ኡበር አካል ጉዳተኞችን ከታሪፍ በላይ በማስከፈሉ በአሜሪካ ፍትህ ቢሮ ተከሰሰ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው ታዋቂው ኡበር ኩባንያ የአካል ጉዳተኞችን ከታሪፍ በላይ እያስከፈላቸው ነው በሚል በአሜሪካ የፍትህ ቢሮ ተከሷል።
የኡበር "የጥበቃ ጊዜ" ክፍያ መኪና ውስጥ ለመግባት ከሁለት ደቂቃ በላይ ለሚያስፈልጋቸው አካል ጉዳተኞች አግላይ ነው ብሏል ቢሮው።
ኡበር የአሜሪካውያን የአካል ጉዳተኞች ህግን ማክበር አለበትም በማለትም አክሏል።
ኡበር በበኩሉ የጥበቃ ጊዜ ክፍያው ለአካል ጉዳተኛ ተሳፋሪዎች እንዲተገበር የታሰበ እንዳልሆነ እና ክፍያውን ተመላሽ ሳደርግ ነበር ብሏል።
የፍትህ ቢሮው የሲቪል መብቶች ክፍል ረዳት ዋና አቃቤ ህግ የሆኑት ክሪስተን ክላርክ የክሱ ዓላማ "ኡበር አካል ጉዳተኛ ተሳፋሪዎችን መኪና ውስጥ ለመግባት ተጨማሪ ጊዜ ስለሚያስፈልጋቸው ብቻ መቅጣት አይችልም" የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ያለመ ነው ብለዋል።
ኡበር እና ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች "አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ለሁሉም ሰዎች እኩል ተደራሽነትን ማረጋገጥ አለባቸው" ሲሉ ተናግረዋል።
ኡበር በበኩሉ ፖሊሲዎቹ ከአሜሪካ የአካል ጉዳተኞች ህግን የሚጥሱ ናቸው መባሉን አልስማማበትም ብሏል።
የኩባንያው ቃል አቀባዩ ድርጅቱ ይህንን "አስገራሚ እና አሳዛኝ" ክስ ከመመመስረቱ በፊት ከቢሮው ጋር እየተነጋገረ ነበር ብሏል።
የጥበቃ ጊዜ ክፍያዎች "በተመረጡት ቦታዎች ዝግጁ ሆነው ለሚጠብቁ እና ወደ መኪናው ለመግባት ተጨማሪ ጊዜ ለሚፈልጉ መንገደኞች የታለመ አይደለም" ብለዋል ።
አካል ጉዳተኛ መንገደኞች ለድርጅቱ ሲያሳውቁ ኡበር የጥበቃ ጊዜ ክፍያን የመመለስ ፖሊሲ ነበረው ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።"ባለፈው ሳምንት ከተደረገ ለውጥ በኋላ ማንኛውም አካል ጉዳተኛ መሆናቸውን የሚረጋግጥ መንገደኞች ክፍያቸው ወዲያውኑ ይሰረዛል" ሲሉ አክለዋል።
የኡበርና የአካል ጉዳተኞች ውዝግቦች
ኡበር ከአውሮፓውያኑ 2016 ጀምሮ ነው ተሳፋሪዎችን ለአሽከርካሪ የጥበቃ ጊዜ ማስከፈል የጀመረው።
ድርጅቱ አሽከርካሪዎች በአማካይ ከ60 ሳንቲም በታች እንደሚከፍሉ የሚያደርግ መሆነ ኡን ጠቁሟል። በተሽርካሪ ወንበር ሊደረጉ የሚችሉ ጉዞዎች ወይም 'የኡበር አሲስት' ጉዞዎች ቀድሞውንም ምንም አይነት የጥበቃ ጊዜ ክፍያ የላቸውም ብሏል።
ኡበር ከአካል ጉዳተኝነት ጋር በተያያዘ ራሱን ውዝግብ ውስጥ ሲያገኝ የመጀመሪያው አይደለም።
በሚያዝያ ወር በሳን ፍራንሲስኮ የምትገኝ አንዲት ማየት የተሳናት ሴት ለ14 ጊዜ ጥሪ አቅርባ መኪና ከተከለከለች በኋላ 1.1 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተወስኖበታል።
በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ደግሞ የፓራሊምፒክ ሜዳሊያ አሸናፊው ጃክ ሃንተር ስፓይቪ በመስከረም ወር ኡበር እና ሌሎች የታክሲ ሹፌሮች የዊልቸር ተጠቃሚ መሆኑን ሲያዩ አዘውትረው አለፈውት እንደሚሄዱ ተናግሯል።
በአውሮፓውያኑ 2020 በቴነሲ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት አሜሪካ ውስጥ ለአካል ጉዳተኞች የአካል ጉዳተኛ ካልሆነ ሰው ጋር ተመሳሳይ የኑሮ ደረጃ ላይ ለመድረስ 28 በመቶ ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስፈልጋቸው አረጋግጧል።
የአሜሪካ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ማሪያ ታወን ለቢቢሲ እንደተናገሩት አካል ጉዳተኞች "ብዙውን ጊዜ በሚታወቁ ምክንያቶች መለወጥም ሆነ መቆጣጠር በማይችሉት ነገር ተመጣጣኝ ያልሆነ የኢኮኖሚ ሸክም ያጋጥማቸዋል።"
ለጤና አገልግሎት፣ ለሕክምና አቅርቦቶች እና ለሚጠቀሙበት መሳሪያዎች ከሚወጣው ከፍተኛ ወጪ በተጨማሪ ለምሳሌ እንደ ግሮሰሪ ወይም ራይድሼር የመቆያ ጊዜ የመተግበር ለአካል ጉዳተኞች ተጨማሪ ክፍያ እና "ታክስ" እንደሚጨምር ተናግረዋል።
አካል ጉዳተኛ አሽከርካሪዎች የጥበቃ ጊዜ ክፍያ የማስከፈልን ማስቆም "ወደ ኢኮኖሚያዊ እና ክብር እኩልነት የመሄጃ ትክክለኛው አቅጣጫ ነው" ሲሉ ታወን አክለዋል።
ማህበሩ ተሳፋሪው ተሽከርካሪ ወንበር፣ ክራንች፣ መራመጃ ወይም መንገድ የሚመራ ውሻ ሲጠቀም የሚያዩ የኡበር አሽከርካሪዎች አልፈው የሚሄዱበትን ብዙ ጉዳዮችን ሰምቻለሁ ብሏል።
የአካል ጉዳተኞች ለተሽከርካሪ ወንበር ተደራሽ የሆኑ አገልግሎቶችን ወይም ኡበር አሲስትን ብቻ እንዲጠቀሙ መጠበቁ የኡበር ፍትሃዊ አለመሆን ያሳያል ብለዋል።
"በተለያዩ ምንገዶች ከታየ ላይ ፍትሃዊ አይደለም። የእነዚህ መኪኖች አቅርቦት ውስን ነው። ሲቀጥል ሁሉም የአካል ጉዳተኞች እርዳታ ላይፈልጉ ይችላሉ" ሲሉ አበክራ ገልጸዋል።
አንድ ሰው የድጋፍ ጉዞ እንዲጠቀም ማስገደድ "ሙሉ በሙሉ አላስፈላጊ የሆነ አንዳንዴም ውጥረት የበዛበት የአሽከርካሪና የተጓዦች ስሜትን ይፈጥራል" ሲሉ ታወን ተናግረዋል።












