የዩኬ መንግሥት ዕድሜያቸው የገፉ አርሶ አደሮችን ጡረታ እንዲወጡ ሊከፍል ነው

በሜዳ ላይ ያለ ትራክተር

የፎቶው ባለመብት, CactuSoup

አዲስ ሀይል ወደ በእርሻው ዘርፍ እንዲሰማራ በማለም የዩኬ መንግስት እድሜያቸው የገፉ የእንግሊዝ አርሶ አደሮችን በጡረታ እንዲገለሉ ሊያደርግ ነው። የጡረታ ደመወዝም ይቆርጥላቸዋል።

በአማካኝ አንድ አርሶ አደር የጡረታ ጊዜውን ክፍያ ድምር 50 ሺህ ፓውንድ ሊያገኝ ይችላለ። ሰፋ ያለ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች ደግሞ ይህ ክፍያ በእጥፍ አድጎ በአማካኝ 100 ሺህ ፓውንድ ይከፈላቸዋል።

ይህ የጡረታ ክፍያ በሰፋፊ እርሻዎች ላይ አርሶ አደሮች ከባቢያቸውን እንዲንከባከቡ የሚያበረታታው የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴ አካል ነው። ሆኖም ይህንን ሀሳብ አንቀበልም ያሉ በዕድሜ የገፉ አርሶ አደሮች አሉ።

አሁን ላይ የእንግሊዝ አርሶ አደሮች በቀደመው የአውሮፓ ህበረት ስርዓት ባላቸው የእርሻ መሬት ልክ ድጋፋ የሚደረግላቸው ሲሆን በአማካኝ ወደ 21 ሺህ ፓውንድ ያገኛሉ።

ምንም እንኳን እንደ ንግሰቲቱ ያሉ ሰዎች ባላቸው ግዙፍ የእርሻ መሬት ልክ በዓመት እስከ ግምማሽ ሚሊዮን ፓውንድ ቢከፈላቸውም።

በዌልስ ያሉ አርሶ አደሮችም በአዲሱ የዩኬ መንግስት የጡረታ ክፍያ ውስጥ እንደሚካተቱ ይጠበቃል።

ታዲያ እንደ አካባቢ ጠበቃ ባለሙያው ጆርጅ ኢውስተስ ገለጻ የአውሮፓ ህብረት የአርሶ አደሮች የድጋ ስርዓት አከባቢን ለመታደግና አርሶ አደሮችን ከስጋት ለማላቀቅ ያግዛል።

አዲሱ የዩኬ መንግስት በጡረታ የማግለል ሀሳብ ደገሞ አርሶ አደሮቹን በሌሎች የስራ መስኮች እንዲሰማሩ ያበረታታል በለዋል።

ከ 10 አርሶ አደሮች ወደ 4 የሚጠጉት ዕድሜያቸው ከ 65 በላይ ሲሆን አማካኙ ደግሞ 59 ነው።