ከጦርነት ሽሽት ከቤተሰቡ ተለይቶ አስራ አንድ አገራትን ያቆራረጠው ስደተኛ ታዳጊ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,

ከአስር ዓመታት በፊት የተቀሰቀሰው የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት የአገሪቱን ዜጎች አገራትን እንዲሰደዱ አድርጎ ኢትዮጵያን ጨምሮ እግራቸው ወደመራቸው አገር ለመሰደድ ተገደዋል።

ጦርነቱ ሲነሳ ገና የስድስት ዓመት ታዳጊ የነበረው ኻሊል ከወላጆቹ ጋር ነበር ለስደት የወጣው። ኋላ ላይ ግን ከቤተሰቡ ተለይቶ የአስራአ አንድ አገራትን ድንበሮች እያቆራረጠ ሰርቢያ ደርሷል።

ቤተሰቡ ደግሞ ከቱርክ ሆነው በሕጋዊ መንገድ ወደ ኔዘርላንድስ በመሻገር ለመኖር የሚያስችላቸው ፈቃድ በማግኘታቸው መጨረሻ ላይ ከቤተሰቡ ጋር ለመቀላቀል ችሏል።