የተመድ ሰላም አስከባሪዎች እንዲወጡ የማሊ መንግሥት ጠየቀ

ሰላም አስከባሪዎች

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪዎች “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠየቀ።

አብዱልዬ ዲዮፕ ሰላም አስጠባቂ ኃይሉ “የችግሩ አካል ሆኗል” ሲሉ ከሰዋል።

በሚኒሙሳ ግዛት ያሉት ኃይሎች “ውጥረቱን አባብሰዋል” ሲልም ወቅሷል።

በዚህ ግዛት ከ13,000 በላይ ወታደሮች አሉ።

ከአሥርታት በላይ የቆየ ሰላም ማስከበር ሥራ ቢሠሩም የጂሀዲስት መስፋፋትን ማስቆም አልቻሉም።

የሩሲያ ቅጥረኛ ተዋጊ ዋግነር አሁን ለማሊ መከላከያ ድጋፍ እየሰጠ ነው።

ምዕራባውያን ዋግነር በዩክሬንና በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ሰብአዊ መብት ጥሷል ሲሉ ከሰዋል።

በማሊ የቡድኑ መሪ የተባለው ኢቫን ማስሎቭ ላይ አሜሪካ ባለፈው ወር ማዕቀብ ጥላለች።

የውጭ ጉዳዩ ከዚህ ቀደም የፈረንሳይን ጣልቃ ገብነት በተመለከተም ተቃውሞ አሰምቷል።

ከቀድሞዋ የማሊ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ ጋር ያለው ግንኙነት አምና ነበር መሰናክል የገጠመው።

ሚኒስትሩ “ተመድ ከዚህ ግዛት እንዲወጣ የማሊ መንግሥት ይጠይቃል” ብለዋል።

እአአ በሰኔ 29 የተሰጣቸው ፈቃድ ማብቂያ ቢሆንም የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ሥራውን እንዲቀጥል ይሻሉ።

ከቻድ፣ ባንግላዲሽ እና ግብፅ በኩል የሚቃጡ ወታደራዊ ጥቃቶች እንደሚኖሩ ተመድ ይገልጻል።

በማሊ የተመድ ተወካይ ኤልጋሲም ዌን “የፀጥታ ምክር ቤቱ የሚወስነውን እናከብራለን” ብለዋል።

የሚሠሩበት አገር ፈቃደኛ ካልሆነ በዛ አገር ውስጥ መሥራት ፈታኝ እንደሆነ አክለዋል።