አርሰናል ከሲቲ፣ ዩናይትድ ከቼልሲ ማን ያሽነፋል? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

ጊዮኬሬሽና ሀላንድ

በአምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መርሃ ግብር አርሰናል ማንቸስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።

ለሊጉ ዋንጫ እንደሚፎካከሩ የሚጠበቁት ሁለቱ ቡድኖች ኤምሬትስ ላይ ጨዋታቸውን እሑድ ያከናውናሉ።

ማንቸስተር ዩናይትድ ከቼልሲ እና ሊቨርፑል ከኤቨርተን የሚያከናውኗቸው ጨዋታዎችም ከፍተኛ ትኩረት አግኝተዋል።

በሳምንቱ ማብቂያ ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ውጤት ምን ይሆናል ብለው ይገምታሉ?

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን እነዚህን ጨምሮ የአምስተኛ ሳምንት የሊጉን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።

ቅዳሜ
ሊቨርፑል እና ኤቨርተን

ሊቨርፑል ከ ኤቨርተን

ኤቨርተን የውድድር ዓመቱን በጥሩ አቋም ጀምሯል። ጃክ ግሪሊሽ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ሲሆን ቤቶም የሚቀመስ አልሆነም።

ዴቪድ ሞዬስ ደግሞ ለመስበር የሚከብድ ቡድን በመስራት አይታሙም።

ሊቨርፑል ባለቀ ሰዓት ማሸነፉን ቀጥሎ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ሦስት ነጥብ ነጥቋል።

ቡድኑ በጥሩ አቋም ላይ ባይሆንም ብዙ አማራጮች ያሉት ቡድን መሆኑ ለዚህ ጨዋታ ወሳኝ ይሆንለታል።

ግምት፡ 2 - 0

ብራይተን ከ ቶተንሃም

ቶተንሃም በሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ቪያሪያልን ቢያሽነፍም ጥሩ አልተንቀሳቀሰም።

ስፐርስም እንደ ሊቨርፑል ጥሩ ሳይጫወት ነጥቦችን መሰብሰቡን ቀጥሏል።

ክሪስቲያን ሮሜሮ እና ሚኪ ቫን ደ ቬን በሻምፒዮንስ ሊጉ ጨዋታ ድንቅ ነበሩ።

ብራይተን ወጥ አቋም ማሳየት ባይችልም ድንቅ አጥቂዎችን ይዟል።

ግምት፡ 2 - 1

በርንሌይ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

በርንሌይ ባለቀ ሰዓት በተቆጠረበት ጎሎች በማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ተሸንፏል።

ቡድኑ ባለፈው ዓመት ጥሩ የተከላካይ መስመር ያለው መሆኑን አስመስከሯል። ይህ ዘንድሮስ ይቀጥላል?

ፎረስት ከ 2 ለምንም መምራት በስዋንሲ ከካራባኦ ዋንጫ ውጭ ሆኗል።

አንጅ ፖስትኮግሉ ለዚህ ጨዋታ ሲሉ በርካታ ተጫዋቾችን አሳርፈዋል።

ግምት፡ 0 - 1

ዌስት ሃም ከ ክሪስታል ፓላስ

ዌስት ሃም በሜዳው መጫወቱ ይጎዳዋል እንጅ አይጠቅመውም። ይህንን ደጋግመን ተመልክተናል።

ችግር ሲፈጠር ባለቤቶቹ ቢተቹም በዝውውር መስኮቱ 120 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥተዋል። አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር ግን ቡድኑን ማሻሻል አልቻሉም።

ፓላስ የተጎዱትን ኢስማኤሊያ ሳር እና አዳም ዋርተንን ባያሳለፍም በደንብ የተዋሃደ ቡድን አለው።

ግምት፡ 0 - 1

ዎልቭስ ከ ሊድስ

ዎልቭስ በአራቱም ጨዋታዎች ቢሸነፍም አስልጣኝ ቺቶር ፔሬራ አዲስ ኮንትራት ሊቀርብላቸው ነው።

ሆኖም በቀጣይ አራት ጨዋታዎች ከተሸነፉ ሊባረሩ ይችላሉ።

ሊድስ ከሜዳው ውጭ ነጥብ አላገኘም፤ ጎልም አላስቆጠረም።

ዎልቭስ አጥቂው የርገን ስትራንድ ላርሰን በጉዳት ባይሰለፈም ጨዋታውን የሚያሸንፍ ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 - 0

ዩናይትድ ከቼልሲ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ

ፖል ስኮልስ ዩናይትድ ቡድኑን የሚመጥን አማካይ የለውም ሲል ተደምጧል።

የሩበን አሞሪም 3-4-3 አሰላልፍ በየሳምንቱ ውጤት ባያመጣ እንኳን የተሻለ አጨዋወት ሊያሳይ ቢገባውም ሁለቱም አልሆነም።

በአንዳንድ ጨዋታዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢኖራቸውም ምን ተጠቀሙበት? ወደ ማሸነፍ ሊመለሱ ይገባል።

ዩናይትድ በአውሮፓ መድረኮች አለመሳተፉ ለሊጉ ጨዋታ ዝግጅት ትልቅ ዕድል ፈጥሮለታል።

ቼልሲ ጥሩ ደረጃ ላይ ባይደርስም ጥሩ ለመንቀሳቀስ እየሞከረ ነው።

ኮል ፓልመር ወደ ድንቅ አቋሙ እየተመለሰ ይገኛል።

ግምት፡ 1 - 2

ፉልሃም ከ ብሬንትፎርድ

ይህ ለመገመት የሚከብድ መርሃ ግብር ነው።

ብሬንትፎርድ በመልሶ ማጥቃት ሚጫወት ቡድን ሆኗል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ሁለቱንም ጨዋታዎች ፉልሃም በማሸነፉ አሁንም ግምቴን ለእነሱ እሰጣለሁ።

ግምት፡ 2 - 1

እሑድ

ቦርንመዝ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

ይህን ጨዋታ ለመገመት ከባድ ቢሆንም ዕድሉን ለቦርንመዝ አሰጣለሁ።

ቡድኑ በመከላከል እና በማጥቃት እንቅስቃሴው አስገርሞኛል።

ኒውካስል ባለፈው ሳምንት ዎልቭስን ቢያሽንፍም አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ወደ ቪታሊቲ ስታዲየም ሄደው ከኒውካስል ጋር ድል አይቀናቸውም።

ግምት፡ 2 - 1

ሰንደርላንድ ከ አስቶን ቪላ

ሰንደርላንድ ውጤት ከራቀው አስቶን ቪላ ጋር ተጫውቶም ያሸንፋል የሚል እምነት የለኝም።

ቪላ የመጀመሪያ ጎሉን ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ ድሉንም የሚያስመዘግብበት ጨዋታ ይሆናል።

ግምት፡ 0 - 2

አርሰናል ከቼልሲ

አርሰናል ከ ማንቸስተር ሲቲ

ስለዚህ ጨዋታ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ - አርሰናል ያሸንፋል።

ሲቲ ባለፈው ሳምንት ዩናይትድን ቢያሽንፍም ያሸነፈው ደካማውን ማንቸስተር ዩናይትድን ነው። አርሰናል ደግሞ ሌላ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሲቲ ላይ የበላይነታቸውን ከማሳየታቸውም በላይ ኧርሊንግ ሃላንድን መፈናፈኛ ያሳጡታል።

ግምት፡ 1 - 0