ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰውን ወይም ኤአይን እያወራን እንደሆነ እንዴት መለየት እንችላለን?
ከሌላ ሰው ጋር ወይንም ከሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ጋር እያወራን እንደሆነ ማወቅ ወይም መለየት እንችላለን?
ይህ ጥያቄ ኮምፒውተሮች በሰው ሠራሽ አስተውሎት ምን ያህል እንደበለፀጉ ለማወቅ ለረጅም ጊዜ ሲጠየቅ ከነበረው ጥያቄ ውስጥ አንዱ ነው።
የዚህ ጥያቄ መነሻ 'የተርኒንግ ፈተና' በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ እንግሊዛዊ የሒሳብ እና የኮምፒውተር ተመራማሪ አለን ተርኒንግ የማሽኖችን ዕውቀት ለመጀመሪያ ጊዜ በስሌት መለካት እንደሚቻል ያቀረቡት ሀሳብ ነው።
በፈተናው መሠረት የኮምፒውተሮች ባህሪ ከሰዎች የማይለይ ከሆነ "ልሂቅ" ባህሪ አሳየ መባል ይችላል።
በአውሮፓውያኑ 2014 የኤአይ ቻትቦት ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተናውን ማለፋቸው ሲነገር ክስተቱ ወሳን ምዕራፍ ከመሆን ይልቅ ውዝግቡን አባብሶታል።
የማስመሰል ጨዋታ
'የተርኒንግ ፈተና' አንድ ሰው በጽሑፍ ለኮምፒውተር እና ለሰው እኩል በመናገር የማስመሰል ጨዋታ ነው።
የትኛው ኮምፒውተር የትኛው ሰው ነው የሚለውን ከመወሰናቸው በፊት የፈለጉትን ማንኛውም ጥያቄ ይጠይቃሉ።
በኒው ዮርክ በሚገኘው ስቶኒ ብሩክ ዩኒቨርስቲ የሥነ ልቦና ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ካሜሮን ጆንስ "ተርኒንግ ያለው ሰዎች በማሽን እና በሰው መካከል በእርግጠኝነት ልዩነቱን መናገር ካልቻሉ ሰው ያስባል፤ ማሽን ግን አይችልም የምንልበት ምንም መሠረት የለም" ይላሉ።
ተርኒንግ በአውሮፓውያኑ 2000 ዓመት ከአምስት ደቂቃ ጥያቄ በኋላ ቢያን 30 በመቶ ጊዜ ኮምፒውተሮች እንደ ሰው መምሰል እንደሚችሉ ተንብየዋል።
'ፍትሐዊ ያልሆነ ጨዋታ'
በአውሮፓውያኑ 2014 'ዩጂን ጉስትማን' የተባለ የኤአይ ቻትቦት በ'ተርኒንግ ፈተና' 33 በመቶ ሰው እንደሆነ ዳኞችን አሳምኗል። ይህም በአወዳዳሪዎች የተቀመጠውን ዝቅተኛ ቁጥር ተሻግሮ ያለፈ ነው።
ቻትቦቱ በእንግሊዘኛ በመግባባት የ13 ዓመት ዩክሬናዊ ልጅን ባህሪ መውረስ ችሏል።
በጀርመን በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ተጋባዥ መምህር እና ፈላስፋ የሆኑት ዶ/ር ማርከስ ፓንታስራ ይህ ማለት "ፍትሐዊ ያልሆነ ጨዋታ" እየተጫወተ ነው ማለት ነው ይላሉ።
"የቻትቦቱ የእንግሊዘኛ ጉድለት የዩክሬን ታዳጊ ካለው ጉድለት ጋር የሚገጣጠም ዓይነት ነው" ሲሉ ይከራከራሉ።
ከዚህን ጊዜ በኋላ የላቁ መሳሪያዎች 'የተርኒንግን ፈተና' ማለፋቸው ተነግሯል።
በ2025 ጅማሮ ላይ በታተመ ጽሑፍ ዶ/ር ጆንስ የኦፕንኤአይ ንብረት የሆነው 'ቻትጂፒቲ 4.5' ከአቻው ሰው ይልቅ 73 በመቶ ሰው መሆኑ በዳኞች መረጋገጡን ይጠቅሳሉ።
የሜታ ኩባንያው 'ላማ 3.1' 56 በመቶ ሰው ተብሎ በዳኞች ተረጋግጧል።
"[የኮምፒውተር] ሞዴሎች ከሰዎች በላይ ሰው እንደሆኑ በዳኞች አላለፉም ብሎ መከራከር በጣም ከባድ ነው" ይላሉ።
ይሁን እንጂ አንዳንዶች ይህ ማለት ኮምፒውተሮች በእውነት ያስባሉ የሚለውን አያረጋግጥም የሚሉ ተጠራጣሪዎች አሉ።
የቻይናው ክፍል መከራከሪያ
በ1980 ፈላስፋው ጆን ሰርል፤ 'ቻይኒዝ ሩም' የተሰኘ መከራከሪያ ይዞ ብቅ አለ።
መከራከሪያው ይህ ነው፡ ቻይንኛ ቋንቋ መናገር የማይችል እንግሊዛዊ ቻይንኛ ጽሑፍ ያለበት ቤት ውስጥ ከእንግሊዝኛ መመሪያው ጋር እንዲዘጋበት ተደረገ።
ውጭ ያሉ ሰዎች በቻይና የተፃፉ ጥያቄዎችን በወረቀት ያስገቡለታል። እሱን መመሪያውን ተከትሎ በቻይንኛ ምላሽ ይሰጣል።
ከክፍሉ ውጭ ላሉ ሰዎች እንግሊዛዊው ግለሰብ ቻይንኛ እንደሚናገር ሊያስቡ ይችላሉ። ነገር ግን ሰውየው ምን እያለ እንደሆነ አያውቀውም።
አንዳንዶች ይህ መከራከሪያ ለኮምፒውተሮችም ይሠራል ይላሉ። እኒህ ቁሶች የተሠራላቸው ፕሮግራም ትክክለኛውን ምላሽ እንዲሰጡ ነው እንጂ የሚሉት አያውቁትም።
ቱሪንግ ቴስት ሰው ሠራሽ አስተውሎትን መለየት እንደሚችል ቢናገርም እውነታው ግን ማሺን የሰውን ልጅ ምን ያህል ማስመሰል ይችላል የሚለውን ብቻ ነው የሚረዳው" ይላሉ መቀመጫቸውን ካሊፎርኒያ ያደረጉት የሶፍትዌር ኢንጂነሩ ጆርጅ ማፖራስ።
ይህን ለማብራራት ምሳሌ ተጠቅመው ያስረዳሉ።
"የትኛውንም ዓይነት የኤአይ ጥያቄ እና መልስ መስጫ ሳጥን (ቦት) ከፍታችሁ ዲጂታል ያልሆኑ ሰዓቶች እንዴት እንደሚሠሩ ብትጠይቁት በቀላሉ ያስራዳችኋል" ይላሉ።
ነገር ግን አሁን ያለንበትን ትክክለኛ ሰዓት የሚያሳይ ሰዓት ፎቶ ስጠኝ ብትሉት የወቅቱ የኤአይ ሞዴሎች የመሳሳት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
"ይህን መረጃ ለመረዳት ይከብደዋል።"
ተለዋጭ ሙከራዎች
ፓንትሳር ባለፉት ዓመታት ከቀረቡት በርካታ አማራጮች መካከል አንዱ የሆነውን "በማኅበረሰብ ላይ የተመሠረተ የአስተውሎት መፈተኛ" ይዞ ብቅ ብሏል።
ከቱሪንግ ሙከራ በተለየ ኤአይ ሰዎች ሳያውቁት ማኅበረሰብ ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል። ለምሳሌ ኢንተርኔት ላይ የተሰባሰቡ የሒሳብ አዋቂዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
ከዚያም የማኅበረሰቡ አባላት ይህ ነገር ማሺን ነው አይደለም የሚለውን በራሳቸው መለየት ይችላሉ ወይ የሚለውን መከታተል ነው።
ይህ ጉዳይ ማታለል ነው ተብሎ ቢቆጠርም ፓንትሳር ግን ማሺን "ልክ እንደ ሰው ሆኖ እንዴት መኖር ይችላል" የሚለውን ለማሳየት የሚደረግ ነው ይላሉ።
ምንም እንኳ ትችቶች ቢቀርቡበት የቱሪት መኩራ አሁን ባለንበርት የኤአይ ዓለም ቦታ አለው ሲሉ የሚከራከሩ አሉ።