ሩሲያ ከዩክሬን ‘የወሰደችውን’ እህል ለገበያ እያቀረበች ነው?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሩሲያ ከዩክሬን እህል ክምችት ወደ ባህርማዶ እየላከች ነው ሲሉ በሩሲያ የተሾሙት የደቡብ ዩክሬን ባለስልጣናት ተናገሩ።
ቢቢሲ ይህንን ማረጋገጥ ባይቻለውም የዩክሬን ባለስልጣናት ሩሲያ ወደ 600 ሺህ ቶን እህል ሰርቃ የተወሰነውን ወደ ውጭ ትልካለች ሲሉ ይከሳሉ።
ሩሲያ እህል እየሰረቀች ነው መባሏን አስተባብላለች።
የዩክሬን ለሽያጭ ያከማቸችውን እህል ማግኘት በአለምአቀፍ ደረጃ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል።
ቀደም ባለው ጊዜ ቢሆን በሚሊዮን የሚቆጠር ቶን በየዓመቱ ወደ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ይላካል።
አሁን ግን ይህ የሚቻል አይደለም። ምክንያት ከተባለ የሩስያ የባህር ሃይል የዩክሬን ጥቁር ባህር ወደቦችን በመዝጋቱ ነው።
ዩክሬን በጥቁር ባህር ዳርቻ የሚገኙ ፈንጂዎችን ካላጸዳች ሥራው የሚሳካ አይደለም ትላለች ሩሲያ።
ኒው ዮርክ ታይምስ ደግሞ ነገሩ ወዲህ ነው ይላል።
ሩሲያ የተሰረቀውን የዩክሬን ስንዴ በድርቅ ለተጎዱ የአፍሪካ ሃገራት ለመሸጥእየጣረች ነው ስትል አሜሪካ ማስታወቋን ዘግቧል።
በግንቦትወር አጋማሽ አሜሪካ ለ14 ሃገራት (አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት ናቸው) ማስጠንቀቂያ ልካ ነበር።
የሩሲያ ጭነት መርከቦች ከዩክሬን አቅራቢያወደቦች በእህል ተሞልተው ጉዞ መጀመራቸውን አሳውቋል ሲል ጋዜጣው የውጭ ጉዳይ ዲፓርትመንት መረጃን ጠቅሶ ዘግቧል።
ሩሲያ ምን ትላለች?
በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትገኘው የዛፖሪዥያ ግዛት አስተዳዳሪ የሆኑት ይባሊትስኪ በጭነት ባቡሮች እህሉ ወደ ክሬሚያ አቅንቷል ብለዋል። እአአ በ2014 በሃይል ከተቆጣጠረቻት ክሬሚያ ደግሞ ወደ መካከለኛው ምስራቅ።
ለሩሲያ የመንግሥት ቴሌቪዥን "ዋናዎቹ ስምምነቶች ከቱርክ ጋር እየተጠናቀቁ ናቸው" ሲሉ ዝርዝሩን ሳይገልጡ አልፈዋል።
ክሬሚያ የሚገኘው የሩሲያ ቃል አቀባይ ኦሌግ ክሪችኮቭ በእህል የተሞሉ 11 ፉርጎዎች እህል ከዛፖሪዥያዋ ሜሊቶፖል ከተማ ክሬሚያ መግባቱንተናግረዋል።
ከሩሲያመንግስት የዜና ወኪል ሪያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ደግሞ ከኬርሰን ግዛትም እህል እየተጓጓዘ ነው ብለዋል።
ቢቢሲአስተያየት እንዲሰጠው የሩሲያ ባለስልጣናትን አነጋግሯል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከቱርኩ አቻቸው ሜቭሉት ካቩሶግሉ ጋር በአንካራ ተወያይተዋል። በእህል አቅርቦት ችግር ዙሪያ ረቡዕ ያደረጉት ውይይት ፍሬ አላፈራም።
ላቭሮቭ ሃገራቸው የዩክሬንን የስንዴ ወጪ ንግድ እያደናቀፈች ነው መባሉን አስተባብለዋል። ኃላፊነት ያለባት ግዳጁ ዩክሬን በመሆኗ ከኦዴሳ እና ሌሎች ወደቦች ዙሪያ ያለውን አካባቢ የተጠንቀቅ ጦር ማንሳት አለባት ብለዋል።
የዩክሬንየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዩክሬን በባህር ዳርቻዎቿ ያሉትን የተጠንቀቅ ጦር ማንሳት አትችልም ብለዋል። ሩሲያ "ደቡባዊ ዩክሬንን ለማጥቃት የእህል መተላለፊያ ኮሪደሮችን ትጠቀማለች" የሚል ነው ምክንያታቸው።
ሩሲያ ለተፈጠረው ምግብ ቀውስ ሌላም ምክንያት ታቀርባለች የምዕራባዊያንን ማዕቀቦች። ምዕራቡ ዓለም ደግሞ ሩሲያ የእህል አቅርቦቱን “እንደ ጦር መሣሪያ ትጠቅማለች” ይላሉ።
ቱርክ ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር መስመሮቸን የሚፈጥር ስምምነት ለመድረስ ደፋ ቀና እያለች ነው።
ዩክሬናውያንስ ምን ይላሉ?
በቱርክየ ዩክሬን አምባሳደር ቫሲል ቦድናር ባለፈው ሳምንት ሩሲያ ከክሬሚያ የተሰረቀ እህል እያጓጓዘች ነው ብለዋል። ከመዳረሻዎቹ አንዷ ደግሞ ራሷ ቱርክ ናት።
"ቱርክ እንድትረዳን ጥሪያችንን አቅርበናል። በቱርክ በኩል በቀረበው ምክረ ሃሳብ መሰረት እህሉን በሚሰርቁ እና በሚሸጡት ላይ የወንጀል ክስ እየጀመርን ነው" ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የዩክሬን እህል ማህበር ኃላፊ ማይኮላ ጎርባቾቭ ችግሩ የከፋ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ከዩክሬን ወደቦች መነሳት ካልቻሉ ሰኔ መጨረሻ የሚጀምረው የሚቀጥለው የመኸር ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል ።
ዩክሬን በሚቀጥለው ዓመት ወደ ውጭ የምትልከው እህል 20 ሚሊዮን ቶን ይሆናል። ባለፈውዓመት 44.7 ሚሊዮን ቶን ወደ ውጭ መላኩን ልብ ማለት ይገባል።
ይህ ለምን አንገብጋቢ ዓለም አቀፍ ጉዳይ ሆነ?
ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዋጋ ንረት አስከትሏል። የእህል፣ የምግብዘይት፣ የነዳጅ እና ማዳበሪያ ዋጋ አልቀመስ ብሏል። የተወሰነው የምዕራቡ ዓለም በሩሲያ ላይ የጣለው ማዕቀብ መዘዝ ነው።
ሩሲያ እና ዩክሬን ከዓለም አቀፍ የስንዴ ገበያ አንድ ሦስተኛ የሚጠጋውን ይሸፍናሉ። የዩክሬን ድርሻ ለብቻ ካየነው ወደ 10 በመቶ ይጠጋል።
ከዓለም አቀፉ የበቆሎ ገበያ ደግሞ የዩክሬን ድርሻ 16 በመቶ ነው። እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሆነ 42 በመቶ የሱፍ አበባ ዘይትን ድርሻ ትሸፍናለች።
እህል ከዩክሬን እንዳይወጣ መከልከሉ እና አንዳንድ ሃገራት ደግሞ እህል በማከማቸት በመጠመዳቸው መጀመሪያም ቋፍ ላይ የነበሩ አንዳንድ ሃገራትን ጫና ከፍ አድርጓል።
በሶማሊያየ ዓለም ምግብፕሮግራም ባልደረባ የሆኑት ፔትሮክ ዊልተን በአፍሪካ ቀንድ ያለው ድርቅ ከወዲሁ አስከፊ እየሆነ ነው ብለዋል።
"ለአራት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ዝናብ አልነበረም። አሥራ አምስት ሚሊዮን የተራቡ ሰዎች ያሉ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ ቁጥሩ ወደ 20 ሚሊዮን ያድጋል" ብለዋል።












