በረመዳን ጸሎት ወቅት ኢማሙ ላይ ወጥታ በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ የሆነችው ድመት
አልጄሪያ ውስጥ በሚገኝ አንድ መስጂድ ምሽት ላይ የረመዳን ጸሎት በሚደረግበት ጊዜ አንዲት ድመት ጸሎቱን በሚመሩት ኢማም ላይ በድንገት ወጥታ ታይታለች።
ጸሎቱን የሚመሩት ኢማም ግን በድመቷ ድንገተኛ ድርጊት ሳይረበሹ የጸሎት ሥነ ሥርዓቱን መምራታቸውን ቀጥለዋል።
የጸሎት ሥነ ሥርዓቱ በቀጥታ ይተላለፍ ስለነበረ ድመቷ ኢማሙ ደረት ላይ ከዚያም ትከሻቸው ላይ ስትወጣ ብዙ ሕዝብ አይቷታል።
እንዲሁም ይህንን ክስተት የሚያሳየው ቪዲዮ በአጭሩ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በስፋት እየተዘዋወረ በኣለም ዙሪያ ሚሊዮኖች ተመልክተውታል።









