የዶናልድ ትራምፕ ሕይወት በምሥሎች

ትራምፕ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የዶናልድ ትራምፕ ሕይወት በምሥሎች
ትራምፕ ስልክ እያወሩ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ዶናልድ ጆን ትራምፕ ኒው ዮርክ ውስጥ በምትገኘው ኩዊንስ በምትባል አካባቢ በአውሮፓውያኑ ሰኔ 14/1946 ነበር የተወለዱት።

ወላጆቻቸው ካሏቸው ሦስት ወንዶች እና ሁለት ሴት ልጆች መካከል አራተኛው ናቸው። ወንድሞቻቸው ፍሬድ ጁኒየር እና ሮበርት እንዲሁም እህቶቻቸው ማሪያን እና ኤልዛቤት የሚባሉ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በሕይወት ያሉት እህታቸው ኤልዛቤት ብቻ ናቸው።

አባታቸው ፍሬድ እዚያው ኒው ዮርክ ውስጥ ስኬታማ የግንባታ ተቋም ባለቤት ነበሩ። ትራምፕ በ1968 ለመጀመሪያ ጊዜ የሥራውን ዓለም ከተቀላቀሉ በኋላ፣ ብዙም ሳይቆዩ በመሃል ማንሃተን ውስጥ ራሳቸውን ችለው መሥራት ጀመሩ።

ዶናልድ ትራምፕ ከአባታቸው ፍሬድ ጋር ኒውዮርክ ውስጥ

የፎቶው ባለመብት, New York Daily News Archive/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዶናልድ ትራምፕ ከአባታቸው ፍሬድ ጋር ኒውዮርክ ውስጥ
ዶናልድ ትራምፕ ማንሃተን በሚገኘው ትራምፕ ፕላዛ በተባለው ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው ቢሯቸው ውስጥ ስልክ ሲያናግሩ 1987

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዶናልድ ትራምፕ ማንሃተን በሚገኘው 'ትራምፕ ፕላዛ' በተባለው ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው ቢሯቸው ውስጥ ስልክ ሲያናግሩ-1987
ዶናልድ ትራምፕ ኒው ጀርሲ አትላንቲክ ሲቲ ውስጥ የሚገኝ የካዚኖ ቤት ምረቃ ላይ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዶናልድ ትራምፕ ኒው ጀርሲ አትላንቲክ ሲቲ ውስጥ የሚገኝ የካዚኖ ቤት ምረቃ ላይ

ትራምፕ የካዚኖ ማጨወቻዎች፣ ኮንዶሚኒየሞች፣ የጎልፍ መስኮች እና ሆቴሎችን በባለቤትነት በመያዝ ሀብታቸው በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ ከመስፋፋቱ በተጨማሪ ሥራውን ወደ ሕንድ፣ቱርክ እና ፊሊፒንስ አስፋፍተዋል።

ባላቸው ዘናጭ እና ትኩረት የሚስብ የሕይወት ዘይቤ ምክንያት ትራምፕ በኒውዮርክ የንግዱ ዘርፍ ጎልተው እንዲታዩ ከማድረጉ በተጨማሪ በመዝናኛው ዓለም ‘ዘ አፕሬንቲስ’ የተባለ የቴሌቪዥን ትርዒት በማቅረብ ዝነኛ ሆኑ።

ዶናልድ ትራምፕ በመኖርያ ቤታቸው ውስጥ ቀይ ሸሚዝ፣ በነጭ ኮት ለብሰው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ዶናልድ ትራምፕ በኒውዮርክ በመንትዮቹ ሕንጻ ላይ በሂሊኮፕተር እየበረሩ ጋዜጣ ሲያነቡ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ዶናልድ ትራምፕ ከወንድ ልጃቸው ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር እና ከሴት ልጃቸው ኢቫንካ ትራምፕ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዶናልድ ትራምፕ ከወንድ ልጃቸው ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር እና ከሴት ልጃቸው ኢቫንካ ትራምፕ

ሦስት ጊዜ ጋብቻ የመሠረቱት ትራምፕ አምስት ልጆች አባት ናቸው። የመጀመሪያ የጋብቻ ቀለበታቸውን ያሰሩት ከኢቫና ዜሌኒኮቫ ጋር በአውሮፓውያኑ 1977 ነው።

ዶናልድ ትራምፕ ከመጀመሪያ ሚስታቸው ኢቫና ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዶናልድ ትራምፕ ከመጀመሪያ ሚስታቸው ኢቫና ጋር
ዶናልድ ትራምፕ ከአሁኗ ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዶናልድ ትራምፕ ከአሁኗ ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ ጋር

ትራምፕ ሦስተኛ ሚስታቸው የሆነችውን ሜላኒያ ናውስን የተዋወቁት ከ20 ዓመት በፊት ሲሆን፣ ከመጋባታቸው ሰባት ዓመት በፊት ሲገናኙ ትራምፕ 52 ሜላኒያ ደግሞ 28 ዓመታቸው ነበር።

የትራምፕ የፖለቲካ ሕይወት የጀመረው በአውሮፓውያኑ 2015 በቤተሰቦቻቸው ተከበው ትራምፕ ታወር በተባለው ሕንጻ ውስጥ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ሲያሳውቁ ነበረ።

ትራምፕ የምርጫ መቀስቀሻ መፈክራቸው “አሜሪካንን እንደገና ታላቅ ማድረግ” (Make America great again) የሚል ነው።

ትራምፕ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ይፋ ያደረጉበት ጋዜጣዊ መግለጫ

የፎቶው ባለመብት, Bloomberg/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ይፋ ያደረጉበት ጋዜጣዊ መግለጫ
ትራምፕ ለመጀመሪያው ዙር ምርጫ ዕጩነታቸውን በተቀበሉበት ወቅት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ለመጀመሪያው ዙር ምርጫ ዕጩነታቸውን በተቀበሉበት ወቅት
ዶናልድ ትራምፕ እና ሂላሪ ክሊንተን ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በተፎካከሩበት ወቅት ክርክር ካደረጉ በኋላ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዶናልድ ትራምፕ እና ሂላሪ ክሊንተን ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በተፎካከሩበት ወቅት ክርክር ካደረጉ በኋላ

ከስምንት ዓመታት በፊት በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት ትረምፕ እና ሂላሪ ክሊንተን ዕጩዎች ነበሩ። ሁለቱ ዕጩዎች ለመመረጥ ከፍተኛ ፉክክር ከማድረጋቸው በተጨማሪ ውዝግብም ነበረው።

በመጨረሻም ትራምፕ ሂላሪን በመርታት 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን በአውሮፓውያኑ 2017 ቃለ መሐላ ፈጸሙ።

ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ዕለት ንግግር ለማድረግ ወደ መድረክ ሲያመሩ (2017)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ዕለት ንግግር ለማድረግ ወደ መድረክ ሲያመሩ (2017)
ትራምፕ ዋይት ሐውስ ውስጥ በሚገኘው ፕሬዝዳንታዊ ጽህፈት ቤታቸው

የፎቶው ባለመብት, Bloomberg/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ዋይት ሐውስ ውስጥ በሚገኘው ፕሬዝዳንታዊ ጽህፈት ቤታቸው

ከውጭ አገራት መሪዎች ጋር በይፋ በተደጋጋሚ ሲወዛገቡ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት የሥልጣን ዘመናቸው ለአሜሪካ ወዳጆች የተረጋጋ ወቅት አልነበረም።

ትራምፕ ዋነኛ ከሚባለው የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት አገራቸውን በማስወጣት ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ ገብተው ነበረ።

ትራምፕ ከቡድን 7 አገራት መሪዎች ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ከቡድን 7 አገራት መሪዎች ጋር
ከቀድሞዋ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ከቀድሞዋ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ጋር

ትራምፕ የሥልጣን ዘመናቸው የመጨረሻው ዓመት በኮቪድ ወረርሽኝ አያያዛቸው ምክንያት ከፍተኛ ትችት ውስጥ የቆዩበት ነበረ።

በሽታውን ተከትሎ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት ትራምፕ የኮሮና ቫይረስ ተግኝቶባቸው ከምርጫ ቅስቀሳው እረፍት እንዲወስዱ ተገደው ነበር።

ዶናልድ ትራምፕ በኮቪድ ተይዘው ከቆዩ በኋላ በዋይት ሐውስ በረንዳ ላይ ሆነው የፊት መሸፈኛ ጭምብላቸውን ሲያወልቁ

የፎቶው ባለመብት, Bloomberg/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዶናልድ ትራምፕ በኮቪድ ተይዘው ከቆዩ በኋላ በዋይት ሐውስ በረንዳ ላይ ሆነው የፊት መሸፈኛ ጭምብላቸውን ሲያወልቁ

በ2020 በተካሄደው ፕሬዝዳንታው ምርጫ ትራምፕ በጆ ባይደን ቢሸነፉም ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ምክንያት ውጤቱን አልቀበልም ብለው ነበር።

ደጋፊዎቻቸውም ዋሽንግተን ውስጥ የሚገኘውን የአገሪቱን ምክር ቤት እንዲወሩ ጥሪ አድርገው ከባድ ቀውስ ተከስቶ ነበር።

ተቃውሞው ተባብሶ ወደ ረብሻ ተቀይሮ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ትራምፕ በዕለቱ የፈጸሙት ተግባር ሁለት የወንጀል ክስ እንዲቀርብባቸው አድጓል።

በረብሻው ዕለት ትራምፕ ከደጋፊዎቻቸው ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በረብሻው ዕለት ትራምፕ ከደጋፊዎቻቸው ጋር
ፍንዳታ እና ቃጠሎ በካፒቶል ሕንጻ አካባቢ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ከረብሻው ጋር ተያይዞ የትራምፕ ደጋፊዎች ፍንዳታ እና ቃጠሎ በካፒቶል ሕንጻ አካባቢ ተከስቶ ነበር

በተለያዩ ምክንያቶች በቀረቡባቸው በርካታ ክሶች ምክንያት የትራምፕ ፖለቲካዊ ሕይወት ያበቃለት መስሎ የነበረ ቢሆንም፣ ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ አሳውቀው ወዲያው የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ሆነው በአሁኑ ምርጫ ቀረቡ።

ትራምፕ የአሁኑን የምርጫ ዘመቻቸውን የጀመሩት 91 ክሶች ቀርበውባቸው በፍርድ ቤት እየታዩ ባለበት ጊዜ ነው።

ትራምፕ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው በፖሊስ የተነሱት ፎቶ

የፎቶው ባለመብት, Handout/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ከአንድ ዓመት በፊት አትላንታ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው በፖሊስ የተነሱት ፎቶ

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ትራምፕ የማጭበርበር እና ምሥጢር እንዳታወጣ ለአንዲት የፊልም ተዋናይት በከፈሉት ገንዘብ ምክንያት ከቀረቡባቸው ክሶች መካከል በ34ቱ ጥፋተኛ ተባሉ።

የቀረቡባቸው ክሶች ያላገዷቸው ትራምፕ ዳግም በፕሬዝዳንትነት ለመመረጥ ቅስቀሳ እያካሄዱ ባለበት ወቅት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ፔንሲልቬኒያ ግዛት በትለር ከተማ ውስጥ በአንድ የ20 ዓመት ጎረምሳ ከተተኮሰባቸው ጥይት ለጥቂት ነበር የተረፉት።

ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላ የተነሱት ዝነኛ ፎቶ

የፎቶው ባለመብት, AP

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላ ደም ፊታቸው ላይ እየፈሰሰ የሚያሳይ ዝነኛ ፎቶ
ትራምፕ በጥይት የቆሰለ ቀኝ ጆሮቸውን በፋሻ ሸፍነው

የፎቶው ባለመብት, Bloomberg/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ በተተኮሰባቸው ጥይት የቆሰለ ቀኝ ጆሮቸውን በፋሻ ሸፍነው የምርጫ ዘመቻቸውን ቀጥለዋል

ትራምፕ በጥይት ከተመቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ በተካሄደው የሪፐብሊካን ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ላይ ተገኝተው የፓርቲው ዕጩ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰየሙ።

ትራምፕ ለሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን በዕጩነት የቀረቡበትን የአሁኑን ምርጫ የሚያሸንፉ ከሆነ በታሪክ በዕድሜ የገፉ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ይሆናሉ።

የሥልጣን ዘመናቸውን ሲያጠናቅቁ ዕድሜያቸው 82 ዓመት ይሆናል።

ትራምፕ ኒው ዮርክ በሚገኘው ትራምፕ ታወር ቢሯቸው ውስጥ

የፎቶው ባለመብት, The Washington Post/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ኒው ዮርክ በሚገኘው ትራምፕ ታወር ቢሯቸው ውስጥ