'ፍሬንድስ' ከ15 ዓመት በኋላ እንደ አዲስ ሊሠራ ነው

የፎቶው ባለመብት, Channel 4 publicity
'ፍሬንድስ' ተከታታይ የቴሌቭዥን ፊልም መታየት ካቆመ ከ15 ዓመት በኋላ በድጋሚ ሊሠራ መሆኑ ተገለፀ። የፍሬንድስ ገፀ ባህሪያት በኤችቢኦ ማክስ በኩል በልዩ ዝግጅትና በአዳዲስ ትዕይንቶች እንደሚቀርቡ ታውቋል።
እያንዳንዱ ነባር ተዋናይ እያንዳንዱን ክፍል ፕሮዲውስ የማድረግ እድል እንደሚያገኝ ማወቅ ተችሏል።
በመጪው ግንቦት ወር ኤችቢኦ ማክስ (HBO Max) ለኦንላየን ተጠቃሚዎቹ ማስተላለፍ ይጀምራል የተባለው ይህ ተከታታይ ድራማ፤ እርግጠኛ መተላለፍ የሚጀምርበት ቀን ግን ይህ ነው ተብሎ አልተቀመጠም።
ጄኔፈር አኒስተን፣ ኮርትኒ ኮክስ፣ ሊዛ ኩድሮው፣ ማት ሌብላንክ፣ ማቲው ፔሪ እንዲሁም ዴቪድ ሺዊመር በድራማው ላይ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል።
ፔሪ በኢንስታግራም ገፁ ላይ "መሆኑ እግርጥ ነው" በማለት ገፀ ባህሪያቱ በ1990 የተነሱትን ምስል አጋርቷል። ከዚህ መልዕክት በኋላም ሌሎቹ ገፀ ባህሪያት ይህንኑ መልዕክት ሲቀባበሉትና ሲያጋሩት ታይቷል።
ይህ ጽሑፍ በInstagram. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የInstagram ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ Instagram ይዘት መጨረሻ
ፍሬንድስ እኤአ ከ1994 እስከ 2004 ድረስ በቴሌቪዥን የታየ ሲሆን፤ የመጨረሻው ክፍል በአሜሪካ ብቻ በ52.5 ሚሊየን ተመልካቾች በመታየት በ2000 ከታዩ የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች ሁሉ ቀዳሚነቱን ይዟል።
ይህ ተከታታይ ድራማ በቅርቡም በኔትፍሊክስ ላይ መታየት ጀምሮ የዘመኑን ወጣት ተመልካቾች ትኩረት መሳብ ችሎ ነበር።
በዚህም የተነሳ በዩናይትድ ኪንግደም ተመራጭ ሲሆን በአሜሪካ ደግሞ ኔትፍሊክስ በ2018 በአሜሪካ ካቀረባቸው የተለያዩ መሰናዶዎች ሁሉ በልጦ ተወዳጅነት ማግኘቱ ታውቋል።
የፍሬንድስ ተዋንያን ዳግመኛ ሊሰባሰቡ ነው የሚለው ወሬ መናፈስ የጀመረው ጄኔፈር አኒስተን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በኢኒስታግራም አካውንቷ ተዋንያኑ በአንድ ላይ ተሰባስበው የተነሱትን ምስል ከለጠፈች በኋላ ነበር።
በአሁን ሰዓት ኤችቢኦ ማክስ የድራማውን መብት እንዲሁም የከዚህ በፊት ቅጂዎችን በአጠቃላይ በ425 ሚሊየን ዶላር ገዝቶታል።
እያንዳንዱ ተዋንያን በዚህ አዲስ ሥራ ላይ በመሳተፉ ብቻ 2.5 ሚሊየን ዶላር ክፍያ እንደሚያገኝ ታውቋል።
የድራማው አድናቂዎች ዜናውን እንደሰሙ ደስታቸውን በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ገልፀዋል።
ኤችቢኦ ማክስ እንደ ኔትፍሊክስ በኢንተርኔት የተለያዩ ትርዒቶችንና ድራማዎችን መከታተል የሚያስችል መተግበሪያ በቅርቡ ያስተዋውቃል ተብሏል።















