ከአርሰናልን ድል በኋላ ሊቨርፑል እና ሲቲ ከሜዳቸው ውጪ በሚያደርጉት ጨዋታ እንዴት ይሆናሉ?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አርሰናል በሜዳው ቼልሲን ያስተናገደበት ጨዋታ በመድፈኞቹ ከፍ ያለ የበላይነት ተጠናቋል።
መድፈኞቹ ትናንት ምሽት የምዕራብ ለንደኑን ቼልሲን 5 ለ 0 አሸንፈዋል።
አርሰናል ሊጉን በ77 ነጥብ እየመራ የሚገኝ ሲሆን፤ ሊቨርፑል አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው 74 ነጥብ ይዞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሲቲ ሁለት ቀሪ ጨዋታ እየቀረው 73 ነጥብ ይዟል።
ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት በመርሲ ሳይድ ደርቢ ወደ ኤቨርተን ተጉዞ ጨዋታውን ያደርጋል። ሲቲ ደግሞ ከብራይተን ጋር ከሜዳው ውጪ ነገ ሐሙስ ይጫወታል።
የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል?
ረቡዕ

ዎልቭስ ከ በርንመዝ
አሠልጣኝ ጋሪ ኦኒዬል ባለፈው ዓመት ያባረራቸውን በርንመዝን የሚበቀሉበት ዕድል የሚፈጥርላቸው ጨዋታ ነው።
ያለፉትን አምስት ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻሉት ዎልቭሶች በጥሩ አቋማቸው ላይ አይገኙም።
በርንመዞችም ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ባይችሉም ከዚህ ጨዋታ ባዶ እጃቸውን አይመለሱም።
ግምት፡ 1 – 1
ክሪስታል ፓላስ ከ ኒውካስል
ክሪስታል ፓላስ እሑድ ዕለት ዌስት ሃም ላይ ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል።
ኤበረቺ ኤዜ እና ማይክል ኦሊሴ ድንቅ ሆነው አምሽተዋል። ከዢን-ፊሊፔ ማቴታ ጋርም አስፈሪ የአጥቂ መስመር ፈጥረዋል።
ኒውካስል ከሰሞኑ ጥሩ እየሆነ ቢመጣም ጨዋታውን ክሪስታል ፓላስ ያሸንፋል።
ግምት፡ 2 – 1
ኤቨርተን ከ ሊቨርፑል
ሞሐመድ ሳላህን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾችን ቀይረው ወደ ሜዳ የገቡት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አሸንፈው ለመውጣት ችለዋል።
ኤቨርተኖች ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ ሙከራ ያደርጋሉ። ኖቲንግሃም ፎረስትን ባሸነፉበት ጨዋታም ብዙ የጎል ዕድሎችን በመፍጠር ረገድ ያለባቸው ችግር ታይቷል።
ሊቨርፑል በርካታ ጥንካራ ጎኖች ያሉት ሲሆን፣ ዕድሎቹን ከተጠቀመ የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታን ያሸንፋል።
ግምት፡ 1 – 2

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሼፊልድ ዩናይትድ
ማንቸስተር ዩናይትድ ይህንን ጨዋታ ያሸንፋል።
በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው ሼፊልድ ከዚህ ጨዋታ የሚጠብቀው ነገር ባለመኖሩ እና ያለጫና ስለሚጫወት ለማንቸስተር ከባድ ሊሆንበት ይችላል።
የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች በቀላሉ እናሸንፋለን ብለው መጠበቅ እንደሌለባቸው ከኮቨንተሪው ጨዋታ ተምረዋል።
ግምት፡ 2 – 0
ሐሙስ
ብራይተን ከ ማንቸስተር ሲቲ
የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋቾች ከፍተኛ ድካም ላይ ቢሆኑም ጠንካራ ተቀያሪ ተጫዋቾችን ይዘዋል።
ያለፈው ዓመት ብራይተን ለሲቲ ከባድ የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ ግን ይህ የሚሆን አይመስልም።
ሊጉን የሚመሩት ሲቲዎች በዚህ ወቅት ነጠብ መጣላቸው የሊጉን ዋንጫ ሊያሳጠቸው ስለሚችል ጫና ይኖርባቸዋል።
ግምት፡ 0 – 2












