የቢቢሲ ዋትስአፕ ቻናል እና ማኅበረሰብ የግል መረጃ ጥበቃ ማስታወቂያ
እርስዎ በእኛ ላይ የሚኖርዎ እምነት በጣም ያስፈልገናል። ይህ ማለት ቢቢሲ የእርስዎን የግል ደኅንነት እና መረጃ ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው ማለት ነው። እንዴት እና ለምን እንደዚህ ዓይነቶቹን ግላዊ መረጃዎች እንደምንጠቀም ለማወቅ ይህንን ማስታወቂያ ማንበብዎ አስፈላጊ ነው። ይህ የግል ማስታወቂያ በመረጃ ጥበቃ ሕግ መሠረት ከእኛ ጋር በሚኖርዎ ግንኙነት ጊዜ እና በኋላ ላይ ግላዊ መረጃን እንዴት እንደምንሰበስብ እና እንደምንጠቀም ይገልጻል።
ቢቢሲ ምን ዓይነት የግል መረጃ እንደሚሰበስብ እና እንደሚጠቀም
የቢቢሲ ቻናሎች እና ቡድኖችን ሲቀላቀሉ እና ሲከታተሉ ለመስጠት የፈቀዷቸውን ግላዊ መረጃዎች ይሰበስባል፤ ያደራጃል። እነዚህ መረጃዎችም ከታች ከተዘረዘሩት የተወሰኑትን ወይም ሁሉንም ሊያካትት ይችላል።
ግላዊ መረጃ
የሚሰበሰቡት ግላዊ መረጃዎች የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፦
- ገጽ/አካውንት/በዋትስአፕ ላይ የሚታይ የመለያ ስም
- የሞባይል ቁጥርን የመሳሰሉ የአድራሻ ቁጥሮች
- የሚታዩ ምሥሎች
የሚታይ ምሥልዎን ሁኔታ እና የግላዊ መረጃ ደኅንነት መቆጣጠሪያ ይዘትን (ፕራይቬሲ ሴቲንግ) መሠረት በማድረግ፣ ሊገልጿቸው የፈቀዷቸውን የልዩ መደብ መረጃዎች በመባል የሚታወቁትን ስሱ መረጃዎች ቢቢሲ ይሰበስባል፤ ያደራጃል። ይህ ለምሳሌ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦
- ዘርን ወይም ጎሳን
- የጤና መረጃን
- ሃይማኖትን ወይም የፍልስፍና አቋምን
- የወሲብ ዝንባሌን
- ፖለቲካዊ አመለካከትን
የዋትስአፕ መለያ ምሥልን ወደ ግል መረጃ ማዞር
በዋትስአፕ አካውንትዎ ላይ ያለውን ምሥል ሁሉም ሰው እንዲያይ ከፈቀዱ፣ ቢቢሲም ይህን መረጃ ሊያየው ይችላል። ከእኛ ጋር በዋትስአፕ የሚያጋሩትን ግላዊ መረጃ ለመቀነስ የሚሹ ከሆነ የግላዊ መረጃ መቆጣጠሪያዎን ለሚያውቋቸው ሰዎች ብቻ (ኮንታክትስ ኦንሊ) እንዲቀይሩ ይበረታታሉ።
መረጃዎችን የሚቆጣጠረው ማነው?
ቢቢሲ ከእርስዎ የተሰጡትን ማናቸውንም ግላዊ መረጃዎች እንዲሁም በቢቢሲ መሣሪያዎች እና ሥርዓቶች ላይ የተከማቹ መረጃዎችን በነጻነት ይቆጣጠራል።
ዋትስአፕ በመተግበሪያው በኩል የምትልኩትን ማንኛውንም መረጃ በተመለከተ ራሱን የቻለ “የመረጃ ተቆጣጣሪ” ነው። ስለዚህም ለዋትስአፕ የግላዊ መረጃ ፖሊሲ እና የአገልግሎት ደንቦች ተገዢ መሆንዎን መዘንጋት የለብዎትም። ዋትስአፕ የእርስዎን መረጃ በሜታ ኩባንያዎች መካከል ሊያጋራ ይችላል።
እያንዳንዱ የመረጃ ተቆጣጣሪ የእርስዎን የግል መረጃ ጥቅም ላይ የሚያውልበት እና የሚያደራጅበትን መንገዶች የሚያራዝመው እና የሚወስነው በራሱ ነው። ጥርጣሬን ለማስወገድ የግል መረጃዎ በቢቢሲ የሚሰበሰበውና እና የሚደራጀው በዚህ የግላዊ መረጃዎች ጥበቃ ማስታወቂያ ላይ ለተቀመጡት ዓላማዎች ብቻ ነው። ይህም የቢቢሲ ዋትስአፕ ቻናልን መቀላቀል እና መከተል ነው። ስለዚህም እያንዳንዱ የግላዊ መረጃ ተቆጣጣሪ የግላዊ መረጃ ጥበቃ ሕግን ማክበርን እና ይህንንም የመፈጸም ኃላፊነት አለበት።
የእርስዎን ግላዊ መረጃን ለማደራጀት ሕጋዊ መሠረት
እርስዎን የሚመለከት የግል መረጃን ለመጠቀም በሚሰጡት ፍቃድ ላይ እንመሠረታለን። ይህም የሚሆነው ወደ ዋትስአፕ ቻናላችን ለመግባት መርጠው ሲወስኑ ነው። በቻናላችን በኩል የሚቀርቡ ዜናዎች እና ታሪኮችን መከታተል ማቆም ከፈለጉ በማንኛውም ጊዜ እራስዎን ከቻናሉ በማስወጣት ፈቃድዎን ማንሳት ይችላሉ።
የእርስዎን መረጃ ማጋራት
ቢቢሲ ያለ ፈቃድዎ ግላዊ መረጃዎትን ለየትኘውም ሦስተኛ ወገን አያጋራም።
መረጃዎን ይዞ ማቆየት
ቢቢሲ በዚህ የግላዊ መረጃ አያያዝ ማስታወቂያ ውስጥ የተቀመጡትን ዓላማዎች ለመፈጸም አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ የእርስዎን ግላዊ መረጃ ያደራጃል።
የእርስዎ መብቶች እና ተጨማሪ መረጃ
በዩናይትድ ኪንግደም የመረጃ ጥበቃ ሕግ መሠረት መብቶች አልዎት። ቢቢሲ እነዚህን መረጃዎች እስከያዘ ድረስ የእርስዎን የቢቢሲ አካውንት መረጃ እና ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ጨምሮ እርስዎን የሚመለከቱ መረጃዎችን ቅጂ መጠየቅ ይችላሉ።
በሚከተለው የኢሜይል አድራሻችን ሊያገኙን ይችላሉ [email protected]።
ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም ስለ መብቶችዎ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ማግኘት ከፈለጉ፣ እባክዎ የቢቢሲን ግላዊ መረጃ እና የኩኪስ ፖሊሲን http://www.bbc.co.uk/privacy ላይ ይጎብኙ።
ቢቢሲ የእርስዎን ግላዊ መረጃ የሚይዝበትን መንገድ በተመለከተ ስጋት ካልዎት፣ ለዚሁ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ላለው ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን፣ የመረጃ ኮሚሽነር ቢሮ (ICO) https://ico.org.uk ማቅረብ ይችላሉ።
ይህን የግላዊ መረጃ ማስታወቂያ ማሻሻል በተመለከተ
የእርስዎን ግላዊ መረጃ በምንጠቀምበት መንገድ ላይ ጉልህ ለውጦች ካሉ ይህንን የግላዊ መረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ማስታወቂያውን እንከልሳለን።












