በመላው ዓለም እየታየ እንዳለው አንዳንዶች ለምን አሁንም ድረስ በኮቪድ ይሰቃያሉ?

ኮቪድ የተያዘች ሴት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ኮቪድ ከጥቂት ዓመታት በፊት በመላው ዓለም ዋነኛ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት በነበረበት ጊዜ በጣም አስጨናቂ ሁኔታን ፈጥሮ ነበር።

በዚያ ወቅት ይህ የመከላከያ ክትባትም ሆነ ፈዋሽ መድኃኒት ያልነበረው ወረርሽኝ በርካቶችን ለስቃይና ለሞት በመዳረጉ ዓለም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሆኑ ከእንቅስቃሴው ተቆጥቦ ነበር።

በርካቶች በበሽታው ተይዘው ያገገሙ ሲሆን፣ ብዙዎች ደግሞ በተደጋጋሚ በበሽታው የመያዝ መጥፎ አጋጣሚ አላቸው።

የመከላከያ ክትባቱ ከተገኘ እና በርካታ የዓለማችን ሕዝብ ከተከተበም በኋላ አሁን ድረስ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች አሉ። ምንም እንኳይ የሞት መጠኑ በእጅጉ የቀነሰ ቢሆንም ስቃይ እና ህመሙ ግን እንዳለ ነው።

ታዲያ አሁን ላይ ሰዎች በኮቪድ ሲያዙ ምን ሊሰማቸው ይችላል? የሚለው አጠያያቂ ነው።

አንድ በኮቪድ ተይዞ በጠና የታመመ ሰው “በበሽታው በተደጋጋሚ ስንያዝ ህመሙ እየቀለለ ይሄዳል ብዬ አስብ ነበር” ይላል።

ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ህመሙ ምን ያህል ጠንካራ እንደነበር ሲገለጽ ቆይቷል። ባለፉት ወራትም በጠና የታመሙ ግን አሉ።

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ህመሙ በሳል ጀምሯቸው ወደ ራስ ምታት እና ከዚያም ወደ አካላዊ ድካም ይወስዳቸዋል።

ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶችም ይታያሉ።

ክትባት ከመጀመሩ በፊት በሽታው ያልያዛቸው ወይም ምልክት ያላሳዩ አሉ።

በሰዎች ተፈጥሯዊ በሽታን የመቋቋም አቅም ላይ ጥናት የሚሠሩ ባለሙያዎች እንደሚሉት አሁንም ኮቪድ ሊይዘን፣ ከቀደመው ጊዜ በባሰ ሊያመንም እንደሚችል ይናገራሉ።

ይህ የሚሆነው በቫይረሱ ባህሪ እና በሰውነት በሽታን የመቋቋም አቅም ምክንያት ነው።

ሰዎች በቫይረሱ በሚያዙበት የመጀመሪያ ወቅት ላይ ሰውነታቸው ቫይረሱን ምን ያህል መከላከል እንደሚችል መወሰን የሚቻልበት ነው።

ቫይረሱ የሰውነት መከላከል አቅምን እያዳከመ ሲሄድ እየተስተዋለ ነው።

ፕሮፌሰር ኤሊኖር ሪሊ በኤደንብራ ዩኒቨርስቲ ኢምዩኖሎጂስት (ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅምን የሚያጠና ዘርፍ) ባለሙያ ናት።

ኮቪድ ከተጠበቀው በላይ “ጠንካራ” መሆኑን ታስረዳለች።

“የሰዎች በሽታን የመከላከል አቅም ክትባቱ በተጀመረበት ጊዜ የነበረውን ያህል ደካማ ነው” ትላለች።

ፀረ ተዋህሲያን (አንቲቦዲስ) አሁንም ያላቸው አቅም ውስን መሆኑን ባለሙያዋ ታስረዳለች።

በሽታውን የመቋቋም አቅም ከፍተኛ ሲሆን፣ ቫይረሱም እምብዛም ህመም ሳያስከትል ይጠፋል።

ኮቪድ የተያዘች ሴት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

“አሁን አነስተኛ አንቲቦዲስ ስላሉ ቫይረሱ በከፍተኛ መጠን ወደ ሰውነት እየገባ ጠንካራ ህመም እያስከተለ ነው” ትላለች ባለሙያዋ።

ብዙዎች ክትባቱን ከወሰዱ ቆየት ስላሉ የሰውነት ተፈጥሯዊ በሽታውን የመከላከል አቅማቸው ተዳክሟል።

በለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ የሚሠራው ፕሮፌሰር ፒተር ኦፕንሻው በበኩሉ “ቀድሞ ክትባት በፍጥነት መሰራጨቱ ለውጥ አምጥቷል” ይላል።

አሁን ክትባቱን የሚወስዱ ሰዎች ውስን ናቸው።

በቀደመው ጊዜ ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ ክትባቱ ሲሰጣቸው አሁን ከ65 በላይ የሆኑ ሰዎች ለህመም ተጋላጭ ከሆኑ ነው ክትባቱን የሚወስዱት።

ብዙዎች ለቀናት ወይም ለሳምንታት በጠና የሚታመሙት ለዚህ እንደሆነ ባለሙያው ያስረዳል።

“በኮቪድ በጠና እንደታመሙ ሰዎች ሲናገሩ እሰማለሁ። ዘለግ ላለ ጊዜም ነው የሚታመሙት” ይላል።

ኮቪድ ከዚህ ቀደም ያልያዛቸው ሰዎች ሊያዙበት የሚችል ዕድል እንዳለ ባለሙያው ያምናል።

ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ክትባት በቅድሚያ ቢሰጥም ከ65 ዓመት በታች የሆኑም በቫይረሱ ሊያዙ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

ክትባት የመውሰድ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የቫይረሱ ባህሪ መለወጥም ሌላው ነጥብ ነው።

የቫይረሱ ባህሪው ሲለወጥ የሰውነት የመከላከል አቅምም ይደክማል። የፀረ ተዋህሲያን አቅምም እንደዚሁ ይዳከማል።

ፕሮፌሰሩ እንደሚያስረዳው፣ አሁን እየተስፋፋ ያለው ቫይረስ ቀድሞ ከነበረው የተለየ ነው።

ክትባቶች የተሠሩት ደግሞ በቀድሞው ቫይረስ መነሻነት ነው።

ኦሚክሮንን [የኮቪድ ቫይረስ አይነት] ጨምሮ ለሌሎች የቫይረሱ ዝርያዎች በርካቶች ያላቸው የመከላከል አቅም ውስን እንደሆነ ያስረዳል።

የሰውነት ህመምን የመከላከል አቅም ሲዳከም ቲ-ሴልስ በመባል የሚታወቁት ህዋሳት ለመካከል ጥረት ያደርጋሉ። ይህም ከቀደመ ህመም ተሞክሮ እና ከክትባቶች በመነሳት የሚከናወን ነው።

በኮቪድ የተያዙ ሕዋሳትን በመግደል ነው የሚታወቁት። ባህሪያቸው በሚለወጥ ቫይረሶች በቀላሉ ላለመሸነፍም ይሞካራሉ።

“በጠና እንዳንታመም ያደርጋሉ። ታመን ሆስፒታል እንዳንገባ ለማድረግ ቫይረሱን የመግደል ሥራ ይሠራሉ” ስትል ፕሮፌሰር ኤሊኖር ታስረዳለች።

የጡንቻ ሕመምን የመሰሉ ሕመሞች የሚሰማን ቲ-ሴልስ የሚባሉት ህዋሳቶቻችን ከቫይረሱ ጋር ሲዋጉ ነው።

ከዚህ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ እንደ ጉንፋን ዓይነት ምልክት ያላቸው አራት የኮሮናቫይረስ ዓይነቶች አሉ።

በልጅነታችን ወይም በሌላ የሕይወታችን ክፍል ስለያዙን ለከፋ ሕመም እንደማይዳርጉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ፕሮፌሰር ፒተር እንደሚለው በተደጋጋሚ ኮቪድ ሲይዘን ተፈጥሯዊ ቫይረሱን የመላከል አቅም እናዳብራለን።

እስከዚያ ድረስ ግን ህመሙ በተወሰኑ ሰዎች ላይ መከሰቱ አይቀርም ይላል።