ጋና ከአፍሪካ ዋንጫ በጊዜ የተሰናበተውን ብሄራዊ ቡድን አልጣኝ አባረረች

አሰልጣኙ ሚሎቫን ራጄቫክ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የጋና ብሄራዊ ቡድን በካሜሩን እየተካሄደ ባለለው የአፍሪካ ዋንጫ በመጀመሪያው የውድድሩ ዙር መሰናበቱን ተከትሎ እንደሚችሉ አሰልጣኙ ሚሎቫን ራጄቫክ መሰናበታቸውን ለቢቢሲ የደረሰ መረጃ አመላክቷል።

በዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ጋና በሰርቢያዊው አሰልጣኝ እየተመራች ከሞሮኮ፣ ጋቦን እና ኮሞሮስ ጋር ባደረገችው ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የምድቧን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ ከውድድሩ ተሸኝታለች።

አራት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ያነሳችው ጋና በዘንድሮ ውድድር በኮሞሮስ 3ለ2 ተሸንፎ ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉትን 16ቱን ብድን መቀላቀል ሳይችል ቀርቷል ይህም በብሄራዊ ቡድኑ ታሪክ ዝቅተኛውን ነጥብ ሆኖ ተመዝግቧል።

ራጄቫክ እንደ አውርፓውያኑ 2021 መስከረም ላይ የጋና ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ለሁለተኛ ጊዜ ስምምነታቸውን ያደሱ ሲሆን በስምምነታቸው መጀመሪያ በጥሩ እንቅስቃሴ ጋናን ወደ 2022ቱ የካታር ዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ማጣሪያ አድርሰዋል።

ሆኖም በአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑ ባሳየው ብቃት አሰልጣኙ ተሰናብተዋል።

ታዲያ ጥቁር ከዋክብት የሚሰኘው የጋና ብሄራዊ ቡድን ለካታር 2022 የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች በጊዜያዊ አሰልጣኝ ዝግጅቱን እንደሚቀጥል ታውቋል።