"የቱሪስት ማግኔት" የሆነችው ቬኒስ ከተማን ጎርፍ እያስጨነቃት ነው

የፎቶው ባለመብት, AFP
በዓለም አቀፍ ደረጃ የቱሪስት ማግኔት አላት የምትባለው የጣልያኗ ቬኒስ ከተማ በጎርፍ እየተፈተነች ነው። ጎርፉ ቬኒስን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አሳጥቷታል ተብሏል።
በጎርፉ ምክንያት የውሃ መተላለፊያ የሆነው የከተማዋ ዋና አደባባይ ሴንት ማርክ ፣ትምህርት ቤቶችና ንግድ ቤቶች ተዘግተዋል።
የጣልያን መንግስሥትም በዩኔስኮ ድረ ገፅ ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል።
ለውሃ እና ለስነ ህንፃዎቿ ጥበብ ቱሪስቶች የሚተሙላት ቬኒስን እያስጨነቀ ያለው ጎርፍ እርዝመት ማክሰኞ እለት 187 ሴ.ሜ ደርሶ ነበር ተብሏል።
ቤታቸው በጎርፍ የተጎዳባቸው የቬኒስ ኗሪዎች እስከ አምስት ሺህ ዩሮ ሲያገኙ ንግድ ቤቶች ደግሞ 20 ሺህ ዩሮ ድረስ ካሳ ይሰጣቸዋል ተብሏል።
ከመቶ በላይ ከሚሆኑ ደሴቶች የተሰራችው ቬኒስ በየአመቱ በጎርፍ የምትጠቃ ሲሆን የአሁን እንደ አውሮፓውያኑ በ1923 ተከስቶ ከነበረውና አስከፊ ከተባለው ጎርፍም የባሰ ነው ተብሏል።
የጣልያን መንግሥት ለቬኒስ 20 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል።













