ቢዮንሴ በህንድ ለቱጃር ልጅ ለሆነችው አምባኒ ፒራማል ሰርግ ዘፈነች

የፎቶው ባለመብት, Instagram/Beyonce
አሜሪካዊቷ ዘፋኝ ቢዮንሴ በህንድ ታዋቂ ለሆነው ቱጃር ሙኬሽ አምባኒ ሰርግ ላይ መዝፈኗ ተዘግቧል።
በህንድ የናጠጠ ሃብታም ልጅ የሆነችው ኢሻ አምባኒ ከህንዳዊው ቢሊዮነር ልጅ አናንድ ፒራማል ጋር በዚህ ሳምንት ትጋባለች።
ለሰርጉ ከመጡት ታዋቂ ሰዎች መካከል ቢዮንሴ አንዷ ስትሆን ሂላሪ ክሊንተንም ከሰርጉ በፊት ያለውን ዝግጅት እንደታደሙ ተገልጿል።
በባለፈው ሳምንት ሙሽራዋ የታዋቂዋ ተዋናይት ፕሪያንካ ቾፕራና አሜሪካዊው ዘፋኝ ኒክ ጆናስ ሰርግ ላይ ሚዜ ነበረች።
ይህ ጽሑፍ በInstagram. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የInstagram ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ Instagram ይዘት መጨረሻ

ይህ ቅንጡ መሆኑ የተዘገበለት ሰርግ ለረቡዕ የተቆረጠ ሲሆን ቅድመ ዝግጅቱ ግን ቅዳሜና እሁድ እንደተጀመረም ተገልጿል።
የተቀናጣና የደመቀ ሰርግ ይሆናል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ሰርግ ላይ በአሜሪካ የፕሬዚዳንትነት ዕጩ የነበሩት ሂላሪ ክሊንተንን ጨምሮ ታዋቂዋ የሚዲያ ግለሰብ አሪያና ሃፊንግተን ሰርጉን ይታደማሉ።
ሚዲያዎች እንደዘገቡት እንግዶቹን ለማመላለስም 100 የሚሆኑ የግል አውሮፕላኖች እንደተመደቡ ነው።
ታዋቂ ጦማሪዎች፣ የመዝናኛ ፀሐፊዎች ስለ ፌስቲቫሉ በኢንስታግራም ላይ እየፃፉም እንደሆነ ተገልጿል።
ቢዮንሴ ከሰርጉ በፊት እሁድ እለት ሳንጌት ተብሎ በሚጠራው ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ስራዎቿን ያቀረበች ሲሆን፤ ፎቶዎቿንም በኢንስታግራም አጋርታለች።
ለዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ምን ያህል እንደተከፈላት ግልፅ ባይሆንም፤ የሙሽራዋ አባት ሙከሺ አምባኒ 47 ቢሊዮን ዶላር አንጡራ ኃብት እንዳላቸው ተዘግቧል።












