'ምንም ጥቅም ስለሌለኝ በቃ ራሴን እንደሞተ ሰው ነው የምቆጠረው'

የፎቶው ባለመብት, BBC News
ከ38 ባላነሱ አገራት ላለፉት 20 ዓመታት ሴቶች በግዳጅ ወይም ያለፈቃዳቸው መሃን እንዲሆኑ መገደዳቸውን ሪፖርቶችን አመላክተዋል። ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት ሴቶች ሲወልዱ ከፈቃዳቸው ውጭ የተገደዱ ናቸው።
በፕሮፌሰር ሳም ሮውላንድስ በተደረገው ጥናት መሰረት በሁሉም የአለም አህጉራት ውስጥ የሚገኘውን ያለፈቃድ መካን ማድረግን እንዲያቆሙ እና መንግስታት ተጠያቂዎችን በህግ እንዲጠየቁ የተባበሩት መንግስታት ጥሪ አቅርቧል።
የጎሳ አናሳ ማህበረሰቦች፣ በኤች አይ ቪ የተያዙ ሴቶች እና ጾታ የሚለውጡትን ጨምሮ ሌሎች የተገለሉ ቡድኖች በዓለም ዙሪያ ይህ እንደሚገጥማቸው ታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጤና ጥበቃ መብት ባለሙያዋ ዶ/ር ትላለንግ ሞፎከንግ "በዓለም አቀፍ ደረጃ ከመሃንነት ጋር በተያያዘ የመድልዎ እና የመብት ጥሰት አለ። ይህ እስከ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል። ይህ በራሱ እኔ እንደማስበው አጠቃላይ የመብት ጥሰት ነው" ይላሉ።
የግዳጅ መሃንነት በታሪክ ተሻለ ዘር ለመፍጠር መሣሪያ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን እንደ ናዚ ጀርመን ካሉትም ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ጥናቱ እንደሚያመለክተው ግን እስከ 21ኛው ክፍለዘመን እንደቀጠለ ይጠቁማል።
ዚሺሎ ድሉድላ በጎርጎሮሳዊያኑ 2011 በደቡብ አፍሪካ በሆስፒታል ውስጥ በምትወልድበት ጊዜ መሃን እንድሆን ስትደረግ ፈቃደኛ አንዳልነበረች ተናግራለች።
የ50 ዓመቷ የሦስት ልጆች እናት እንደምትለው "በግዳጅ መሃን መሆን ለእኔ ትልቅ ጭካኔ ነው። ምክንያቱም የእኔ ምኞት ስላልነበረ በጭራሽ አልስማማም፡፡ ስለዚህ ነገር ብረሳው ብመኝም አልተሳካም። በሕይወት እያሉ ከሞተ ሰው ጋር አንድ ነዎት። ሆኖም እንደሞቱ ነው የሚቆጠሩት" ብላለች።
"እኔ በሕይወት ሳለሁ የሞትኩኝ ነኝ ምክንያቱም እኔ ምንም ጥቅም የሌለኝ እንደሆንኩ አውቃለሁ" ትላለች፡፡

የፎቶው ባለመብት, BBC News
ዚሺሎ እንደምትለው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስላለባት ብቻ ያለ ፈቃድ መሃን እንደሆነች ታምናለች፡፡
ዶ / ር ሞፎክንግ እንደሚሉት "ብዙ ሴቶች የሆኑት ነገር ሆስፒታል ውስጥ በነበሩበት ጊዜ መ ብታቸው ተጥሰዋል ማለት ነው፡፡"
"ሁሉም ጥቁር ናቸው። አብዛኛዎቹም ከገጠር የመጡ ናቸው፡፡ መሃን እንዲሆኑ ለማስማማት የስምምነት ቅጽ እንዲፈርሙ የተገደዱት ወይም ጫና የደረሰባቸው ናቸው፡፡"
ዚሺሎ የወለደችበት ሆስፒታል የህክምና ማስረጃዎቿ እንደሚያሳዩት በቀዶ ጥገና ከመውለዷ በፊት መሃን ለመሆን እንደፈቀደች ይናገራል፡፡
እንደመግለጫው ከሆነ ይህ የሆነበት ምክንያት ቀደም ሲል ሁለት ቀዶ ጥገና ስላደረገች እና ከብዙ ቀዶ ጥገናዎች በጤና ላይ ስጋት ስለሚጨመሩ ሴቶች ከሦስተኛው በኋላ መሃን እንዲሆኑ ማድረግ መደበኛ ተግባር መሆኑን ነው፡፡
ለቢቢሲ እንደገለጹትም "ሴቶች በግዳጅ ወይም በተጽዕኖ መሃን አይሆኑም… [በተጨማሪም] አንዳንዶች ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ምኞታቸው ይከበራል" ብለዋል ፡፡
ዚሺሎን እና ሌሎች በርካታ ሴቶች ጋር ስምምነት-አልባ መሃን የማድረግ ክሶች ዙሪያ የደቡብ አፍሪካ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት ኮሚሽን ባለፈው ዓመት ምርመራ አድርጓል፡፡ እንደ ዶ/ር ሞፎክንግ ከሆነ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብዙም አልተሠራም ብለዋል፡፡
"የደቡብ አፍሪካ የጤና ስርዓት እና መንግስት በፆታ እኩልነት ኮሚሽነር ሪፖርት ውስጥ የተካተቱትን ሴቶች የገፋ ነው" ብለዋል፡፡
"መምሪያው በራሱ እነዚህ ከባድ ጥሰቶች በእነሱ ቁጥጥር ስር መከናወናቸውን በይፋ ለመቀበል እና ለማመን ገና ነው፡፡"
የደቡብ አፍሪካ የጤና መምሪያ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ የለም፡፡
ሆኖም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለፍላጎት መሃን የማድረግ ተግባር በኤች አይ ቪ ባለባቸው ሴቶች ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡
ለምሳሌ ካናዳ ውስጥ አራት የአገሬው ቀደምት ተወላጅ ሴቶች ከ 2005 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ ከወሊድ ጋር የተዛመዱ መሃን የማድረጎች እንዲኖሩ ግፊት እንደተደረገባቸው ግሎባል ፐብሊክ ሄልዝ ያወጣው ዘገባ ይገልጻል፡፡
ሪፖርቱ በተጨማሪም በቼክ ሪፐብሊክ፣ በሃንጋሪ እና በስሎቫኪያ የሮማ ሴቶች ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ የመሃን መሆንን እንዲቀበሉ በመድኃኒትነት እንደታዘዘላቸው ያሳያል።

የፎቶው ባለመብት, Zuno Photography
ግለሰቦች በሀገራቸው ውስጥ ባሉ ህጎች ሲገደዱ ወይም ተቀስቅሰው በግዴታ መሃን እንዲሆኑ መደረም ታይቷል፡፡
በጃፓን ጾታ የቀየሩ ሰዎች ያላቸው ሰዎች በሕጋዊ መንገድ በመረጡት ጾታቸው እንዲኖሩ ለማስቻል መሃን መደረግ አለባቸው፡፡ የቀዶ ጥገና ሕክምናው ካላከናወኑ ማግባት ወይም እንደ ፓስፖርቶች ያሉ ኦፊሴላዊ ሰነዶች ላይ ጾታቸውን የመቀየር መሰረታዊ መብቶቻቸው ይገድባል፡፡
በሕንድ ደግሞ ግዛቶች የህዝብ ብዛትን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ቤተሰቦቻቸውን በሁለት ልጆች ላይ ለሚወስኑ ጥንዶች በግብር፣ በሥራ እና በትምህርት ላይ ማበረታቻዎችን ይሰጣሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጥቅማ ጥቅም ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የመጡ ወጣቶች ብዙውን ጊዜ በማይቀለበስ ሂደት እንዲያልፉ ሊያበረታታቸው ይችላል በሚል በባለሙያዎች ቅሬታ ይቀርብበታል፡፡
በእንግሊዝ የሚገኘው የቦርንማውዝ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሳም ሮውላንድስ እና ዶ/ር ጄፍሪ ዋል እንደሚሉት ህንድ መሃንነትን እምቢ ባሉ ባለትዳሮች ላይ የምግብ ራሽን ካርድን እንደመከልከል ያሉ ማዕቀቦችን ተጠቅማለች፡፡
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው መሃን መደረጋቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ያልቻሉ ሰዎች ለልጆቻቸው አልሚ ምግብ መከልከላቸውን ጠቁሟል፡፡
ከዚህም በላይ ቴሌቪዥኖችን፣ ማብሰያዎችን እና የገንዘብ ድጎማዎችን ጨምሮ የተለያዩ ማበረታቻዎች እንደሚሰጡ ማስረጃዎች አስደግው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ የገንዘብ ማበረታቻዎች ድምር ከአማካይ ወርሃዊ ደመወዝ እጥፍ ይሆናል፡፡
ያለፍቃድ የመሃን የማድረግ ምሳሌዎች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሲሆን እንደዶ/ር ሞፎክንግ ከሆነ መንግስታት እና ክልሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች መሆን አለባቸው፡፡
"ስሜትን የሚያደክም ነው። ሆኖም አንዳችን ለሌላው ከመሆን ውጭ ምርጫ የለንም። እኔ ራሴ ሴት ነኝ፣ ጥቁር ነኝ፣ የደቡብ አፍሪካ የገጠር ከተማ ነዋሪ ነኝ። በራሴ እኩዮች እና በራሴ ማህበረሰብ ላይ የተከናወኑ አስቀያሚዎቹን አንዳንድ ጉዳዮች አውቃለሁ። ግን ውጤታማ የሆነ መፍትሄ የለም "ብለዋል፡፡
"ሥራዬ በጤናው መብት ላይ ልዩ ዘጋቢ እንደመሆኔ መጠን በእነዚህ ሪፖርቶች ላይ ትክክለኛ እና ውጤታማ ምርመራ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ማሳሰብ ነው። ወንጀለኞችም በሕግ መጠየቅ አለባቸው፡፡"
"እነዚህ በጣም ከባድ እና ኢ-ሰብዓዊ [ሂደቶች] ሴቶች የሚያዙበት መንገድ ነው። ስለሆነም በህግ፣ በፖሊሲም ይሁን በተግባር እንዲቀጥል መፍቀድ የለብንም " ብለዋል።












