በማንተጋፍቶት ስለሺ ተፅፎ የተዘጋጀው ግርታ ፊልም በቅርቡ በቤልጂየም በተዘጋጀ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ላይ አሸናፊ ሆኗል።
በማንተጋፍቶት ስለሺ ተፅፎ የተሰናዳው ግርታ ፊልም በቅርቡ በቤልጂየም በተዘጋጀ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ላይ አሸናፊ ሆኗል። የ8 ደቂቃ ርዝመት ያለው ፊልም በአለም አቀፍ እና በአህጉር አቀፍ መድረኮች ድል ሲቀናው የመጀመሪያው አይደለም ።ከ50 በላይ ፊልሞች ለዕይታ በቀረበቡት የአሁኑ ፌስቲቫል ላይ ‘ግርታ’ አንደኛ የሆነው ፣የኦስካር ሸልማት የመጨረሻ ዙር ዕጩ የነበረውን የኬንያ እና ጀርመን ባለሙያዎች ጥምረት የታየበትን ‘ዋቱ ዋቴ’ ፊልም በመቅደም ነው።ከፊልሙ ፀሃፊ እና አሰናጅ ጋር የተደረገውን አጭር ቆይታ ያዳምጡ።