የነጻነት ቅርጫት: መወልወያ

የቤት ውስጥ ስራ፤ በተለየ መልኩ ደግሞ የቤት ውስጥ የጽዳት ሥራዎች ለሴቶች ብቻ የተተዉ ተግባራት ተደርገው ይወሰዳሉ።
በበርካታ ሃገራት ከወንዶች በላይ ሴቶች የቤት ውስጥ ሥራ የሙሉ ሰዓት ወይም ከስራ በኋላ የሚጠብቃቸው ሌላኛው ኃላፊነታቸው ነው።
የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፤ ባደጉት ሃገራት ተከፍሏቸውም ይሁን ሳይከፈላቸው ሴቶች ከወንዶች በላይ በየቀኑ ለተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ሥራ ላይ ይቆያሉ። እያደጉ ባሉ ሃገራት ደግሞ ሴቶች ከወንዶች በላይ ለተጨማሪ 50 ደቂቃዎች በየቀኑ በሥራ ያሳልፋሉ።











