ቼልሲ ከሊቨርፑል እና የሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ኤንዞ ፈርናንዴዝ እና ሞ ሳላህ

ሊቨርፑል ሁለት ጨዋታዎችን በተከታታይ ተሸንፏል።

"የአርን ስሎት የተከላካይ መስመር ክፍተት አለበት" ይላል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን።

ቀጣዩ ተጋጣሚያቸው ቼልሲ መሆኑ እና ግብ ጠባቂው አሊሰን በጉዳት ከሜዳ መራቁ የቡድኑን ተጋላጭነት ይጨምረዋል።

ይህንን ጨምሮ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሑድ የሚካሄዱትን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሱተን እንደሚከተለው ገምቷል።

አርብ

በርንመዝ ከ ፉልሃም

ፉልሃም ባለፈው ሳምንት በአስቶን ቪላ ጥሩ አጀማመር ቢኖረውም በጨዋታው ተሸንፏል።

የ18 ዓመቱ ጆሽ ኪንግ ድንቅ ተጫዋች መሆኑን ያስመሰከረበት ጨዋታም ነበር።

በርንመዝ ደግሞ ከሊድስ ጋር አቻ ተለያይቷል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በርንመዝ ነው ይህንን ጨዋታ ያሸነፈው።

ግምት፡ 1 - 0

ቅዳሜ

ሊድስ ከ ቶተንሃም

ሊድስ እስካሁን ድረስ ካስደነቁኝ ቡድኖች አንዱ ነው።

ቡድኑ ሚዛኑን የጠበቀ ነው። በአርሰናል ከተሸነፈበት ጨዋታ በስተቀር በሌሎቹ ጨዋታዎች ላይ ተፎካካሪ መሆኑን አሳይቷል።

ቶተንሃም በበኩሉ በፕሪሚየር ሊጉ ከዎልቭስ እንዲሁም በሻምፒዮንስ ሊግ ከቦዶ/ግሊምት ጋር አቻ ተለያይቷል።

ይህ ጨዋታም በተመሳሳይ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 - 1

አርሰናል ከ ዌስት ሃም

አርሰናል ከ ዌስት ሃም

ባለፉት ሁለት የኤምሬትስ ጨዋታዎች ዌስትሃም ማሸነፍ ቢችልም አሁን ግን መድፈኞቹ ነጥብ የሚጥሉ አይመስልም።

በመጀመሪያው የኑኖ እስፕሪንቶ ሳንቶስ ጨዋታ ዌስት ሃም ከኤቨርተን ጋር ለመፎካከር ቢችልም አርሰናል ግን ይከብዳቸዋል።

አርሰናል ጠንካራ ከመሆኑም በላይ የቡድን ጥልቀቱም አስተማማኝ ነው።

ግምት፡ 3 - 0

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሰንደርላንድ

ሰንደርላንድ በደንብ የተደራጀ ቡድን ከመሆኑም በላይ አስደናቂ ጉዞ እያደረገ ነው።

ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ ዝብርቅርቅ እንዳለ ነው።

ምንም እንኳን ሩበን አሞሪም ቢተቹም ባለፈው ሳምንት የተቆጠሩባቸው ጎሎች በተጫዋቾች ስህትት ነው።

በዚህ ጨዋታ ሰንደርላንድ ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ። አሞሪም ውጤት ቢቀናቸው እንኳ ቡድኑ በአሰልጣኙ ስር መሻሻል አያሳይም።

ግምት፡ 0 - 1

ቼልሲ ከ ሊቨርፑል

ቼልሲ ከ ሊቨርፑል

ቼልሲ በሊጉ በማንቸስተር ዩናይትድ እና በብራይተን ተከታታይ ሽንፈቶችን አስተናግዷል።

እንዳለፉት ጨዋታዎች በቀይ ተጫዋቾቹን የማያጣ ከሆነ ሊቨርፑልን ይፈትነዋል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ቢመስለኝም ትልቅ ጨዋታ እንደመሆኑን አንዱን ቡድን ለመምረጥ ወስኛለሁ።

አርን ስሎት ቡድን ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናግዳል።

ግምት፡ 2 - 1

እሑድ

አስቶን ቪላ ከ በርንሌይ

ቪላ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ የሊግ ድሉን ፉልሃምን በማሸነፍ አስመዝገቧል።

ቡድኑ በሳምንቱ አጋማሽ በዩሮፓ ሊግ ላይ በመሳተፉ ጫናው ይበረታበታል።

በርንሌይ ባለፈው ሳምንት 5 ለ 1 ቢሸነፍም ማንቸስተር ሲቲን ሲፈትኑ አምሽተዋል። ከሊቨርፑል ጋርም ጥሩ ተፎካካሪ ነበሩ።

ግምት፡ 1 - 1

ኤቨርተን ከ ክሪስታል ፓላስ

ኤቨርተን በአዲሱ ሜዳው እስካሁን ሽንፈት ያላስተናገደ ቢሆንም ከሦስት ጨዋታዎች በሁሉቱ አቻ ተለያይቷል።

ይህ በሁለት ጥሩ አሰልጣኞች መካከል የሚደረግ ጨዋታ ስለሚደረግ ጥሩ ጨዋታ ይሆናል።

ኦሊቨር ጋልስነር ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል ጋር እንዳደረጉት ቀጥተኛ አጨዋወትን ከመረጡ ይጠቀማሉ።

ኤቨርተን በተለይም ጃክ ግሪሊሽ ድንቅ ቢሆንም አጥቂ መስመሩ ጎሎችን እያስቆጠረ አይደለም።

ግምት፡ 0 - 1

ኒውካስል ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ኒውካስል በሊጉ ብዙ ጎሎችን ባያስቆጥርም በሳምንቱ አጋማሽ ቤልጂም ላይ አራት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ቡድኑ በሜዳው የተሸነፈው በአርሰናል እና በሊቨርፑል ብቻ ነው።

ጨዋታው ክፍት ስለሚሆን ብዙ ዕድሎችን እንደሚኣገኙ ተስፋ አድርጋለሁ።

አንጀ ፖስትኮግሉ መጀመሪያ ጨዋታቸውን ለማሸነፍ አሁንም ለመጠበቅ የሚገደዱ ይሆናል።

ግምት፡ 3 - 1

ዎልቭስ ከ ብራይተን

ዎልቭስ በሜዳው ሦስት ጨዋታዎችን ተሸንፏል። እህ ግን በመቀጠል አይኖርበትም።

ብራይትን ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋቾች ከተጫወተው ቼልሲ ጋር ጥሩ ቢንቀሳቀስም ቡድኑን ለመገመት ይከብዳል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ቢችልም ሊያሽንፍ ሚችለውን ቡድን ገምቻለሁ።

ግምት፡ 1 - 2

ብሬንትፎርድ ከ ማንቸስተር ሲቲ

ብሬንትፎርድ ከ ማንቸስተር ሲቲ

ብሬንትፎርድ በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት የሚመርጥ ይመስላል።

ማንቸስተር ሲቲ በስድስት ጨዋታዎች ባይሸነፍም እስካሁን አሳማኝ መሆን አልቻለም።

ፊል ፎደን ወደ ድንቅ ብቃቱ ተመልሷል። ሃላንድ ደግሞ ኳስን እና በማገናኘት ላይ ነው።

ሲቲ የአማካይ ክፍሉ ክፍተት ያለበት ሲሆን የቀኝ መስመሩም ጥያቄ ይነሳበታል።

ግምት፡ 1 - 2