ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ስለቢቢሲ አማርኛ ዳታ ቆጣቢ ድረ ገጽ የበለጠ ለመረዳት
የቢቢሲ አማርኛ ዳታ ቆጣቢ ድረ ገጽ ሙሉው የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ይዘት በጽሁፍ ብቻ የሚቀርብበት ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያቱ ደካማ የኢንተርኔት ግንኙነት ባለባቸው ቦታዎች ገጻችን በቀላሉ እንዲከፍት እና የተጠቃሚዎችን የኢንተርኔት ዳታን ለመቆጠብ ነው።
በዚህ ዳታ ቆጣቢ ገጻችን ላይ ከፍ ያለ ዳታን ከሚፈልጉት ፎቶግራፎች እና ቪዲዮዎች ውጪ ሁሉም ይዘት ምንም ሳይጎድል በጽሁፍ በቀላሉ ያገኙታል።
የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ተጠቃሚዎች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ውስጥ፣ የተለያየ የኢንተርኔት ዳታ አቅርቦት፣ ዋጋ እና መገልገያዎችን እንሚጠቀሙ እንረዳለን። ስለዚህም እንደተጠቃሚዎች ምርጫ እና የኢንተርኔት አቅርቦት አመቺ በሆነ ሁኔታ እንደ ፍላጎታቸው የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ ማንበብ ይችላሉ።
ስለዚህም ከዋናው የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ጎን ለጎን አዲሱን የድረ ገጻችንን ይዘት ለማቅረብ ዋናው ዓላማችን አንባቢዎች ዝቅተኛ የኢንተርኔት ዳታ በመጠቀም የቢቢሲ አማርኛ ገጾችን በቀላሉ እና በፍጥነት እንዲከፍቱ ማድረግ ነው።
ገጻችን ቀላል እና ያለብዙ ዳታ በፍጥነት እንዲከፈት አንዳንድ ለውጦችን አድርገናል። ለምሳሌም ቀለል ተደርጎ በቀረበው ገጻችን ላይ ምንም ዓይነት ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች እና የድምጽ ይዘቶች አይኖሩም።
ይህ ማለት ግን ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች እና ድምጾች ያሉትን የተመሳሳዩን ገጽ ይዘት ማየት ቢፈልጉ ፈጽሞ አያገኙትም ማለት አይደለም። ሙሉውን የገጹን ይዘት ለማንበብ፣ ለመመልከት እና ለማድመጥ ወደ ዋነኛው የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ በቀላሉ መመለስ ይችላሉ።
ይህ የቢቢሲ አማርኛ ቀለል ያለ አዲሱ ገጽታ ለተጠቃሚዎች አዲስ ሲሆን፣ በየጊዜውም እየተሻሻለ የሚሄድ ነው። ደካማ ኢንተርኔት ግንኙነት ባለባቸው እና ዳታ ውድ በሆነባቸው አካባቢዎች ላሉ የቢቢሲ አማርኛ ተከታታዮች ጠቃሚ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።