የአውሮፓ ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር የምድብ ጨዋታ ግምቶች

ጀርመን በምታስተናግደው የዩሮ 2024 ውድድር 51 ጨዋታዎች ይስተናገዳሉ።
በመክፈቻው ጨዋታ ስኮትላንድ ከአዘጋጇ ጀርመን ጋር በባየር ሚዩኒክ ስታዲየም አሊያንዝ አሬና የመጀመሪያውን ፍልሚያ ያደርጋሉ።
በስድስት ምድቦች የተከፋፈሉት ቡድኖች ከዛሬ በኋላ በየዕለቱ ከሁለት እስከ አራት የምድብ ጨዋታዎችን ያደርጋሉ።
ጨዋታዎቹ ከሰዓት 10 ሰዓት፣ ምሽት 1 እና ምሽት 4 ሰዓት ላይ በአስር የጀርመን ከተሞች በሚገኙ ስታዲየሞች ይከናወናሉ።
ለአንድ ወር ገደማ የሚከናወነው ውድድር ሐምሌ 7/2016 በበርሊን ከተማ በሚደረግ የፍጻሜ ጨዋታ ይጠናቀቃል።
የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የ51ዱን ጨዋታዎች ግምት በየጊዜው ያቀርባል።
ለዛሬ ጀርመን ከስኮትላንድ የሚያደርጉትን የመክፈቻ ጨዋታ ጨምሮ ከዛሬ አርብ ሰኔ 7 እስከ ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም. የሚደረጉ የመጀመሪያው ዙር የምድብ ጨዋታዎችን ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።
አርብ ሰኔ 7
ጀርመን ከ ስኮትላንድ
ግምት፡ 2 – 0 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 5 - 1)
ቅዳሜ ሰኔ 8
ሃንጋሪ ከ ስዊትዘርላንድ
ግምት፡ 1 – 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 3)
ስፔን ከ ክሮሺያ
ግምት፡ 2 – 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 3 - 0)
ጣልያን ከ አልባንያ
ግምት፡ 1 – 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 2 - 1)
እሑድ ሰኔ 9
ስሎቬኒያ ከ ዴንማርክ
ግምት፡ 0 – 0 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 1)
ሰርቢያ ከ እንግሊዝ
0 – 2 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 0 - 1)
ፖላንድ ከ ኔዘርላንድስ
ግምት፡ 1 - 2 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 2)
ሰኞ ሰኔ 10
ኦስትሪያ ከ ፈረንሳይ
ግምት፡ 1 – 2 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 0 - 1)
ሮማንያ ከ ዩክሬን
ግምት፡ 1 – 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 3 - 0)
ቤልጂየም ከ ስሎቫኪያ
ግምት፡ 2 – 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 0 - 1)
ማክሰኞ ሰኔ 11
ቱርክ ከ ጆርጂያ
ግምት፡ 1 – 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 3 - 1)
ፖርቹጋል ከ ቼክ ሪፐብሊክ
ግምት፡ 2 – 0 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 2 - 1)












