ቡና ስናፈላ ወደ ጀበና የምንጨምረው የቡና መጠን ሲበዛ አካባቢ ይበከላል?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በየቀኑ ሁለት ቢሊዮን ስኒ ቡና በመላው ዓለም ይጠጣል።
ዝነኛው ቡና እንደ የአገሩ ባህል በተለያየ መንገድ ነው የሚፈላው።
በኢትዮጵያ በሸክላ ጀበና ቡና ማፍላት ይዘወተራል።
ቡናን በማሽን የሚያፈሉም አሉ።
ቡና ሲፈላ ጥቅም ላይ የሚውሉ ፕላስቲክ ነኮቹ ቁሶች (capsules) አካባቢን እንደሚበክሉ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ከፕላስቲክ ወይም አልሙንየም የሚሠሩ (pods) መጠቀምም አጠያያቂ ሆኖ ቆይቷል።
በካናዳ፣ ኪውቤክ ግዛት የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው፣ ቡና በባህላዊ መንገድ ሲፈላ የበለጠ አካባቢን ይበክላል።
ለምን? ቢባል፣ አንድ ስኒ ቡና ለማፍላት የሚያስፈልገው የቡና መጠን እና ኃይል ይጨምራል። ቡናውን ለማፍላት እንዲሁም ለማሞቅም የሚያስፈልገው የኃይል መጠንም ከፍ ስለሚል ብክለት ይጨምራል ይላል።
ከፕላስቲክ እና ከአልሙንየም የሚሠራ ቡና ማፍያ ለማዘጋጀት ከባድ ከመሆኑ ባሻገር በድጋሚ ጥቅም ላይ ለማዋልፍ ይፈትናል።
ይህም እአአ ከ2021 እስከ 2022 የገበያ ድርሻው በ24 በመቶ ሲያድግ፣ በዓለም 12.33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቷል።
በ2016 የጀርመኗ ሀምቡርግ ክልከላ የጣለችው ያለ ምክንያት አልነበረም።
የካናዳ አጥኚዎች እንደሚሉት ግን ቡና ከሚፈላባቸው መንገዶች ሁሉ አካባቢን የሚበክለው ይህኛው አይደለም።
ጥናቱን የሠሩት 280 ሚሊ ሊትር ቡና በማፍላት በሂደቱ የሚፈጠረውን የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት (Greenhouse Gas emissions ወይም GHG) በመለካት ነው።
ምርምሩ የተካሄደው የቡና ፍሬን ከማምረት ጀምሮ ነው። ቡና ተተክሎ እስኪበቅል ያለው ሂደት፣ ከሌሎች ቡና ለማፍላት ከሚያስፈልጉ ሂደቶች በላቀ ከፍተኛ የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት የሚያስከትል ነው።
ምርምሩ ከቡና ተከላ ጀምሮ አንድ ስኒ ቡና ሲጠጣ እስከሚፈጠረው ትራፊ ድረስ ነው የተደረገው።
ቡና ለማፍላት ከሚፈለገው በላይ የቡና ዱቄት ሲጨመር የአካባቢ ብከላው መጠንም ይጨምራል።
ብዙዎች ቡና ሲያፈሉ የሚያስፈልጋቸውን የቡና ዱቄት መጠን አይወስኑም። ከሚያስፈልገው የቡና ዱቄት ከ20 በመቶው የበለጠ ነው የሚጠቀሙት።
በካናዳ ኪውቤክ እና አልበርታ ያለው ከቡና ጋር የተያያዘ የአካባቢ ብክለት ሲወዳደር በባህላዊ መንገድ ቡና የሚዘጋጅበት ቦታ ነው የበለጠ ብክለት የገጠመው።
በባህላዊ መንገድ ቡና ሲዘጋጅ የሚያመነጨው ካርቦን ዳይኦክሳይድ ይጨምራል።
ሁለተኛው አካባቢ የሚበክለው ቡና አሠራር ፍሬንች ፕረስ ነው። ይህም ቡና ለማፍላት የሚፈልገው ቡና መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው።
ካፕሱል ሦስተኛው በካይ ነው። ምክንያቱም የቡና ዱቄቱን መጠን መቆጣጠር ይቻላል። በዚህ መንገድ ከ11 እስከ 13 ግራም ቡና ማትረፍ ይቻላል።
ተዘጋጅቶ የተቀመጠ ቡና (Instant coffee) በሞቀ ውሃ ደባልቆ መጠጣት አካባቢን ከማይበክሉ የቡና አጠጣጦች ቀዳሚው ነው።
ከጥናቱ ፀሐፊዎች አንዱ ሉቺያኖ ሮድሪጌስ ቪና እንደሚሉት፣ ቡና ወዳጆች ቡና በአካባቢ የሚፈጥረውን ብክለት ለመቆጣጠር ይቸገራሉ።
“በዋናነት አካባቢ የሚበክለው ቡና ማሳ ላይ ሳለ ነው። ቡና በየትኛውም መንገድ ቢፈላ ሲበቅል ያለው ብክለት ያህል አይፈጥርም። ቡና ማሳ ላይ ሳለ ከ40 በመቶ እስከ 80 በመቶ ብክለት ይፈጠራል” ይላሉ።
ፀሐፊው የሚመክሩት የምንጠጣው የቡና መጠን እንዲቀንስ ነው። ለምሳሌ ከ50 ሚሊሊትር እስከ 100 ሚሊሊትር የሚደርስ ቡና ቢጠጣ ይመክራሉ።
ለዚህ የሚመጥን የቡና ዱቄት ብቻ መጨመር፣ ቡና ከተፈላ በኋላ የሚፈጠረውን ተረፈ ምርት መጠንም ይቀንሳል።
በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ በሚውል መንገድ ቡናን ማፍላትም ተረፈ ምርትን ለመቀነስ ይረዳል።












