ሱዳን የነበሩት 'በመቶዎች የሚቆጠሩ' የቀድሞ የኮሎምቢያ ወታደሮች የት ደረሱ?

የሱዳን ጦር ሃይሎች ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጎን ተሰለፉ ኮሎምቢያዊያንን ማግኘቱን አስታውቋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሱዳናውያን ታጣቂዎች በእንጨት ሳጥን ላይ የተቆለሉ ሰነዶችን እያገላበጡ ነው።

በመሃል ክርስቲያን ሎምባና ሞንካዮ የሚል ስም ያለበት የኮሎምቢያ ፓስፖርት አገኙ። የግለሰቡ የትራንስፖርት ካርድ እና መታወቂያም አለ።

የልጅ በሚመስል የእጅ ጽሑፍ በስፓኒሽ የተጻፈ ደብዳቤም አብሮ አለ:። 'አንተ የእኔ ምርጥ አባት ነህ። እወድሃለሁ' የሚል ጽሑፍ ሰፍሮበታል።

ይህንን የሚያሳይ ቪዲዮ በብዙ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በቅርቡ ተጋርቶ ቢቢሲ ቬሪፋይ ተመልክቶታል። እነዚህ ቪዲዮዎች የትና መቼ እንደተቀረጹ ቢቢሲ በትክክል ማወቅ አልቻለም። በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ሰነዶች እውነተኛ ይመስላሉ።

ከቪዲዮዎቹ አንዱ ዘ ጆይንት ፎርስስ ኦፍ አርምድ ስትራግል (ጄኤፍኤኤስ) የተሰኘው ቡድን ካወጣው መግለጫ ጋር አብሮ ነው። ተሽከርካሪዎች "የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች ጭነው ከሊቢያ ወደ ዳርፉር ሲያቀኑ በጄኤፍኤኤስ መያዛቸውን ያትታል።

የሎምባና ሞንካዮ ሰነዶችን በማጣቀስም "በሱዳን ግጭት ውስጥ የውጭ ኃይሎች ተሳትፎ ደረጃን" ያሳያል ብሏል ጄኤፍኤኤስ።

ሎምባና ሞንካዮ መታወቂያ

የፎቶው ባለመብት, Captura de redes sociales

ሎምባና ሞንካዮ የት እንዳለ ወይም ስለመገደሉም ግልጽ አይደለም።

በሱዳን ጦር ሃይሎች (ኤስኤኤፍ) እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ውስጥ የተሳተፈ የኮሎምቢያ ቡድን አካል እንደሆነ ይገመታል ሲሉ የኮሎምቢያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች፣ የቢቢሲ ሙንዶ ምንጮች እና የኮሎምቢያ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

በሌላ አጋጣሚ ደግሞ እአአ ህዳር 29/2024 የኤስኤኤፍ ኃይሎች በዳርፉር በፈጸሙት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ከአርኤስኤፍ ጎን የተሰለፉ "22 የኮሎምቢያ ዜግነት ያላቸውን ቅጥረኞች ገድያለሁ" ብሏል።

'በመቶዎች የሚቆጠሩ' ኮሎምቢያውያን

የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ሚያዝያ 2023 ተጀመረ። ይህም በአህጉሪቱ አስከፊ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ ፈጥሯል። በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል።

በግጭቱ ውስጥ ስለተሳተፉት ኮሎምቢያውያን ቁጥር ምንም አይነት ይፋዊ መረጃ የለም። በሱዳን በርካታ የውጭ አገራት ዜጎች በጦርነቱ መሳተፋቸውን የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

ከሪፖርቶቹ መካከል ላሲላ ቫቺያ የተባለው መጽሔት ከ300 በላይ መሆናቸውን ገምቷል።

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "የተታለሉ ወጣቶቻችንን ለመመለስ መንገዶችን ይፈልግ" ሲሉ የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ ህዳር 27 ለሚዲያ ዘገባዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የኮሎምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎች ወደ አፍሪካ መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት እንደሚጓዙ እንደሚያውቅ አስታውቋል። "በዚህም አንዳንድ ወገኖቻችን በተራቀቁ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች መረቦች ተታልለው በመጓዝ በዓለም አቀፍ ግጭቶች ውስጥ እንደ ቅጥረኛ ሆነው ይሳተፋሉ" ብሏል።

ቢቢሲ ሙንዶ የኮሎምቢያውያኑን ቁጥር በገለልተኝነት ማረጋገጥ አልቻለም። የጸጥታ ጉዳዮች ባለሙያዎች ማሪዮ ኡሬና ሳንቼዝ በበኩላቸው "የማይታወቅ ቁጥር" አይመስልም ብለዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ኮሎምቢያውያን የዩክሬን ጦርን ተቀላቅለዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የውጭ አገር ቅጥር

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

በውጭ አገር ጦርነቶች ለመሳተፍ ወደ ውጭ የሚጓዙ የኮሎምቢያ ወታደሮች ከብዙ አሥርት ዓመታት በፊት ጀምሮ የነበረ ጉዳይ ነው።

ለዓመታት የዘለቀው የትጥቅ ግጭት እና የአደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎች ላይ የተደረገ ዘመቻ፤ የደቡብ አሜሪካዋ አገር በመቶዎች የሚቆጠሩ ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው ወታደሮች እንድታገኝ ዕድል ፈጥሮላታል።

እነዚህ ወታደሮች በኮሎምቢያ በሚያገኙት ዝቅተኛ ገቢ ምክንያት ኑሯቸውን ለመግፋት ይቸገራሉ። አማራጭ የሥራ ዕድል ስለሌላቸው እንደዩክሬን ወይም ቀደም ባሉት ዓመታት ደግሞ እንደአፍጋኒስታን ወይም ኢራቅን በመሳሰሉ ጦርነቶች ለመሳተፍ ወደ ባህር ማዶ ያቀናሉ።

የቀድሞ ወታደራዊ መኮንን አልፎንሶ ማንዙር የኮሎምቢያ ጡረተኛ ወታደሮች ፖሊሲዎችን የሚከታተል ተመራማሪ ነው።

እንደማንዙር ከሆነ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ወደ ውጭ አገራት የሚሄዱት ወታደሮች ቁጥር ጨምሯል። ይህም ፕላን ኮሎምቢያ በሚባለው እና ከአሜሪካ ጋር በተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን እና የታጠቁ ቡድኖችን ለመዋጋት በአስር ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወታደራዊ ዕርዳታ ለአገሪቱ መሰጠቱን ተከትሎ የመጣ ነው።

"ይህ ደግሞ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በቂ የገቢ ምንጭ ሳይኖራቸው ጡረታ መውጣት የጀመሩትን የኮሎምቢያ ወታደሮች ቁጥር የበለጠ ጨምሮታል" ይላሉ ማንዙር።

እነዚህ የቀድሞ ወታደሮች ዝቅተኛ አደጋ ያላቸውን ሥራዎችን እንደሚያገኙ ቃል እየተገባላቸው በቀጥታ ወደ ጦር ግንባር እንዲላኩ መደረጉ የተለመደ ነው።

ቢቢሲ ሙንዶ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ እንደዘገበው ከሆነ ይህ ጉዳይ ወደ ዩክሬን በተጓዙ በበርካታ ኮሎምቢያዊያን ላይ እየደረሰ ነው። የሱዳኑም ከዚህ የተለየ ላይሆን ይችላል።

በደርዘን የሚቆጠሩ እና መዳረሻቸው ሱዳን የሆኑ ኮሎምቢያውያን "ግልጽ ባልሆነ ሂደት" በአፍሪካ የጸጥታ ተቋማት እንደሚሠሩ ተገልጾላቸው በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) በኩል እንዲጓዙ መደረጉን የቢቢሲ ሙንዶ ምንጮች ዘግበዋል።

ምንጮች ጉዳዩን የሚደግፍ ሰነድ ቢያቀርቡም ቢቢሲ ሙንዶ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አልቻለም።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በግጭቱ እጇን አስገብታ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን (አርኤስኤፍን) ትደግፋለች ሲል የሱዳን ጦር ይከሳል።

በሱዳን ጦር ከተገኙት ኮሎምቢያውያን መካከል በአርኤስኤፍ ጦር ውስጥ በተለያየ ደረጃ የሚሠሩ ባለማዕረግ አመራሮች እንደሚገኙበት አስታውቀዋል።

ከሎምባና ሞንካዮ ንብረቶች መካከል የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ገንዘብ እንደሚገኝበት የበይነ መረብ እና ቢቢሲ ቬሪፋይ የተመለከታቸው ቪዲዮዎች ያሳያሉ።

ሎምባና ሞንካዮ የዱባይ እና የአቡዳቢ ትዕይንቶችን ጨምሮ በቲኪቶክ እና በፌስቡክ ገጾቹ ላይ ጉዞውን በተመለከተ ያስቀመጠውን መረጃ ቢቢሲ ቬሪፋይ ተመልክቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጥር ወር ባወጣው ዘገባ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ወታደራዊ ድጋፍ ለመስጠት በሊቢያ፣ በቻድ እና በደቡብ ሱዳን በኩል ለአርኤስኤፍ የጦር መሳሪያ፣ የሎጅስቲክስ እና የተሽከርካሪ ድጋፍ እያደረገች ነው የሚለውን ሃሳብ "የሚታመን" ሲል ገልጾታል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ግን በሱዳን ግጭት ውስጥ እጇ እንደሌለበት በተደጋጋሚ አስተባብላለች።

የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ሚሊዮኖችን አፈናቅሏል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ወደ ሱዳን የሚወስደው መንገድ

ምሑሩ ኡሬና ሳንቼዝ እንደሚሉት ኮሎምቢያውያን በውጪ አገር የሥራ ዕድል የሚያገኙት በስም ጥር ወታደሮች በሚከፈቱ የዋትስአፕ አካውንቶች ነው። መጨረሻቸው ግን እንደሱዳን ያሉ የእርስ በርስ ጦርነትን ግጭቶች ውስጥ መዋጋት ነው።

"በሥራ ላይ ላሉ ወይም ጡረታ ለወጡ የኮሎምቢያ ወታደሮች ከገበያው በጣም ጨለማ ጎኖች አንዱ ነው" ብለዋል።

ሳንቼዝ እንደሚሉት ምልመላ የሚከናወነው "በወረቀት ላይ ባሉ ኩባንያዎች" ነው። ብዙውን ጊዜም የሚንቀሳቀሱት "በአንድ ሰው" ሲሆን ብዙ ጊዜም በከፍተኛ የኮሎምቢያ የጦር መኮንኖች በሚዘጋጁ የዋትአፕ አካውንቶች የሥራ ዕድሎቹ ይቀርባሉ።"

ኦማር አንቶኒዮ ሮድሪጌዝ ከበርካታ ዓመታት በፊት ጀምሮ የኮሎምቢያ የቀድሞ ወታደሮችን ለደህንነት ሥራ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚልክ ኩባንያ ነበረው። ወታደር ስለነበረ አሁንም ድረስ በውጭ አገር ከሚሠሩ በርካታ የቀድሞ ወታደሮች ጋር የቅርብ ግንኙነት አለው።

አንዳንዶቹ በሊቢያ ላለ የደህንነት ሥራ ተብለው ተቀጥረው በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኩል መጨረሻቸው የሱዳን ግጭት ውስጥ መሳተፍ እንደሆነ እንደነገሩት ሮድሪጌዝ ገልጿል።

"በሊቢያ የግል የደህንነት ሥራ እንደሚሰሩ ቃል ቢገባላቸውም ከአርኤስኤፍ ጎን በመሰለፍ ከሱዳን ጦር ጋር እንደሚዋጉ ለማወቅ ተችሏል" ሲል ለቢቢሲ ሙንዶ ተናግሯል።

"አንዳንዶችተመልሰዋል። ሌሎች ደግሞ በቦምብ ፍንዳታ እና በቀጥታ ግጭት ውስጥ ከተሳተፉ በኋላ (ወደ ኮሎምቢያ) ለመመለስ እየጠየቁ ነው ቢሆንም ግን ቀላል አይደለም" ይላል ሮድሪጌዝ።

ለአፍሪካ የደህንነት ሥራዎች የሚጓዙ የኮሎምቢያውያን እንደቀጠለ መሆኑን ሮድሪጌዝ እና በኮሎምቢያ የታተሙት ሪፖርቶች ገልጸዋል።

"የቋንቋ ችግር፣ የግዛቱ ስፋት እና ኮሎምቢያ በአፍሪካ ያላት ውሱን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ ኮሎምቢያዊያንን ለመውጣት ከባድ አድርጎታል" ሲል ኡሩዬና አክሎ ተናግሯል።

ቢቢሲ ሙንዶ በዚህ ታሪክ ውስጥ ከተካተቱት ክሶች ጋር በተያያዘ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አነጋግሯል።

"አገሪቱ በሱዳን ጦርነት ውስጥ እጇን ማስገባቷን" አጥብቆ በማስተባበል መግለጫ ሰጥቷል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በግጭቱ ለሚሳተፉ "ለሁለቱም ወገኖች ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ ወይም አቅርቦት" እንደማትሰጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። "አፋጣኝ የተኩስ ማቆም እና [ለግጭቱ] ሠላማዊ መፍትሄ እንዲሰጠውም" ጥሪ አቅርቧል።

የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እየተዋጉ ነው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ከዚህ ቀደም በርካታ ኮሎምቢያውያን የኤሚሬት ጦርን ተቀላቅለዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚገኙ ኮሎምቢያውያን

በሥራ ላይ ያሉም ሆነ ጡረታ የወጡ የኮሎምቢያ ወታደሮች ሄደው ለመሥራት ከሚፈልጓቸው አገራት አንዷ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ናት። አንደኛው ምክንያት ደግሞ የሚያገኙት ከፍተኛ ደሞዝ ነው።

የክራይስስ ግሩፕ የደኅንነት እና የግጭት ተንታኝ የሆኑት ኤልዛቤት ዲኪንሰን ግን ጡረታ የወጡ የኮሎምቢያ ወታደሮች በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተመልምለው "ከዓመታት በፊት በየመን ግጭት ውስጥ የተሳተፉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።"

"በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ብቻ እንደሚሰለጥኑ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እንደሚኖሩ እና መቼም ወደ ጦርነት እንደማይላኩ የሚያምኑ በጡረታ የወጡ ወታደሮችን ከዚህ ቀደም አናግሬአለሁ። መጨረሻቸው ግን ከዚህ በጣም የተለየ ሁኔታ ነው" ሲሉ ዲኪንሰን ለቢቢሲ ሙንዶ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በዚህ ዘገባ ላይ ከተጋለጡት ሁነቶች እና ምስክርነቶች ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላት ብትገልጽም "አሁን እየተከሰቱ ያሉ አጠራጣሪ ምልመላዎች እንዳሉ እንድታምን ያደርግሃል" ብለዋል።

እአአ 2010 መጀመሪያ ላይ የኮሎምቢያን ጦር ለቀው የወጡ በርካታ በሥራ ላይ ያሉ ወይም ጡረታ የወጡ ወታደሮች የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኃይሎችን ተቀላቅለዋል።

የዚህ እቅድ አካል ሆነው የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጦርን የተቀላቀሉት ኮሎምቢያውያን በሱዳኑ ጦርነት ስለመሳተፋቸው የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ የለም።

"ይህም የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የላቲን አሜሪካውያን ማለትም ኮሎምቢያውያን፣ ፓናማውያን፣ ቺሊውያን እና ሳልቫዶራውያን ያካተተ ወታደራዊ ክፍሎችን እና ሻለቆችን ለማቋቋም ያላት እቅድ አካል ናቸው" ሲሉ ሮድሪጌዝ ያስረዳሉ። ይህ ግን በህጋዊ መንገድ መከናወኑን እና ከአሁኑ የሱዳን ግጭት ጋር እንደማይያዝ አስታውቀዋል።

"ሌሎችም በህጋዊ መንገድ ከግል የደህንነት ኩባንያዎች ጋር የስለላ ስራዎችን ለመሥራት ሄደዋል" ሲል አክለዋል።

የኮሎምቢያ ወታደሮች ደሞዝ ከ500-700 ዶላር ይደርሳል። በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚያገኙት ከኮሎምቢያው ከአራት እስከ አምስት እጥፍ ሊበልጥ ይችላል።

"ይህ ሳቢ በመሆኑ የወቅቱ የጁዋን ማኑዌል ሳንቶስ መንግስት (2010-2018) የመከላከያ ሚኒስትር ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አቅንተው ኮሎምቢያውያንን ላለመጉዳት ሂደቱ ህጋዊ እንዲሆን ጠይቀዋል" ሲሉ ያስታውሳሉ።

"የደህንነት ትብብር በኮሎምቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት መሠረት ነበር። በዚህ ብቻ ሳይወሰን በንግድ እና በኢንቨስትመንት ዘርፎችም እያደገ ነው" ብለዋል ባለሙያው።

ሰፊው እና ህገወጡ ገበያ

በሱዳን ውስጥ ያሉ ክስተቶች ኮሎምቢያውያን የቀድሞ ወታደሮች ከሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕጽ ጦርነቶች እስከ ሄይቲ ግጭት ተኩስ ድረስ ሊገቡ እንደሚችሉ የሚያስታውስ ነው።

"ኮሎምቢያ ውስጥ ቅትረኛ ነፍሰ ገዳእነት መታገድ አለበት። ወታደሩ ኮሎምቢያ ውስጥ የተሻለ ኑሮ ሊኖረው ይገባል። በውጭ አገራት በሚፈሰው የወጣት ወታደሮች ደም ትርፍ የሚያገኙ ሰዎች መቀጣት አለባቸው" ብለዋል የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ።

በኮሎምቢያ ውስጥ ላሉ በርካታ የጸጥታ ባለሙያዎች ግን በአሁኑ ጊዜ በውጪ አገራት ግጭቶች ሕይወታቸውን ለአደጋ የሚያጋልጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ፍላጎቶች ማሟላት ያልቻሉ የሚመስሉ የወታደሮች ፖሊሲዎችን ሳያሻሽሉ ችግሩን ለመፍታት አስቸጋሪ ይሆናል።