ጭምቅ ሃሳቦች
- እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት የአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ሳኢድ ኢዛዲ መገደላቸውን የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ማረጋገጡን የአገሪቱ ሚዲያ ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።
- የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን ከአሜሪካ ጥቃት በፊት የበለጸገ የዩራኒየም ክምችቷን ከፎርዶ የኒውክሌር ጣቢያ አዛውራለች የሚለውን ሪፖርት አስተባበሉ።
- በኳታር የአሜሪካ የጦር ሰፈርን ለመከላከል የቀሩት 44 ወታደሮች ብቻ እንደነበሩ አሜሪካ ገለጸች
- አሜሪካ 'ኦፕሬሽን ሚድናይት ሐመር' በሚል ስያሜ በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃት ለ15 ዓመታት የታቀደበት እንደሆነ የአገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ዳን ኬይን ገለጹ።
- በኢራን ላይ የተፈጸመው "የተሳካ ታሪካዊ ጥቃት ነበር" ሲሉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ገለጹ
- አሜሪካ በኢራን የፈጸመችው ጥቃት ኢራንን እጅ የማሰጠት እንጂ በጭራሽ ከኒውክሌር ማበልጸግ ጋር ፍጹም ግንኙነት እንደሌለው የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኻሜኒ ተናገሩ
- ትራምፕ፤ የአሜሪካ ጥቃት የኢራን ኒውክሌር ይዞታዎችን አላወደመም የሚለውን የደህንነት ግምገማ ውድቅ አደረጉ
- የአሜሪካ ጥቃት የኢራን ኒውክሌር ይዞታዎችን እንዳላወደመ የደህንነት ግምገማ አሳየ








