 102.5 ሚሊዮን ዶላር
- ኬቨን ዱራንት፣ ቅርጫት ኳስ፡ 101.4 ሚሊዮን ዶላር















