ቤተ ክርስቲያኒቱ 'አጭር ቀሚስ ለብሳችሁ ባትመጡ ደስ ይለኛል' አለች

የፎቶው ባለመብት, View Pictures
በኬንያ ናይሮቢ የምትገኝ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ሴቶች አጫጭር ቀሚሶችን እየለበሳችሁ እየመጣችሁ ተቸግሪያለሁ ብላለች።
በኬንያ በስፋት የሚሰራጨው የኬንያ ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ 'ሴት ምዕመናን እባካችሁ አለባበሳችሁን ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት ብታደርጉ' ስትል ተማጽናለች ብሏል።
ቅዱስ ጴጥሮስ ክላቨር ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ናት ይህን መልእክት ያስተላለፈችው። በተለይ መልእክቱ የተለላፈበት መንገድ ለብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህንን መልእክት ለምእመናኑ ያስተላለፈችው የቤተ ክርስቲያኒቱ መግቢያ በር ላይ የሰሌዳ ማስታወቂያ በመስቀል ጭምር ነው።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
በዚህ ማስታወቂያ ላይ ሴት ምእመናን ሊለብሷቸው አይገባም ያለቻቸውን 10 ዓይነት አለባበሶችን በፎቶ ጭምር በማስደገፍ ዘርዝራለች።
ከነዚህ መሀል አጭሬ ቀሚስ (ሚኒስከርት)፣ ታፋው ላይ የተቦዳደሰ ጂንስ ሱሪ፣ "ቀይ ሰይጣን" የሚል ጽሑፍ ያለበት ቲሸርት፣ የተገላለጠ ገላን የሚያሳይ ረዥም ቀሚስና ሌሎችንም ይጨምራል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህን መመሪያ በሚተላፈሉት ላይ ምን እርምጃ እንደምትወስድ ያለችው ነገር የለም።












